ተረፈ ባሮክ 2

2
1ያን​ጊ​ዜም ኤር​ም​ያ​ስና ባሮክ፥ “የዚህ ነገር ምል​ክት በእ​ው​ነት እንደ ተገኘ ዛሬ ዐወ​ቅን” ብለው አለ​ቀሱ። 2ኤር​ም​ያ​ስም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አን​ዲት ነገ​ርን እስ​ክ​ለ​ም​ነው ድረስ ከተ​ማ​ዋን ሁሉ እን​ዳ​ታ​ጠፉ እለ​ም​ና​ች​ኋ​ለሁ” ብሎ መላ​እ​ክ​ትን ማለ​ዳ​ቸው። 3ጌታም፥ “ከወ​ዳጄ ከኤ​ር​ም​ያስ ጋራ እስ​ክ​ነ​ጋ​ገር ድረስ ከተ​ማ​ዪ​ቱን አታ​ጥፉ” ብሎ ለመ​ላ​እ​ክት ነገ​ራ​ቸው።
4ኤር​ም​ያ​ስም ያን​ጊዜ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ ከአ​ንተ ጋር እና​ገር ዘንድ እዘ​ዘኝ” ብሎ ተና​ገረ፤ ጌታም፥ “ወዳጄ ኤር​ም​ያስ ሆይ፥ የም​ት​ወ​ድ​ደ​ውን ተና​ገር” አለው። 5ኤር​ም​ያ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “አቤቱ ጌታዬ፥ ይቺን ከተማ በጠ​ላ​ትዋ እጅ አሳ​ል​ፈህ እን​ደ​ም​ት​ሰ​ጣት የባ​ቢ​ሎ​ንም ሕዝብ እን​ደ​ሚ​ይ​ዟት እነሆ፥ ዛሬ ዐወ​ቅሁ። 6ተሰ​ው​ረን ስለ​ም​ና​ገ​ለ​ግ​ል​ባ​ቸው ንዋ​ያተ ቅድ​ሳት ምን አደ​ርግ ዘንድ ትወ​ድ​ዳ​ለህ? በላ​ያ​ቸ​ውስ ምን አደ​ርግ ዘንድ ትወ​ድ​ዳ​ለህ?” 7ጌታም አለው፥ “እነ​ር​ሱን ወስ​ደህ ለም​ድር አደራ ስጣት፤ አንቺ ምድር በው​ኆች ላይ የፈ​ጠ​ረሽ፥ በሰ​ባ​ቱም ማኅ​ተም ያተ​መሽ የፈ​ጣ​ሪሽ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰም​ተሽ ጌጥ​ሽን ተቀ​በዪ፤ ተወ​ዳ​ጁም እስ​ኪ​መጣ ድረስ ገን​ዘ​ብ​ሽን ጠብቂ በላት።” 8ኤር​ም​ያ​ስም እን​ዲህ ሲል ተና​ገረ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ ሕዝ​ቡን ብዙ ዘመን ለጠ​በ​ቃ​ቸው፥ እኔን ባሪ​ያህ ኤር​ም​ያ​ስ​ንም ከሀ​ገሩ ሰው ሁሉ ይልቅ ለጠ​በ​ቀኝ ለኢ​ት​ዮ​ጵ​ያ​ዊው ለአ​ቤ​ሜ​ሌክ የማ​ደ​ር​ገ​ውን ግለ​ጥ​ልኝ። 9እርሱ ከረ​ግ​ረግ ጕድ​ጓድ አወ​ጣኝ፤ እን​ዳ​ያ​ዝን የከ​ተ​ማ​ዋን ጥፋት ያይ ዘንድ አል​ወ​ድ​ለ​ትም።”
10ጌታም ለኤ​ር​ም​ያስ እን​ዲህ አለው፥ “ወደ አግ​ሪ​ጳስ ወይን ቦታ በዚህ ተራራ ጎዳና አቤ​ሜ​ሌ​ክን ላከው፤ ሕዝ​ቡን ወደ ሀገ​ራ​ቸው እስ​ክ​መ​ል​ሳ​ቸው ድረስ እኔ እሰ​ው​ረ​ዋ​ለሁ። 11አን​ተም ኤር​ም​ያስ ወደ ባቢ​ሎን ሀገር እስ​ክ​ት​ደ​ርስ ድረስ ከሕ​ዝቡ ጋራ ወደ ግብፅ ሂድ፤ ወደ ሀገ​ራ​ቸ​ውም እስ​ክ​መ​ል​ሳ​ቸው ድረስ ስታ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸው ኑር። 12ባሮ​ክን ግን በዚያ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተወው፤” ጌታም ይህን ሁሉ ነገር ለኤ​ር​ም​ያስ ነግ​ሮት ከኤ​ር​ም​ያስ ዘንድ ወደ ሰማይ አልፎ ወጣ።
13ባሮ​ክና ኤር​ም​ያ​ስም ወደ ቤተ መቅ​ደስ ገቡ፤ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ት​ንም ዕቃ ሁሉ ጌታ እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው ለም​ድር ሰጧት፤ ምድ​ርም ያን​ጊዜ ተቀ​ብላ ዋጠ​ችው። 14ሁለ​ቱም ሁሉ ተቀ​ም​ጠው አለ​ቀሱ፤ በማ​ግ​ሥ​ቱም በነጋ ጊዜ ኤር​ም​ያስ አቤ​ሜ​ሌ​ክን፥ “ሙዳ​ዩን ይዘህ ወደ አግ​ሪ​ጳስ የወ​ይን ቦታ በተ​ራ​ራው ጎዳና ሂድ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረድ​ኤት፥ ጌት​ነ​ቱም በአ​ንተ ራስ አድ​ሯ​ልና ለታ​መሙ ወገ​ኖች ጥቂት በለ​ስን አምጣ” ብሎ ላከው። 15እር​ሱም እን​ዳ​ዘ​ዘው ሄደ፤ በማ​ግ​ሥ​ቱም በነጋ ጊዜ የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሠራ​ዊት ከተ​ማ​ዪ​ቱን ከበ​ቧት፤ ታላ​ቁም መል​አክ መለ​ከ​ቱን ነፋ። 16እር​ሱም፥ “የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሠራ​ዊት፥ ግቡ፤ እነሆ፥ በሮቹ ይከ​ፈ​ቱ​ላ​ች​ኋል” አለ። 17ያን​ጊ​ዜም ንጉሡ ከሠ​ራ​ዊቱ ጋር ገብቶ ሕዝ​ቡን ሁሉ ማረከ።
18ያን​ጊ​ዜም ኤር​ም​ያስ የቤተ መቅ​ደ​ሱን መክ​ፈቻ ይዞ ከከ​ተማ ወደ ውጭ ወጣ። 19ይህ​ንም መክ​ፈቻ “ፀሐይ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት መክ​ፈቻ ተቀ​በል” ብሎ በፀ​ሐይ ፊት ጣለው። 20“ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን እኛ እየ​ተ​ከ​ባ​ከ​ብ​ናት ስለ ተገ​ኘን ከተ​ወ​ለ​ድን ጀምሮ እር​ሱን ለመ​ጠ​በቅ አይ​ገ​ባ​ን​ምና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ር​ሱን ነገር እስ​ከ​ሚ​ነ​ግ​ርህ እስከ ብዙ ዘመን ድረስ ጠብ​ቀው” አለው። 21ኤር​ም​ያ​ስም ለወ​ገ​ኖቹ ሲያ​ለ​ቅስ እያ​ዳፉ አወ​ጡት፤ ከሕ​ዝ​ቡም ጋር እስከ ባቢ​ሎን ድረስ ወሰ​ዱት። 22ባሮክ ግን አመድ ዘግኖ በራሱ ላይ ነሰ​ነሰ፤ ተቀ​ም​ጦም አለ​ቀሰ፤ ይህ​ንም ሙሾ አሞሸ። እን​ዲ​ህም አለ፦
23“ስለ ተወ​ደደ ስለ ሕዝቡ ኀጢ​አት ነው እንጂ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ስለ ምን ጠፋች? 24ኃጥ​ኣን እን​ዳ​ይ​ታ​በዩ፥ የአ​ም​ላ​ክ​ንም ከተማ በኀ​ይ​ላ​ችን መያዝ ተቻ​ለን እን​ዳ​ይሉ በሕ​ዝቡ ኀጢ​አ​ትና በእኛ ኀጢ​አት በጠ​ላ​ቶ​ችዋ እጅ ወደ​ቀች እንጂ በእ​ነ​ርሱ ኀይል አይ​ደ​ለም። 25በእኛ ኀጢ​አት ለእ​ና​ንተ ተሰ​ጠ​ቻ​ችሁ እንጂ ይቺን ከተማ መያዝ የተ​ቻ​ላ​ችሁ በእ​ና​ንተ ጽናት አይ​ደ​ለም። 26አም​ላ​ካ​ች​ንም ያዝ​ን​ል​ናል፤ ወደ ሀገ​ራ​ች​ንም ይመ​ል​ሰ​ናል፤ ለእ​ና​ንተ ግን ድኅ​ነት የላ​ች​ሁም። 27ከዚህ ዓለም ተለ​ይ​ተው ሄደ​ዋ​ልና፥ የዚ​ች​ንም ከተማ ጥፋት አላ​ዩ​ምና አባ​ቶ​ቻ​ችን አብ​ር​ሃ​ምና ይስ​ሐቅ ያዕ​ቆ​ብም ብፁ​ዓን ናቸው።”
28ይህ​ንም ከተ​ና​ገረ በኋላ እያ​ለ​ቀሰ ወጣ፤ “ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ስለ አንቺ ኀዘ​ንን አዝ​ና​ለሁ” አለ። 29ከከ​ተ​ማ​ውም ወጥቶ በመ​ቃ​ብር ቤት አደረ፤ መላ​እ​ክ​ትም እየ​መጡ ሁሉን ይነ​ግ​ሩት ነበር።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ