የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 21

21
የጳ​ው​ሎስ ጕዞ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም
1ከእ​ነ​ር​ሱም ከተ​ለ​የን በኋላ እኛ በመ​ር​ከብ ተሳ​ፍ​ረን፥ መን​ገ​ዳ​ች​ን​ንም አቅ​ን​ተን ወደ ቆስ መጣን፤ በበ​ነ​ጋ​ውም ወደ ሮዶስ፥ ከዚ​ያም ወደ ጳጥራ ገባን። 2ወደ ፊን​ቄም የሚ​ያ​ልፍ መር​ከብ አግ​ኝ​ተን በዚያ ላይ ተሳ​ፍ​ረን ሄድን። 3ቆጵ​ሮ​ስ​ንም አየ​ናት፤ በስተ ግራ​ች​ንም ትተ​ናት ወደ ሶርያ ሄድን፤ ወደ ጢሮ​ስም ወረ​ድን፤ በመ​ር​ከብ ያለ​ውን ጭነት ሁሉ በዚያ ያራ​ግፉ ነበ​ርና። 4በዚ​ያም ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትን አገ​ኘ​ንና በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ሰባት ቀን ተቀ​መ​ጥን፤ እነ​ር​ሱም በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ተገ​ል​ጾ​ላ​ቸው ጳው​ሎ​ስን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ዳ​ይ​ወጣ ነገ​ሩት። 5ከዚ​ህም በኋላ ለመ​ሄድ ወጣን፤ ሁሉም ከሚ​ስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ከል​ጆ​ቻ​ቸው ጋር እስከ ከተ​ማው ውጭ ሸኙን፤ በባ​ሕ​ሩም ዳር ተን​በ​ር​ክ​ከን ጸለ​ይን። 6እርስ በር​ሳ​ች​ንም ተሳ​ስ​መን ተሰ​ነ​ባ​በ​ትን፤ ከዚ​ህም በኋላ ወደ መር​ከብ ወጣን፤ እነ​ር​ሱም ወደ ቤታ​ቸው ተመ​ለሱ።
7እኛም ከጢ​ሮስ ወጥ​ተን አካ#በግ​ሪኩ “ጵቶ​ሎ​ማ​ይስ” ይላል። ወደ​ም​ት​ባል ሀገር መጣን፤ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ን​ንም አግ​ኝ​ተን ሰላም አል​ና​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ዘንድ አንድ ቀን አደ​ርን። 8#የሐዋ. 6፥5፤ 8፥5። በማ​ግ​ሥ​ቱም ወጥ​ተን ወደ ቂሳ​ርያ ሄድን፤ ወደ ወን​ጌ​ላ​ዊው ወደ ፊል​ጶስ ቤትም ገባን፤ እር​ሱም ከሰ​ባቱ ወን​ድ​ሞች ዲያ​ቆ​ናት አንዱ ነው። 9ለእ​ር​ሱም ትን​ቢት የሚ​ና​ገሩ አራት ደና​ግል ሴቶች ልጆች ነበ​ሩት። 10#11፥28። በእ​ር​ሱም ዘንድ ብዙ ቀን ኖርን፤ ከይ​ሁ​ዳም አጋ​ቦስ የሚ​ባል አንድ ነቢይ ወረደ። 11ወደ እኛም መጣና የጳ​ው​ሎ​ስን መታ​ጠ​ቂያ አን​ሥቶ እጁ​ንና እግ​ሩን በገዛ እጁ አስሮ እን​ዲህ አለ፥ “መን​ፈስ ቅዱስ እን​ዲህ ይላል፤ የዚ​ህን መታ​ጠ​ቂያ ጌታ አይ​ሁድ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ዲህ ያስ​ሩ​ታል፤ ለአ​ሕ​ዛ​ብም አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​ታል።” 12ይህ​ንም ሰም​ተን የሀ​ገ​ሪ​ቱን ሰዎች ይዘን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ዳ​ይ​ወጣ ጳው​ሎ​ስን ማለ​ድ​ነው። 13ጳው​ሎስ ግን መልሶ፥ “ለምን እን​ዲህ ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ? እያ​ለ​ቀ​ሳ​ችሁ ልቤን ትሰ​ብ​ሩ​ታ​ላ​ችሁ፤ እኔ እኮ ተስፋ የማ​ደ​ር​ገው መከ​ራ​ንና እግር ብረ​ትን ብቻ አይ​ደ​ለም፤ እኔ ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለመ​ሞ​ትም ቢሆን የቈ​ረ​ጥሁ ነኝ” አለ። 14እንቢ ባለ ጊዜም ዝም አልን፤ እኛም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፈ​ቀ​ደው ይሁን ብለን ተው​ነው። 15ከእ​ነ​ዚ​ያም ቀኖች በኋላ ተዘ​ጋ​ጅ​ተን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጣን። 16ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም ከቂ​ሳ​ርያ አብ​ረ​ውን የመጡ ነበሩ፤ ሄደ​ንም ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዎቹ ደቀ መዛ​ሙ​ርት ወገን ከሆ​ነው በቆ​ጵ​ሮስ በሚ​ኖ​ረው በም​ና​ሶን ቤት አደ​ርን።
17ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በደ​ረ​ስን ጊዜም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን በደ​ስታ ተቀ​በ​ሉን። 18በማ​ግ​ሥ​ቱም ጳው​ሎስ ከእኛ ጋር ወደ ያዕ​ቆብ ገባ፤ ቀሳ​ው​ስ​ትም ሁሉ በዚያ ነበሩ። 19ጳው​ሎ​ስም ሰላ​ምታ ካቀ​ረ​በ​ላ​ቸው በኋላ በእ​ርሱ ሐዋ​ር​ያ​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ሕ​ዛብ ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ ነገ​ራ​ቸው። 20እነ​ር​ሱም ሰም​ተው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገኑ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ወን​ድ​ማ​ችን ሆይ፥ ከአ​ይ​ሁድ መካ​ከል ያመ​ኑት ስንት አእ​ላ​ፋት እንደ ሆኑ ታያ​ለ​ህን? ሁሉም ለኦ​ሪት የሚ​ቀኑ ናቸው። 21ነገር ግን የማ​ይ​ሆ​ነ​ውን እን​ደ​ም​ታ​ስ​ተ​ምር፥ የሙ​ሴ​ንም ሕግ እን​ደ​ም​ታ​ስ​ተ​ዋ​ቸው፥ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ያሉ ያመኑ አይ​ሁ​ድ​ንም ልጆ​ቻ​ቸ​ውን እን​ዳ​ይ​ገ​ርዙ፥ የኦ​ሪ​ት​ንም ሕግ እን​ዳ​ይ​ፈ​ጽሙ እን​ደ​ም​ት​ከ​ለ​ክ​ላ​ቸው ስለ አንተ ነግ​ረ​ዋ​ቸ​ዋል። 22አሁ​ንሳ ምን ይሁን? ሕዝቡ ወደ​ዚህ እንደ መጣህ ይሰ​ሙና ይሰ​በ​ሰቡ ይሆ​ናል። 23ስለ​ዚ​ህም ይህን የም​ል​ህን አድ​ርግ፦ ብፅ​ዐት ያላ​ቸው አራት ሰዎች በእኛ ዘንድ አሉ። 24#ዘኍ​. 6፥13-21። ይዘ​ሃ​ቸው ሂድ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ራስ​ህን አንጻ፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም እን​ዲ​ላጩ ስለ እነ​ርሱ ገን​ዘብ ክፈ​ል​ላ​ቸው፤ የሚ​ያ​ሙ​ህም በሐ​ሰት እንደ ሆነ፥ አን​ተም የኦ​ሪ​ትን ሕግ እን​ደ​ም​ት​ጠ​ብቅ ሁሉም ያው​ቃሉ። 25#የሐዋ. 15፥29። ስለ​ሚ​አ​ም​ኑት አሕ​ዛብ ግን እርም ከሆ​ነ​ውና ለጣ​ዖ​ታት ከሚ​ሠ​ዉት፥ ከዝ​ሙት፥ ሞቶ የተ​ገ​ኘ​ው​ንና ደምን ከመ​ብ​ላት እን​ዲ​ከ​ለ​ከሉ እኛ አዝ​ዘ​ናል።” 26ያን​ጊ​ዜም ጳው​ሎስ ሰዎ​ችን ይዞ በማ​ግ​ሥቱ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነጻ። የመ​ን​ጻ​ታ​ቸ​ው​ንም ወራት መድ​ረ​ሱን ከነ​ገ​ራ​ቸው በኋላ ሁሉም እየ​አ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርቡ ዘንድ ወደ ቤተ መቅ​ደስ ይዞ​አ​ቸው ገባ።
ጳው​ሎስ ስለ መከ​ሰሱ
27በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ከእ​ስያ የመጡ አይ​ሁድ ጳው​ሎ​ስን በመ​ቅ​ደስ አዩት፤ ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ በእ​ርሱ ላይ አነ​ሳ​ሥ​ተው ያዙት። 28እየ​ጮ​ሁም እን​ዲህ አሉ፥ “እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሆይ፥ ርዱን፤ በየ​ስ​ፍ​ራው ሕዝ​ባ​ች​ንን፥ ኦሪ​ት​ንም፥ ይህ​ንም ስፍራ የሚ​ቃ​ወም ትም​ህ​ርት ለሰው ሁሉ የሚ​ያ​ስ​ተ​ምር እነሆ፥ ይህ ሰው ነው፤ አሁ​ንም አረ​ማ​ው​ያ​ንን ወደ መቅ​ደስ አስ​ገባ፤ ቤተ መቅ​ደ​ስ​ንም አረ​ከሰ። 29#የሐዋ. 20፥4። የኤ​ፌ​ሶን ሀገር ሰው የሆነ ጥሮ​ፊ​ሞ​ስን ከጳ​ው​ሎስ ጋር በከ​ተማ አይ​ተ​ውት ነበ​ርና፤ ጳው​ሎ​ስም ወደ ቤተ መቅ​ደስ ያስ​ገ​ባው መስ​ሎ​አ​ቸው ነበ​ርና። 30ከተ​ማ​ውም ሁሉ ታወከ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ እየ​ሮጡ ሄደው ጳው​ሎ​ስን ጐት​ተው ከቤተ መቅ​ደስ አወ​ጡት፤ በሩ​ንም ሁሉ ዘጉ። 31ሊገ​ድ​ሉ​ትም ፈል​ገው ብዙ ደበ​ደ​ቡት፤ ወዲ​ያ​ውም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በመ​ላዋ እንደ ታወ​ከች የሚ​ገ​ልጥ መል​እ​ክት ወደ ሻለ​ቃው ደረ​ሰ​ለት። 32በዚያ ጊዜም ጭፍ​ሮ​ቹን ከአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸው ጋር ይዞ ወደ እነ​ርሱ ሄደ፤ እነ​ር​ሱም የሻ​ለ​ቃ​ውን ጭፍ​ሮች ባዩ ጊዜ ጳው​ሎ​ስን መም​ታ​ታ​ቸ​ውን ተዉ። 33የሻ​ለ​ቃ​ውም ቀረብ ብሎ ያዘው፤ በሁ​ለት ሰን​ሰ​ለ​ትም እን​ዲ​ታ​ሰር አዘዘ፤ “ምን​ድ​ነው? ምንስ አደ​ረገ?” ብሎም ጠየቀ። 34ሕዝ​ቡም እኩ​ሌ​ቶቹ እን​ዲህ ነው፤ እኩ​ሌ​ቶ​ቹም እን​ዲህ አይ​ደ​ለም እያሉ ይጮሁ ነበር፤ ሻለ​ቃ​ውም ሕዝቡ የሚ​ታ​ወ​ክ​በ​ትን ርግ​ጡን ማወቅ ተሣ​ነው፤ ወደ ወታ​ደ​ሮ​ቹም ሰፈር እን​ዲ​ወ​ስ​ዱት አዘዘ። 35ደረ​ጃ​ው​ንም በሚ​ወ​ጣ​በት ጊዜ ወታ​ደ​ሮች ተሸ​ክ​መው አወ​ጡት፤ ሰው ይጋፋ ነበ​ርና። 36ብዙ​ዎ​ችም ይከ​ተ​ሉት ነበር፤ ሕዝ​ቡም፥ “አስ​ወ​ግ​ዱት” እያሉ ይጮሁ ነበር።
ጳው​ሎስ ስለ ራሱ እንደ ተከ​ላ​ከለ
37ወደ ሰፈ​ርም በደ​ረሰ ጊዜ ጳው​ሎስ ሻለ​ቃ​ውን፥ “ላነ​ጋ​ግ​ርህ ትፈ​ቅ​ድ​ል​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ ሻለ​ቃ​ውም፥ “የጽ​ርዕ ቋንቋ ታው​ቃ​ለ​ህን?” አለው። 38“ምና​ል​ባት ከዚህ በፊት ወን​ጀል የሠ​ራ​ህና ከነ​ፍሰ ገዳ​ዮች አራት ሺህ ሰዎ​ችን ይዘህ ወደ ምድረ በዳ የወ​ጣህ ያ ግብ​ፃዊ አንተ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን?” አለው። 39ጳው​ሎ​ስም፥ “እኔስ አይ​ሁ​ዳዊ ሰው ነኝ፤ የተ​ወ​ለ​ድ​ሁ​ባ​ትም ሀገር ጠር​ሴስ የታ​ወ​ቀች የቂ​ል​ቅያ ከተማ ናት፤ ለሕ​ዝ​ቡም እን​ድ​ነ​ግ​ራ​ቸው ትፈ​ቅ​ድ​ልኝ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው። 40በፈ​ቀ​ደ​ለ​ትም ጊዜ ጳው​ሎስ በደ​ረ​ጃው ላይ ቆሞ እጁን ወደ ሕዝቡ ዘረጋ፤ እጅ​ግም ጸጥታ በሆነ ጊዜ ጳው​ሎስ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቋንቋ ተና​ገረ፤ እን​ዲ​ህም አለ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ