የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 17

17
ስለ ጳው​ሎ​ስና ስለ አይ​ሁድ ክር​ክር
1አን​ፊ​ጶ​ልና አጶ​ሎ​ንያ ወደ​ሚ​ባሉ ሀገ​ሮ​ችም ሄዱ፤ የአ​ይ​ሁድ ምኵ​ራብ ወደ አለ​በት ወደ ተሰ​ሎ​ን​ቄም ደረሱ። 2ጳው​ሎ​ስም እንደ አስ​ለ​መ​ደው ወደ እነ​ርሱ ገብቶ ሦስት ሳም​ንት ከመ​ጻ​ሕ​ፍት እየ​ጠ​ቀሰ ሲከ​ራ​ከ​ራ​ቸው ሰነ​በተ። 3ክር​ስ​ቶስ እን​ዲ​ሞት ከሙ​ታ​ንም ተለ​ይቶ እን​ዲ​ነሣ፥ እየ​ተ​ረ​ጐ​መና እየ​አ​ስ​ተ​ማ​ራ​ቸው፥ “ይህ እኔ የነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ ኢየ​ሱስ እርሱ ክር​ስ​ቶስ ነው” ይል ነበር። 4ከእ​ነ​ር​ሱና ከደ​ጋ​ጎች አረ​ማ​ው​ያ​ንም ብዙ ሰዎች፥ ከታ​ላ​ላ​ቆች ሴቶ​ችም ጥቂ​ቶች ያይ​ደሉ አም​ነው ከጳ​ው​ሎ​ስና ከሲ​ላስ ጋር ሆኑ። 5የማ​ያ​ምኑ አይ​ሁድ ግን ቀኑ​ባ​ቸው፤ ከገ​በ​ያም ክፉ​ዎች ሰዎ​ችን አም​ጥ​ተው፥ ሰዎ​ች​ንም ሰብ​ስ​በው ሀገ​ሪ​ቱን አወ​ኳት፤ ፈለ​ጓ​ቸ​ውም፤ የኢ​ያ​ሶ​ንን ቤትም በረ​በሩ፤ ወደ ሕዝ​ቡም ሊያ​ወ​ጧ​ቸው ሽተው ነበር። 6በአ​ጧ​ቸ​ውም ጊዜ ኢያ​ሶ​ንን ጐተ​ቱት፤ በዚ​ያም የነ​በ​ሩ​ትን ጓደ​ኞች ጭምር ወደ ሹሞቹ ወሰ​ዱ​አ​ቸው፤ እየ​ጮ​ኹም እን​ዲህ ይሉ ነበር፥ “ዓለ​ምን የሚ​ያ​ው​ኳት እነ​ዚህ ናቸው፤ ወደ​ዚ​ህም መጥ​ተ​ዋል። 7ይህ ኢያ​ሶ​ንም ተቀ​በ​ላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም በቄ​ሣር ላይ የወ​ን​ጀል ሥራ ይሠ​ራሉ፤ ሌላ ሕግ​ንም ያስ​ተ​ም​ራሉ፤ ኢየ​ሱ​ስም ሌላ ንጉሥ ነው” ይላሉ። 8ሕዝ​ቡና የከ​ተ​ማው ሹሞ​ችም ይህን በሰሙ ጊዜ ታወኩ። 9ከኢ​ያ​ሶ​ንና ከጓ​ደ​ኞ​ቹም ዋስ ተቀ​ብ​ለው ለቀ​ቁ​አ​ቸው።
10ወን​ድ​ሞች ግን ጳው​ሎ​ስ​ንና ሲላ​ስን በሌ​ሊት ወደ ቤርያ ሸኙ​አ​ቸው፤ ወደ​ዚ​ያም በደ​ረሱ ጊዜ ወደ አይ​ሁድ ምኵ​ራብ ገቡ። 11በተ​ሰ​ሎ​ንቄ ካሉ​ትም እነ​ርሱ ይሻ​ላሉ፤ በፍ​ጹም ደስታ ቃላ​ቸ​ውን ተቀ​ብ​ለ​ዋ​ልና፤ ነገ​ሩም እንደ አስ​ተ​ማ​ሩ​አ​ቸው እንደ ሆነ ለመ​ረ​ዳት ዘወ​ትር መጻ​ሕ​ፍ​ትን ይመ​ረ​ምሩ ነበር። 12ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ያመኑ ብዙ​ዎች ነበሩ፤ ከአ​ረ​ማ​ው​ያን ወገን የሆኑ ብዙ ደጋግ ሴቶ​ችም ነበሩ፤ ወን​ዶ​ችም ብዙ​ዎች ነበሩ። 13በተ​ሰ​ሎ​ንቄ የነ​በሩ አይ​ሁድ ግን ጳው​ሎስ በቤ​ርያ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እንደ አስ​ተ​ማረ ባወቁ ጊዜ፥ ወደ​ዚያ መጥ​ተው ሕዝ​ቡን አወ​ኩ​አ​ቸው። 14ያን​ጊ​ዜም ወን​ድ​ሞች ጳው​ሎ​ስን ሸኝ​ተው ወደ ባሕር አደ​ረ​ሱት፤ ሲላ​ስና ጢሞ​ቴ​ዎስ ግን በዚ​ያው ቀሩ። 15ጳው​ሎ​ስን የሸ​ኙት ሰዎ​ችም እስከ አቴና ከተማ ድረስ አብ​ረ​ውት መጥ​ተው ነበ​ርና ፈጥ​ነው ይከ​ተ​ሉት ዘንድ ወደ ሲላ​ስና ወደ ጢሞ​ቴ​ዎስ ላካ​ቸው፤ ተመ​ል​ሰ​ውም ሄዱ።
ስለ ጳው​ሎስ መታ​ወክ
16ጳው​ሎ​ስም በአ​ቴና ሆኖ ሲጠ​ብ​ቃ​ቸው ከተ​ማው ሁሉ ጣዖት ሲያ​መ​ልኩ ባየ ጊዜ ልቡ​ናው ተበ​ሳጨ። 17ስለ​ዚ​ህም በም​ኵ​ራብ አይ​ሁ​ድ​ንና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ሩ​ትን፥ ሁል​ጊ​ዜም በገ​በያ የሚ​ያ​ገ​ኛ​ቸ​ውን ሁሉ ይከ​ራ​ከ​ራ​ቸው ነበር። 18የኤ​ፌ​ቆ​ሮ​ስን ትም​ህ​ርት ከተ​ማሩ ፈላ​ስ​ፋ​ዎች መካ​ከ​ልና ረዋ​ቅ​ያ​ው​ያን ከሚ​ባ​ሉት ወገን የሆኑ ሌሎች ፈላ​ስ​ፎ​ችም የተ​ከ​ራ​ከ​ሩት ነበሩ፤ እኩ​ሌ​ቶ​ችም፥ “ይህ ለፍ​ላፊ ምን ሊና​ገር ይፈ​ል​ጋል?” ይሉ ነበር፤ ሌሎ​ችም፥ “ስለ ኢየ​ሱስ ከሙ​ታን ስለ መነ​ሣ​ቱም ሰብ​ኮ​ላ​ቸ​ዋ​ልና የአ​ዲስ አም​ላክ#ግሪኩ “የአ​ዲ​ሶች አማ​ል​ክት ...” ይላል። ትም​ህ​ር​ትን ያስ​ተ​ም​ራል” አሉ። 19ይዘ​ውም አር​ዮ​ስ​ፋ​ጎስ ወደ​ሚ​ባል ሸንጎ ወሰ​ዱት፤ እን​ዲ​ህም አሉት፥ “ይህን የም​ታ​ስ​ተ​ም​ረ​ውን አዲስ ትም​ህ​ርት እና​ውቅ ዘንድ ይቻ​ለ​ና​ልን? እስቲ ንገ​ረን? 20በጆ​ሮ​አ​ችን እን​ግዳ ነገር ታሰ​ማ​ና​ለ​ህና እኛም ይህ ነገር ምን እንደ ሆነ ልን​ረዳ እን​ወ​ዳ​ለን።” 21የአ​ቴና ሰዎ​ችና በዚ​ያም የነ​በሩ እን​ግ​ዶች ሁሉ አዲስ ነገ​ርን ከመ​ና​ገ​ርና ከመ​ስ​ማት በቀር ሌላ ዐሳብ አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም።
ጳው​ሎስ በፍ​ርድ ሸንጎ ውስጥ ስለ አደ​ረ​ገው ንግ​ግር
22ጳው​ሎ​ስም በአ​ር​ዮ​ስ​ፋ​ጎስ ውስጥ ቆሞ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የአ​ቴና ሰዎች! በሥ​ራ​ችሁ ሁሉ አማ​ል​ክ​ትን ማም​ለክ እን​ደ​ም​ታ​በዙ አያ​ች​ኋ​ለሁ። 23በዚ​ህም ሳልፍ ‘ለማ​ይ​ታ​ወቅ አም​ላክ’ የሚል ጽሕ​ፈት ያለ​በ​ትን የም​ታ​መ​ል​ኩ​በ​ትን መሠ​ዊ​ያ​ች​ሁን አየሁ፤ እነሆ፥ እኔ ይህን ሳታ​ውቁ የም​ታ​መ​ል​ኩ​ትን እገ​ል​ጽ​ላ​ች​ኋ​ለሁ። 24ዓለ​ሙ​ንና በእ​ር​ሱም ያለ​ውን ሁሉ የፈ​ጠረ አም​ላክ እርሱ የሰ​ማ​ይና የም​ድር ጌታ ነውና እጅ በሠ​ራው መቅ​ደስ አይ​ኖ​ርም። 25#1ነገ. 8፥27፤ ኢሳ. 42፥5፤ የሐዋ. 8፥40። እር​ሱም ሕይ​ወ​ት​ንና እስ​ት​ን​ፋ​ስን፥ ሌላ​ው​ንም ነገር ሁሉ ለሁሉ ይሰ​ጣ​ልና እንደ ችግ​ረኛ የሰው እጅ አያ​ገ​ለ​ግ​ለ​ውም። 26እር​ሱም በም​ድር ሁሉ ላይ ይኖሩ ዘንድ ሰዎ​ችን ሁሉ ከአ​ንድ ሰው ፈጠረ፤ ይኖ​ሩ​ባ​ትም ዘንድ ዘመ​ን​ንና ቦታን ወስኖ ሠራ​ላ​ቸው። 27ምና​ል​ባት ያገ​ኙት እንደ ሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈ​ል​ጉት ዘንድ፤ ነገር ግን ከሁ​ላ​ችን የራቀ አይ​ደ​ለም። 28እኛ በእ​ርሱ ሕይ​ወ​ትን እና​ገ​ኛ​ለን፤ በእ​ር​ሱም እን​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሳ​ለን፤ በእ​ር​ሱም ጸን​ተን እን​ኖ​ራ​ለን፤ ከመ​ካ​ከ​ላ​ች​ሁም፦ ‘እኛ ዘመ​ዶቹ ነን’ የሚሉ ፈላ​ስ​ፎች አሉ። 29እን​ግ​ዲህ እኛ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘመ​ዶች ከሆን በሰው ዕው​ቀ​ትና ብል​ሀት በተ​ቀ​ረጸ በድ​ን​ጋ​ይና በብር፥ በወ​ር​ቅም አም​ላ​ክ​ነ​ቱን ልን​መ​ስ​ለው አይ​ገ​ባም። 30የቀ​ድ​ሞ​ው​ንስ ያለ ማወቅ ዘመን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሳ​ል​ፎ​ታል፤ ዛሬ ግን በመ​ላው ዓለም ንስሓ እን​ዲ​ገቡ ሰውን ሁሉ አዝ​ዞ​አል። 31በመ​ረ​ጠው ሰው እጅ በዓ​ለም በእ​ው​ነት የሚ​ፈ​ር​ድ​ባ​ትን ቀን ወስ​ኖ​አ​ልና፤ እር​ሱን ከሙ​ታን ለይቶ በማ​ስ​ነ​ሣ​ቱም ብዙ​ዎ​ችን ወደ ሃይ​ማ​ኖት መል​ሶ​አ​ልና።”
32የሙ​ታ​ን​ንም ትን​ሣኤ በሰሙ ጊዜ እኩ​ሌ​ቶቹ አፌ​ዙ​በት፤ ሌሎ​ችም፥ “ስለ​ዚህ ነገር በሌላ ቀን እና​ዳ​ም​ጥ​ሃ​ለን” አሉት። 33ጳው​ሎ​ስም ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ወጥቶ ሄደ። 34አም​ነው የተ​ከ​ተ​ሉት ሰዎ​ችም ነበሩ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አንዱ ከአ​ር​ዮ​ስ​ፋ​ጎስ ባለ​ሥ​ል​ጣ​ኖች ወገን የሚ​ሆን ዲዮ​ና​ስ​ዮስ ነበር፤ ደማ​ሪስ የም​ት​ባል ሴትም ነበ​ረች፤ ሌሎ​ችም አብ​ረ​ዋ​ቸው ነበሩ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ