መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 9
9
ሳኦል ከሳሙኤል ጋር እንደ ተገናኘ
1ከብንያም ልጆች ስሙ ቂስ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፥ እርሱም የአብሔል ልጅ፥ የያሬድ#ግእዝ “የአዴል” ይላል። ልጅ፥ የባሔር ልጅ፥ የብንያም ሰው፥ የአፌቅ ልጅ፥ ጽኑዕ ኀያል ሰው ነበረ። 2ለእርሱም ሳኦል የሚባል የተመረጠ መልካም ልጅ ነበረው፤ በምድር ሁሉ ላይ ከእስራኤል ልጆች ከእርሱ ይልቅ መልካም የሆነ ሰው አልነበረም፤ ከሕዝቡም ሁሉ ይልቅ ከትከሻውና ከዚያም በላይ ቁመቱ ዘለግ ያለ ነበረ። 3የሳኦልም አባት የቂስ አህዮች ጠፍተው ነበር፤ ቂስም ልጁን ሳኦልን፥ “ከብላቴኖቹ አንዱን ወስደህ ተነሡና ሄዳችሁ አህዮችን ፈልጉ” አለው። 4ወደ ተራራማውም ወደ ኤፍሬም ሀገር ሄዱ፤ በሲልካ ምድርም አለፉ፤ አላገኙአቸውምም፤ በፋስቂም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሴጋልም ሲል” ዕብ. “ሻዕል” ይላል። ምድር አለፉ፤ በዚያም አልነበሩም፤ በኢያሚንም ምድር አለፉ፤ አላገኙአቸውምም።
5ወደ መሴፋ#ግሪክ ሰባ ሊ. “ሴፍ” ይላል። ምድርም በደረሱ ጊዜ ሳኦል ከእርሱ ጋር የነበረውን ብላቴና፥ “አባቴ ስለ አህዮች ማሰብን ትቶ ስለ እኛ እንዳይጨነቅ፥ ና፤ እንመለስ” አለው። 6ብላቴናውም፥ “እነሆ፥ አንድ የእግዚአብሔር ሰው በዚህች ከተማ አለ፤ እርሱም የተከበረ ሰው ነው፤ የሚናገረው ሁሉ በእውነት ይፈጸማል፤ አሁንም ወደዚያ እንሂድ፤ ምናልባት የምንሄድበትን መንገድ ይነግረናልና” አለው። 7ሳኦልም አብሮት ያለውን ብላቴና፥ “እነሆ! እንሄዳለን፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ሰው ምን እንወስድለታለን? እንጀራ ከከረጢታችን አልቆአልና፤ ለእግዚአብሔር ሰው የምንወስድለት ምንም የለንም” አለው። 8ብላቴናው ደግሞ ለሳኦል መልሶ፥ “እነሆ፥ በእጄ የብር ሰቅል ሩብ አለኝ፤ እርሱንም ለእግዚአብሔር ሰው ትሰጠዋለህ፤ የምንሄድበትን መንገድም ይነግረናል። 9ቀድሞ ነቢዩን ባለ ራእይ ይሉት ነበርና አስቀድሞ በእስራኤል ዘንድ ሰው እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ሲሄድ፦ ኑ፤ ወደ ባለ ራእይ እንሂድ ይል ነበር።” 10ሳኦልም ብላቴናውን፥ “የተናገርኸው ነገር መልካም ነው፤ ና፤ እንሂድ” አለውና የእግዚአብሔር ሰው ወዳለበት ከተማ ሄዱ። 11በከተማዪቱም ዳገት በወጡ ጊዜ ቈነጃጅት ውኃ ሊቀዱ ሲወጡ አገኙና፥ “ባለ ራእይ በዚህ አለ ወይ?” አሉአቸው። 12ቈነጃጅቱም፥ “አዎን እነሆ፥ በፊታችሁ ነው። ዛሬ ወደ ከተማዪቱ መጥቶአልና፥ ዛሬም ሕዝቡ በባማ ኮረብታ ላይ መሥዋዕት ማቅረብ አለባቸውና። 13ወደ ከተማዪቱም በገባችሁ ጊዜ ለመብላት ወደ ባማ ኮረብታ ሳይወጣ በከተማው ውስጥ ታገኙታላችሁ፤ መሥዋዕታቸውን እርሱ የሚባርክ ስለሆነ እርሱ ሳይወጣ ሕዝቡ ምንም አይቀምሱምና፥ ከዚያም በኋላ እንግዶች ይበላሉና፤ በዚህም ጊዜ ታገኙታላችሁና አሁን ውጡ” አሉአቸው። 14ወደ ከተማዪቱም ወጡ፤ በከተማዪቱም መካከል በገቡ ጊዜ እነሆ፥ ሳሙኤል ወደ ባማ ኮረብታ ለመውጣት ወደ እነርሱ መጣ።
15ገናም ሳኦል ሳይመጣ ከአንድ ቀን በፊት እግዚአብሔር ለሳሙኤል ጆሮውን ከፈተለት፥ 16እንዲህም አለው፥ “ነገ በዚህች ሰዓት ከብንያም ሀገር አንድ ሰው እልክልሃለሁ፤ ልቅሶአቸው ወደ እኔ ስለ ደረሰ የሕዝቤን ሥቃያቸውን ተመልክችአለሁና ለሕዝቤ ለእስራኤል አለቃ ይሆን ዘንድ ትቀባዋለህ፤ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ ሕዝቤን ያድናል።” 17ሳሙኤልም ሳኦልን ባየ ጊዜ እግዚአብሔር፥ “ያ የነገርሁህ ሰው እነሆ፤ እርሱም በሕዝቤ ላይ ይነግሣል” አለው። 18ሳኦልም በበሩ ወደ ሳሙኤል ቀርቦ፥ “የባለ ራእዩ ቤት ወዴት እንደ ሆነ፥ እባክህ፥ ንገረኝ” አለው። 19ሳሙኤልም መልሶ ሳኦልን፥ “ባለ ራእዩ እኔ ነኝ፤ ዛሬም ከእኔ ጋር ወደ ባማ ኮረብታ በፊቴ ውጣና ምሳ ብላ፤ ነገም በጥዋት አሰናብትሃለሁ፤ በልብህም ያለውን ነገር ሁሉ እነግርሃለሁ፤ 20ከሦስት ቀንም በፊት የጠፉ አህዮችህ ተገኝተዋልና ልብህን አታስጨንቀው። የእስራኤል መልካም ምኞት ለማን ነው? ለአንተና ለአባትህ ቤት አይደለምን?” አለው። 21ሳኦልም መልሶ፥ “እኔ ከእስራኤል ነገዶች ከሚያንስ ወገን የሆንሁ ብንያማዊ ሰው አይደለሁምን? ወገኔስ ከብንያም ነገድ ወገኖች ሁሉ የሚያንስ አይደለምን? እንዲህስ ያለውን ነገር ለምን ነገርኸኝ?” አለ።
22ሳሙኤልም ሳኦልንና ብላቴናውን ወስዶ ወደ አዳራሽ አገባቸው፥ ሰባ#ዕብ. “ሠላሳ” ይላል። ሰዎችም ምሳ በሚበሉበት በምርፋቁ ራስ አስቀመጣቸው፤ 23ሳሙኤልም ወጥ ቤቱን፥ “በአንተ ዘንድ አኑረው ብዬ የሰጠሁህን እድል ፋንታ አምጣ” አለው። 24ወጥቤቱም ወርቹን አምጥቶ በሳኦል ፊት አኖረው። ሳሙኤልም፥ “ሳኦልን ለምስክር ከባልንጀራህ ተለይቶ ቀርቦልሃልና እነሆ፥ በልተህ የተረፈህን በፊትህ አኑር” አለው። በዚያም ቀን ሳኦል ከሳሙኤል ጋር በላ። 25ከባማ ኮረብታም ወደ ከተማዪቱ ወረዱ፤ ሳሙኤልም ለሳኦል በሰገነቱ ላይ መኝታ አዘጋጀለት፤ እርሱም ተኛ። 26ማልደውም ተነሡ፤ በነጋም ጊዜ ሳሙኤል ሳኦልን፥ “ከሰገነቱ ላይ ጠርቶ፦ ተነሣና ላሰናብትህ” አለው። ሳኦልም ተነሣ፤ እርሱና ሳሙኤልም ሁለቱ ወደ ሜዳ ወጡ። 27እነርሱም በከተማዪቱ ዳር ሲወርዱ ሳሙኤል ሳኦልን፥ “ብላቴናው ወደ ፊታችን እንዲያልፍ እዘዘው፤ አንተ ግን ከእኔ ጋር ከዚህ ቁምና የእግዚአብሔርን ቃል ስማ” አለው። ብላቴናውም አለፈ።#“ብላቴናውም አለፈ” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 9: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ