ተረፈ ባሮክ 2
2
1ያንጊዜም ኤርምያስና ባሮክ፥ “የዚህ ነገር ምልክት በእውነት እንደ ተገኘ ዛሬ ዐወቅን” ብለው አለቀሱ። 2ኤርምያስም፥ “እግዚአብሔርን አንዲት ነገርን እስክለምነው ድረስ ከተማዋን ሁሉ እንዳታጠፉ እለምናችኋለሁ” ብሎ መላእክትን ማለዳቸው። 3ጌታም፥ “ከወዳጄ ከኤርምያስ ጋራ እስክነጋገር ድረስ ከተማዪቱን አታጥፉ” ብሎ ለመላእክት ነገራቸው።
4ኤርምያስም ያንጊዜ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እለምንሃለሁ፤ ከአንተ ጋር እናገር ዘንድ እዘዘኝ” ብሎ ተናገረ፤ ጌታም፥ “ወዳጄ ኤርምያስ ሆይ፥ የምትወድደውን ተናገር” አለው። 5ኤርምያስም እንዲህ አለው፥ “አቤቱ ጌታዬ፥ ይቺን ከተማ በጠላትዋ እጅ አሳልፈህ እንደምትሰጣት የባቢሎንም ሕዝብ እንደሚይዟት እነሆ፥ ዛሬ ዐወቅሁ። 6ተሰውረን ስለምናገለግልባቸው ንዋያተ ቅድሳት ምን አደርግ ዘንድ ትወድዳለህ? በላያቸውስ ምን አደርግ ዘንድ ትወድዳለህ?” 7ጌታም አለው፥ “እነርሱን ወስደህ ለምድር አደራ ስጣት፤ አንቺ ምድር በውኆች ላይ የፈጠረሽ፥ በሰባቱም ማኅተም ያተመሽ የፈጣሪሽ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተሽ ጌጥሽን ተቀበዪ፤ ተወዳጁም እስኪመጣ ድረስ ገንዘብሽን ጠብቂ በላት።” 8ኤርምያስም እንዲህ ሲል ተናገረ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እለምንሃለሁ፤ ሕዝቡን ብዙ ዘመን ለጠበቃቸው፥ እኔን ባሪያህ ኤርምያስንም ከሀገሩ ሰው ሁሉ ይልቅ ለጠበቀኝ ለኢትዮጵያዊው ለአቤሜሌክ የማደርገውን ግለጥልኝ። 9እርሱ ከረግረግ ጕድጓድ አወጣኝ፤ እንዳያዝን የከተማዋን ጥፋት ያይ ዘንድ አልወድለትም።”
10ጌታም ለኤርምያስ እንዲህ አለው፥ “ወደ አግሪጳስ ወይን ቦታ በዚህ ተራራ ጎዳና አቤሜሌክን ላከው፤ ሕዝቡን ወደ ሀገራቸው እስክመልሳቸው ድረስ እኔ እሰውረዋለሁ። 11አንተም ኤርምያስ ወደ ባቢሎን ሀገር እስክትደርስ ድረስ ከሕዝቡ ጋራ ወደ ግብፅ ሂድ፤ ወደ ሀገራቸውም እስክመልሳቸው ድረስ ስታስተምራቸው ኑር። 12ባሮክን ግን በዚያ በኢየሩሳሌም ተወው፤” ጌታም ይህን ሁሉ ነገር ለኤርምያስ ነግሮት ከኤርምያስ ዘንድ ወደ ሰማይ አልፎ ወጣ።
13ባሮክና ኤርምያስም ወደ ቤተ መቅደስ ገቡ፤ የሚያገለግሉበትንም ዕቃ ሁሉ ጌታ እንዳዘዛቸው ለምድር ሰጧት፤ ምድርም ያንጊዜ ተቀብላ ዋጠችው። 14ሁለቱም ሁሉ ተቀምጠው አለቀሱ፤ በማግሥቱም በነጋ ጊዜ ኤርምያስ አቤሜሌክን፥ “ሙዳዩን ይዘህ ወደ አግሪጳስ የወይን ቦታ በተራራው ጎዳና ሂድ፤ የእግዚአብሔር ረድኤት፥ ጌትነቱም በአንተ ራስ አድሯልና ለታመሙ ወገኖች ጥቂት በለስን አምጣ” ብሎ ላከው። 15እርሱም እንዳዘዘው ሄደ፤ በማግሥቱም በነጋ ጊዜ የከለዳውያን ሠራዊት ከተማዪቱን ከበቧት፤ ታላቁም መልአክ መለከቱን ነፋ። 16እርሱም፥ “የከለዳውያን ሠራዊት፥ ግቡ፤ እነሆ፥ በሮቹ ይከፈቱላችኋል” አለ። 17ያንጊዜም ንጉሡ ከሠራዊቱ ጋር ገብቶ ሕዝቡን ሁሉ ማረከ።
18ያንጊዜም ኤርምያስ የቤተ መቅደሱን መክፈቻ ይዞ ከከተማ ወደ ውጭ ወጣ። 19ይህንም መክፈቻ “ፀሐይ፥ የእግዚአብሔርን ቤት መክፈቻ ተቀበል” ብሎ በፀሐይ ፊት ጣለው። 20“ኀጢአታችንን እኛ እየተከባከብናት ስለ ተገኘን ከተወለድን ጀምሮ እርሱን ለመጠበቅ አይገባንምና እግዚአብሔር የእርሱን ነገር እስከሚነግርህ እስከ ብዙ ዘመን ድረስ ጠብቀው” አለው። 21ኤርምያስም ለወገኖቹ ሲያለቅስ እያዳፉ አወጡት፤ ከሕዝቡም ጋር እስከ ባቢሎን ድረስ ወሰዱት። 22ባሮክ ግን አመድ ዘግኖ በራሱ ላይ ነሰነሰ፤ ተቀምጦም አለቀሰ፤ ይህንም ሙሾ አሞሸ። እንዲህም አለ፦
23“ስለ ተወደደ ስለ ሕዝቡ ኀጢአት ነው እንጂ ኢየሩሳሌም ስለ ምን ጠፋች? 24ኃጥኣን እንዳይታበዩ፥ የአምላክንም ከተማ በኀይላችን መያዝ ተቻለን እንዳይሉ በሕዝቡ ኀጢአትና በእኛ ኀጢአት በጠላቶችዋ እጅ ወደቀች እንጂ በእነርሱ ኀይል አይደለም። 25በእኛ ኀጢአት ለእናንተ ተሰጠቻችሁ እንጂ ይቺን ከተማ መያዝ የተቻላችሁ በእናንተ ጽናት አይደለም። 26አምላካችንም ያዝንልናል፤ ወደ ሀገራችንም ይመልሰናል፤ ለእናንተ ግን ድኅነት የላችሁም። 27ከዚህ ዓለም ተለይተው ሄደዋልና፥ የዚችንም ከተማ ጥፋት አላዩምና አባቶቻችን አብርሃምና ይስሐቅ ያዕቆብም ብፁዓን ናቸው።”
28ይህንም ከተናገረ በኋላ እያለቀሰ ወጣ፤ “ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ስለ አንቺ ኀዘንን አዝናለሁ” አለ። 29ከከተማውም ወጥቶ በመቃብር ቤት አደረ፤ መላእክትም እየመጡ ሁሉን ይነግሩት ነበር።
Currently Selected:
ተረፈ ባሮክ 2: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ