የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 9

9
ስለ ቅዱ​ሳን አገ​ል​ግ​ሎት
1ለቅ​ዱ​ሳን ስለ​ሚ​ደ​ረ​ገው አገ​ል​ግ​ሎት የም​ጽ​ፍ​ላ​ችሁ ብዙ አለኝ#ግሪኩ “ልጽ​ፍ​ላ​ችሁ አያ​ስ​ፈ​ል​ግም” ይላል። 2እና​ንተ እን​ደ​ም​ት​ተጉ አው​ቃ​ለ​ሁና፤ ስለ​ዚ​ህም “የአ​ካ​ይያ ሰዎች እኮ ከአ​ምና ጀምሮ አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ዋል” ብዬ በመ​ቄ​ዶ​ንያ ሰዎች ዘንድ አመ​ሰ​ገ​ን​ኋ​ችሁ፤ እነ​ሆም የእ​ና​ንተ መፎ​ካ​ከር ብዙ​ዎ​ችን ሰዎች አት​ግ​ቶ​አ​ቸ​ዋል። 3በዚ​ህም ያመ​ሰ​ገ​ን​ና​ችሁ ምስ​ጋና በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ሐሰት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ብን፥ እንደ ነገ​ር​ና​ቸ​ውም ተዘ​ጋ​ጅ​ታ​ችሁ እን​ዲ​ያ​ገ​ኙ​አ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ችን ወደ እና​ንተ ላክ​ና​ቸው።#ግሪኩ “ላክ​ኋ​ቸው” ይላል። 4ምና​ል​ባት የመ​ቄ​ዶ​ንያ ሰዎች ከእኔ ጋር ቢመ​ጡና ሳታ​ዘ​ጋጁ ቢያ​ገ​ኙ​አ​ችሁ እና​ንተ ታፍ​ራ​ላ​ችሁ ባል​ልም እኛ ስለ እና​ንተ ከነ​ገ​ር​ና​ቸው የተ​ነሣ እና​ፍ​ራ​ለን። 5ስለ​ዚ​ህም አስ​ቀ​ድ​መው ወደ እና​ንተ መጥ​ተው በቅ​ድ​ሚያ የተ​ና​ገ​ራ​ች​ኋ​ትን በረ​ከ​ታ​ች​ሁን እን​ዲ​ያ​ዘ​ጋጁ ወን​ድ​ሞ​ችን ማለ​ድሁ፤ እን​ደ​ዚ​ህም የተ​ዘ​ጋጀ ይሁን፤ በረ​ከ​ትን እን​ደ​ም​ታ​ገ​ኙ​በት እንጂ በን​ጥ​ቂያ እንደ ተወ​ሰ​ደ​ባ​ችሁ አይ​ሁን።
6አሳ​ንሶ የሚ​ዘራ ለእ​ርሱ እን​ዲሁ መከሩ ያን​ስ​በ​ታል፤ በብዙ የሚ​ዘራ ግን በብዙ ያመ​ር​ታል። 7ሁሉ ልቡ እንደ ወደደ ያድ​ርግ፤ በደ​ስታ ይስጡ እንጂ በግድ አይ​ሆ​ንም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በደ​ስታ የሚ​ሰ​ጠ​ውን ይወ​ዳ​ልና። 8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​ካ​ሙን ነገር ሁሉ ሊያ​በ​ዛ​ላ​ችሁ ይች​ላል፤ ፍጹም በረ​ከ​ቱ​ንም ለዘ​ወ​ትር ያበ​ዛ​ላ​ችሁ ዘንድ፥ ለሁ​ሉም ታተ​ር​ፉ​ታ​ላ​ችሁ፤ በጎ ሥራ መሥ​ራ​ት​ንም ታበ​ዛ​ላ​ችሁ። 9#መዝ. 111፥9። “በተነ፤ ለድ​ሃም ሰጠ፤ ጽድ​ቁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል” ብሎ መጽ​ሐፍ እንደ ተና​ገረ። 10#ኢሳ. 55፥10። እርሱ ዘርን ለዘሪ ይሰ​ጣል፤ እህ​ል​ንም ለም​ግብ ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ ዘራ​ች​ሁ​ንም ያበ​ዛ​ላ​ች​ኋል፤ የጽ​ድ​ቃ​ች​ሁ​ንም መከር ያበ​ጃል። 11ለብዙ ሰዎች ስለ ሰጣ​ች​ሁም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምስ​ጋና በም​ታ​ደ​ር​ግ​ላ​ችሁ ልግ​ስና ሁሉ ባለ​ጸ​ጎች ትሆ​ና​ላ​ችሁ። 12ይህቺ የዚህ ሥራ አገ​ል​ግ​ሎት ግዳጅ የም​ት​ፈ​ጽ​መው ለዚህ ለቅ​ዱ​ሳን ችግር መሟ​ላት ብቻ አይ​ደ​ለም፤ በቅ​ዱ​ሳን ዘን​ድም#ግሪኩ “በብ​ዙ​ዎች ዘንድ” ይላል። ደግሞ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምስ​ጋና ታበ​ዛ​ለች። 13ክር​ስ​ቶስ ላስ​ተ​ማ​ራት ትም​ህ​ርት ታዝ​ዛ​ች​ኋ​ልና፥ ሁላ​ች​ሁም ደስ ብሎ​አ​ች​ሁና ተባ​ብ​ራ​ችሁ አወ​ጣ​ጥ​ታ​ች​ኋ​ልና በዚች በሃ​ይ​ማ​ኖ​ታ​ችሁ ፈተና#ግሪኩ “በአ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ችሁ ፈተና” ይላል። ምክ​ን​ያት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤ 14እነ​ር​ሱም ስለ እና​ንተ ይጸ​ል​ያሉ፤ ስለ አደ​ረ​ባ​ችሁ ታላቅ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋም ሊያ​ዩ​አ​ችሁ ይመ​ኛሉ። 15ስለ​ማ​ት​መ​ረ​መ​ርና ባላ​ሰ​ቡ​አት ጊዜ ስለ​ም​ት​መ​ጣው#“ባላ​ሰ​ቡ​አት ጊዜም ስለ​ም​ት​መ​ጣው” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ጸጋው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ