መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 23
23
ዳዊት የቂአላን ከተማ ከጥፋት እንደ አዳነ
1ለዳዊትም፥ “እነሆ፥ ፍልስጥኤማውያን ቂአላን ይወጋሉ፤ አውድማውንም ይዘርፋሉ” ብለው ነገሩት። 2ዳዊትም፥ “ልሂድን? እነዚህንስ ፍልስጥኤማውያንን ልምታን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፥ “ሂድ፤ ፍልስጥኤማውያንን ምታ፤ ቂአላንም አድን” አለው። 3የዳዊትም ሰዎች፥ “እነሆ፥ በዚህ በይሁዳ መቀመጥ እንፈራለን፤ ይልቁንስ ፍልስጥኤማውያንን ለመዝረፍ ወደ ቂአላ ብንሄድ እንዴት እንሆናለን?” አሉት። 4ዳዊትም ደግሞ እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም መልሶ፥ “ፍልስጥኤማውያንን በእጅህ አሳልፌ እሰጣለሁና ተነሥተህ ወደ ቂአላ ውረድ” አለው። 5ዳዊትና ሰዎቹም ወደ ቂአላ ሄዱ፤ ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ተዋጉ፤ እነርሱም ከፊቱ ሸሹ፤ እንስሶቻቸውንም ማረኩ፤ በታላቅም አገዳደል ገደሉአቸው። ዳዊትም በቂአላ የሚኖሩትን አዳነ።
6እንዲህም ሆነ፤ የአቤሜሌክ ልጅ አብያታር ወደ ዳዊት ወደ ቂአላ በኰበለለ ጊዜ ኤፉዱን ይዞ ወርዶ ነበር። 7ለሳኦልም ዳዊት ወደ ቂአላ እንደ መጣ ተነገረው፤ ሳኦልም፥ “መዝጊያና መወርወሪያ ወዳለባት ከተማ ገብቶ ተገኝቶአልና እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ ሰጥቶታል” አለ። 8ሳኦልም ወደ ቂአላ ወርደው ይዋጉ ዘንድ፥ ዳዊትንና ሰዎቹንም ይከብቡ ዘንድ ሕዝቡን ሁሉ አዘዘ። 9ዳዊትም ሳኦል በእርሱ ለክፋት ዝም እንደማይል ዐወቀ፤ ዳዊትም ካህኑን አብያታርን፥ “የእግዚአብሔርን ኤፉድ ወደዚህ አምጣ” አለው። 10ዳዊትም፥ “የእስራኤል አምላክ አቤቱ! በእኔ ምክንያት ከተማዪቱን ያጠፋ ዘንድ ሳኦል ወደ ቂአላ ሊመጣ እንደሚፈልግ እኔ ባሪያህ ፈጽሜ ሰምቻለሁ። 11የቂአላ ሰዎችስ ይከበባሉን? ባሪያህስ እንደ ሰማ ሳኦል በውኑ ይወርዳልን? የእስራኤል አምላክ አቤቱ! ለባርያህ ንገረው” አለ። እግዚአብሔርም፥ “ይወርዳል” አለ። 12ዳዊትም፥ “የቂአላ ሰዎች እኔንና ሰዎቼን በሳኦል እጅ አሳልፈው ይሰጡናልን?” አለ። እግዚአብሔርም፥ “አሳልፈው ይሰጡአችኋል” ብሎ ተናገረ። 13ዳዊትና ስድስት መቶ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አራት መቶ” ይላል። የሚሆኑ ሰዎችም ተነሥተው ከቂአላ ወጡ፤ ወደሚሄድበትም ይከተሉት ነበር። ሳኦልም ዳዊት ከቂአላ እንደ ሸሸ ሰማ፤ ስለዚህም ከመውጣት ቀረ። 14ዳዊትም በምድረ በዳ በጠባቡ በማሴሬም ይኖር ነበር፥ በአውክሞዲስ ውስጥም በዚፍ ተራራ ምድረ በዳ ተቀመጠ፤ ሳኦልም ሁልጊዜ ይፈልገው ነበር፤ እግዚአብሔር ግን በእጁ አሳልፎ አልሰጠውም። 15ዳዊትም ሳኦል ሊፈልገው እንደ ወጣ አየ፤ ዳዊትም በቄኒ ዚፍ ምድረ በዳ በአውክሞዲስ ውስጥ ይኖር ነበር። 16የሳኦልም ልጅ ዮናታን ተነሥቶ ወደ ዳዊት ወደ ቄኒ ሄደ። እጁንም በእግዚአብሔር አጸና። 17ለእርሱም “የአባቴ የሳኦል እጅ አታገኝህምና አትፍራ፤ አንተም በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆናለህ፤ እኔም ከአንተ በታች እሆናለሁ፤ ይህን ደግሞ አባቴ ሳኦል ያውቃል” አለው። 18ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን አደረጉ፤ ዳዊትም በቄኒ ውስጥ ተቀመጠ፤ ዮናታንም ወደ ቤቱ ሄደ።
19የዚፍ ሰዎችም ከአውክሞዲስ ወደ ሳኦል ወደ ኮረብታው ወጥተው እንዲህ አሉት፥ “እነሆ፥ ዳዊት በየሴሞን ቀኝ በጠባቡ በኩል በኤኬላ ኮረብታ ላይ በቄኒ ውስጥ በማሴሬት በእኛ ዘንድ ተሸሽጎ የለምን? 20አሁንም፦ ንጉሥ ሆይ! ለመውረድ ፈቃድህ ከሆነ ወደ እኛ ውረድ፤ በንጉሡ እጅ ጥሎታልና።” 21ሳኦልም አለ፥ “እናንተ ስለ እኔ አዝናችኋልና በእግዚአብሔር ዘንድ የተባረካችሁ ሁኑ፤ 22አሁንም ደግሞ ሂዱና አዘጋጁ፤ የተናገራችሁትንም፥ ያለበትንም ቦታ ሁሉ እንዳያታልላችሁ ፈጥናችሁ ዕወቁ። 23እንግዲህ ዕወቁ፤ ከአያችሁ በኋላ ከእናንተ ጋር እንሄዳለን፤ በዚያችም ምድር ካለ በይሁዳ አእላፍ ሁሉ እፈትሻታለሁ።”#ዕብ. “እርሱ የሚደበቅበትንና የሚሸሸግበትን ስፍራ እዩና ዕወቁ፤ በእርግጥም ወደ እኔ ተመለሱ፥ እኔም ከእናንተ ጋር እሄዳለሁ፤ በምድርም ውስጥ ቢሸሸግ በይሁዳ አእላፋት ሁሉ መካከል እፈልገዋለሁ” ይላል።
24የዚፍ ሰዎችም ተነሥተው ከሳኦል በፊት ሄዱ፤ ዳዊትና ሰዎቹ ግን በየሴሞን ቀኝ በኩል በዓረባ በማዖን ምድረ በዳ ነበሩ። 25ሳኦልና ሰዎቹም ሊፈልጉት ሄዱ፤ ለዳዊትም ነገሩት፤ እርሱም በማዖን ምድረ በዳ ወዳለው ዓለት ወረደ፤ ሳኦልም ያን በሰማ ጊዜ ዳዊትን በማዖን ምድረ በዳ ተከትሎ አሳደደው። 26ሳኦልና ሰዎቹም በተራራው በአንድ ወገን ሄዱ፤ ዳዊትና ሰዎቹም በተራራው በሌላው ወገን ሄዱ። ዳዊትም ከሳኦል ፊት ያመልጥ ዘንድ ተሰውሮ ነበር። ሳኦልና ሰዎቹ ዳዊትንና ሰዎቹን ለመያዝ ከብበዋቸው ነበርና። 27ወደ ሳኦልም መልእክተኛ መጥቶ፥ “ፍልስጥኤማውያን ሀገሩን ወርረውታልና ፈጥነህ ና” አለው። 28ሳኦልም ዳዊትን ማሳደድን ትቶ ተመለሰ። ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ሊዋጋ ሄደ። ስለዚህ የዚያ ስፍራ ስም የመለያየት ዓለት ተባለ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 23: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ