የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ካልእ 9

9
ዳዊት ለዮ​ና​ታን ልጅ ቸር​ነት እንደ አደ​ረገ
1ዳዊ​ትም፥ “ስለ ዮና​ታን ቸር​ነት አደ​ር​ግ​ለት ዘንድ ከሳ​ኦል ቤት የቀረ አንድ ሰው አለን?” አለ። 2ከሳ​ኦ​ልም ቤት አንድ ብላ​ቴና ነበረ፤ ስሙም ሲባ ነበረ፤ ወደ ዳዊ​ትም ጠሩት፤ ንጉ​ሡም፥ “አንተ ሲባ ነህን?” አለው። እር​ሱም፥ “እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ነኝ” አለ። 3ንጉ​ሡም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቸር​ነት አደ​ር​ግ​ለት ዘንድ ከሳ​ኦል ቤት የቀረ ሰው አለን?” አለ። ሲባም ንጉ​ሡን፥ “እግ​ሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ የዮ​ና​ታን ልጅ አለ” አለው። 4ንጉ​ሡም፥ “ወዴት ነው?” አለው፤ ሲባም ለን​ጉሡ፥ “እነሆ እርሱ በሎ​ዶ​ባር በአ​ብ​ያል ልጅ በማ​ኪር ቤት አለ” አለው። 5ንጉ​ሡም ዳዊት ልኮ ከሎ​ዶ​ባር ከአ​ብ​ያል ልጅ ከማ​ኪር ቤት አስ​መ​ጣው። 6የሳ​ኦ​ልም ልጅ የዮ​ና​ታን ልጅ ሜም​ፌ​ቡ​ስቴ ወደ ዳዊት መጣ፤ በግ​ን​ባ​ሩም ወድቆ ሰገ​ደ​ለት፤ ንጉሥ ዳዊ​ትም፥ “ሜም​ፌ​ቡ​ስቴ ሆይ፥” አለ፤ እር​ሱም፥ “እነ​ሆኝ አገ​ል​ጋ​ይህ” አለ። 7ዳዊ​ትም፥ “ስለ አባ​ትህ ስለ ዮና​ታን ቸር​ነት ፈጽሜ አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለ​ሁና አት​ፍራ፤ የአ​ባ​ት​ህን አባት የሳ​ኦ​ልን መሬት ሁሉ እመ​ል​ስ​ል​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም ሁል ጊዜ ከገ​በ​ታዬ እን​ጀ​ራን ትበ​ላ​ለህ” አለው። 8እር​ሱም፥ “የሞተ ውሻ ወደ​ም​መ​ስል ወደ እኔ ትመ​ለ​ከት ዘንድ እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ምን​ድን ነኝ?” ብሎ ሰገደ።
9ንጉ​ሡም የሳ​ኦ​ልን አገ​ል​ጋይ ሲባን ጠርቶ፥ “ለሳ​ኦ​ልና ለቤቱ ሁሉ የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ ለጌ​ታህ ልጅ ሰጥ​ቻ​ለሁ። 10አን​ተና ልጆ​ችህ፥ ሎሌ​ዎ​ች​ህም ምድ​ሩን እረ​ሱ​ለት፤ ለጌ​ታ​ህም ልጅ እን​ጀራ ይሆ​ነው ዘንድ ፍሬ​ውን አግቡ፤ እና​ን​ተም ትመ​ግ​ቡ​ታ​ላ​ችሁ፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እር​ሱም እን​ጀራ ይብላ” ይላል።የጌ​ታህ ልጅ ሜም​ፌ​ቡ​ስቴ ግን ሁል​ጊዜ ከገ​በ​ታዬ ይበ​ላል” አለው። ለሲ​ባም ዐሥራ አም​ስት ልጆ​ችና ሃያ አገ​ል​ጋ​ዮች ነበ​ሩት። 11ሲባም ንጉ​ሡን፥ “ጌታዬ ንጉሡ አገ​ል​ጋ​ዩን እን​ዳ​ዘዘ እን​ዲሁ አገ​ል​ጋ​ይህ ያደ​ር​ጋል” አለው። ሜም​ፌ​ቡ​ስ​ቴም ከን​ጉሡ ልጆች እንደ አንዱ ከዳ​ዊት ገበታ ይበላ ነበር። 12ለሜ​ም​ፌ​ቡ​ስ​ቴም ሚካ የተ​ባለ ታናሽ ልጅ ነበ​ረው፤ በሲ​ባም ቤት ያሉ ሁሉ ለሜ​ም​ፌ​ቡ​ስቴ ያገ​ለ​ግሉ ነበር። 13ሜም​ፌ​ቡ​ስ​ቴም ከን​ጉሥ ገበታ ሁል​ጊዜ እየ​በላ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ኖረ፤ ሁለት እግ​ሮ​ቹም ሽባ ነበሩ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ