መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 8
8
እስራኤል ንጉሥ እንዲያነግሥላቸው ሳሙኤልን እንደ ጠየቁ
1እንዲህም ሆነ፤ ሳሙኤል በሸመገለ ጊዜ ልጆቹን በእስራኤል ላይ ፈራጆች አድርጎ ሾማቸው። 2የልጆቹም ስሞች እነዚህ ነበሩ። የበኵር ልጁ ስም ኢዩኤል፥ የሁለተኛውም ስም አብያ ነበረ። እነርሱም በቤርሳቤህ ፈራጆች ነበሩ። 3ልጆቹም በመንገዱ አልሄዱም፤ ነገር ግን ረብ ለማግኘት ፈቀቅ አሉ፤ መማለጃ በሉ፤ ፍርድ አደሉ።
4የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ በአንድነት ተሰብስበው ወደ ሳሙኤል ወደ አርማቴም መጡ፤ 5እንዲህም አሉት፥ “እነሆ፥ አንተ ሸምግለሃል፤ ልጆችህም በመንገድህ አይሄዱም፤ አሁንም እንደ ሌሎች አሕዛብ ሁሉ የሚፈርድልን ንጉሥ አንግሥልን።” 6“የሚፈርድልን ንጉሥ ስጠን” ባሉት ጊዜም ነገሩ ሳሙኤልን አስከፋው፤ ሳሙኤልም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። 7እግዚአብሔርም ሳሙኤልን አለው፥ “በእነርሱ ላይ እንዳልነግሥ እኔን ናቁ እንጂ አንተን አልናቁምና በሚሉህ ነገር ሁሉ የሕዝቡን ቃል ስማ። 8ከግብፅ ካወጣኋቸው ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን ትተው እንግዶች አማልክትን በማምለካቸው እንደ ሠሩት ሥራ ሁሉ እንዲሁ በአንተ ደግሞ ያደርጉብሃል። 9አሁንም ቃላቸውን ስማ፤ ነገር ግን ጽኑ ምስክር መስክርባቸው፤ በእነርሱም ላይ የሚነግሠውን የንጉሡን ሥርዐት ንገራቸው።”
10ሳሙኤልም የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ ንጉሥን ለፈለጉ ሕዝብ ነገራቸው። 11እንዲህም አለ፥ “በእናንተ ላይ የሚነግሠው የንጉሡ ሥርዐት ይህ ነው፤ ወንዶች ልጆቻችሁን ወስዶ ሰረገላ ነጂዎችና ፈረሰኞች ያደርጋቸዋል፤ በሰረገሎችም ፊት ይሮጣሉ፤ 12ለራሱም የሻለቆችና የመቶ አለቆች#“የመቶ አለቆች” የሚለው በዕብ. የለም። የአምሳ አለቆችም#“አምሳ አለቆችም” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ያደርጋቸዋል፤ እርሻውንም የሚያርሱ፥ እህሉንም የሚያጭዱ፥ ፍሬውንም የሚለቅሙ፥ የጦር መሣሪያውንና የሰረገሎቹንም ዕቃ የሚሠሩ ያደርጋቸዋል። 13ሴቶች ልጆቻችሁንም ወስዶ ሽቱ ቀማሚዎችና ወጥ ቤቶች፥ አበዛዎችም ያደርጋቸዋል። 14እርሻችሁንና ወይናችሁንም፥ መልካም መልካሙንም የዘይት ቦታችሁን ወስዶ ለሎሌዎቹ ይሰጣቸዋል። 15ከዘራችሁና ከወይናችሁም ዐሥራት ወስዶ ለጃንደረቦቹና ለሎሌዎቹ ይሰጣቸዋል። 16ሎሌዎቻችሁንና ገረዶቻችሁን፥ ከከብቶቻችሁና ከአህዮቻችሁም መልካም መልካሙን ወስዶ ያሠራቸዋል። 17ከላሞቻችሁ፥ ከበጎቻችሁና ከፍየሎችቻችሁም ዐሥራት ይወስዳል፤ እናንተም ባሪያዎች ትሆኑታላችሁ። 18በዚያም ቀን ለእናንተ ከመረጣችሁት ከንጉሣችሁ የተነሣ ትጮኻላችሁ፤ በእነዚያም ወራት እግዚአብሔር አይሰማችሁም። ለራሳችሁ ንጉሥ መርጣችኋልና።”
19ሕዝቡ ግን የሳሙኤልን ነገር ይሰሙ ዘንድ እንቢ አሉ፥ “እንዲህ አይሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አንግሥልን፤ 20እኛም ደግሞ እንደ አሕዛብ ሁሉ እንሆናለን፤ ንጉሣችንም ይፈርድልናል፤ በፊታችንም ወጥቶ ስለ እኛ ጠላታችንን ይዋጋል” አሉት። 21ሳሙኤልም የሕዝቡን ቃል ሁሉ ሰማ፤ ለእግዚአብሔርም ተናገረ። 22እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፥ “ቃላቸውን ስማ፤ ንጉሥም አንግሥላቸው” አለው። ሳሙኤልም የእስራኤልን ሰዎች፥ “እያንዳንዳችሁ ወደ ከተማችሁ ሂዱ” አላቸው።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 8: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ