የሐዋርያት ሥራ 23
23
1ጳውሎስም በአደባባዩ ወደአሉት ሰዎች አተኵሮ ተመለከተና፥ “እናንተ ሰዎች ወንድሞች፥ እኔስ እስከዚች ቀን ድረስ በመልካም ሕሊና ሁሉ እግዚአብሔርን ሳገለግል ኑሬአለሁ” አላቸው። 2ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ግን ጳውሎስን አፉን እንዲመቱት በአጠገቡ ቆመው የነበሩትን#“በአጠገቡ ቆመው የነበሩትን” የሚለው በግእዙ የለም። አዘዘ። 3#ማቴ. 23፥27-28። ጳውሎስም መልሶ፥ “አንተ የተለሰነ ግድግዳ በሕግ ልትፈርድብኝ ተቀምጠህ ሳለ ያለ ሕግ እመታ ዘንድ ታዝዛለህን? እግዚአብሔር በቍጣው መቅሠፍት ይመታሃል” አለው። 4በአጠገቡ ቆመው የነበሩትም ጳውሎስን፥ “እግዚአብሔር የሾመውን ሊቀ ካህናት እንዴት ትሳደባለህ?” አሉት። 5#ዘፀ. 22፥28። ጳውሎስም፥ “ወንድሞች፥ ሊቀ ካህናት መሆኑን አላውቅም መጽሐፍ ‘በሕዝብህ አለቃ ላይ ክፉ አትናገር’ ይላልና” አላቸው።
6 #
የሐዋ. 26፥5፤ ፊል. 3፥5። ጳውሎስም እኩሌቶቹ ሰዱቃውያን እኩሌቶቹም ፈሪሳውያን እንደ ሆኑ ዐውቆ፥ “እኔ ፈሪሳዊ የፈሪሳዊ ልጅ ነኝ፤ ስለ ተስፋና ስለ ሙታን መነሣትም ይፈረድብኛል” ብሎ በአደባባይ ጮኸ። 7እንዲህም ባለ ጊዜ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ተጣሉ፤ ሸንጎውም ተከፋፈለ። 8#ማቴ. 22፥23፤ ማር. 12፥18፤ ሉቃ. 20፥27። ሰዱቃውያን፥ “ሙታን አይነሡም፤ መልአክም የለም፤ መንፈስም የለም” ይላሉና፤ ፈሪሳውያን ግን ይህ ሁሉ እንዳለ ያምናሉ። 9ታላቅ ውካታም ሆነ፤ ከፈሪሳውያንም ወገን የሆኑ ጸሐፍት ተነሥተው ይጣሉና ይከራከሩ ጀመሩ፤ “በዚህ ሰው ላይ ያገኘነው ክፉ ነገር የለም፤ መንፈስ#የግእዙ ዘር “መንፈስ ቅዱስ” ይላል። ወይም መልአክ ተናግሮት እንደ ሆነ እንጃ፥ ከእግዚአብሔር ጋር አንጣላ” አሉ። 10እጅግም በታወኩ ጊዜ ጳውሎስን እንዳይነጥቁት የሻለቃው ፈራና መጥተው ከመካከላቸው አውጥተው ወደ ወታደሮች ሰፈር ይወስዱት ዘንድ ወታደሮቹን አዘዘ። 11በሁለተኛዪቱም ሌሊት ጌታችን ለጳውሎስ ተገልጦ፥ “ጽና፥ በኢየሩሳሌም ምስክር እንደ ሆንኸኝ እንዲሁ በሮም ምስክር ትሆነኛለህ” አለው።
12በነጋም ጊዜ አይሁድ ተሰብስበው፥ ጳውሎስን እስኪገድሉት ድረስ እንዳይበሉና እንዳይጠጡ ተስማምተው ተማማሉ። 13ይህንም ለማድረግ የተማማሉት ሰዎች ከአርባ ይበዙ ነበር። 14እነርሱም ወደ ሊቃነ ካህናትና ወደ መምህራን ሄደው እንዲህ አሉአቸው፥ “ጳውሎስን እስክንገድለው ድረስ እነሆ፥ እንዳንበላና እንዳንጠጣ ፈጽመን ተማምለናል። 15አሁንም እናንተ ከሸንጎው ጋር ወደ ሻለቃው ሂዱና የምትመረምሩትና የምትጠይቁት አስመስላችሁ ጳውሎስን እንዲያመጣው ንገሩት፤ እኛ ግን ወደ እናንተ ከመድረሱ አስቀድሞ ልንገድለው ቈርጠናል።”
16የጳውሎስም የእኅቱ ልጅ ምክራቸውን በሰማ ጊዜ ሄዶ ወደ ወታደሮች ሰፈር ገባና ለጳውሎስ ነገረው። 17ጳውሎስም ከመቶ አለቆች አንዱን ጠርቶ፥ “የሚነግረው ነገር አለና ይህን ልጅ ወደ የሻለቃው አድርስልኝ” አለው። 18የመቶ አለቃውም ልጁን ይዞ ወደ የሻለቃው ወሰደውና፥ “የሚነግርህ ስለ አለው እስረኛው ጳውሎስ ይህን ልጅ ወደ አንተ እንዳደርሰው ለመነኝ” አለው። 19የሻለቃውም ልጁን በእጁ ይዞ ለብቻው ገለል አድርጎ፥ “የምትነግረኝ ነገሩ ምንድነው?” አለው። 20ልጁም እንዲህ አለው፥ “አይሁድ አጥብቀህ የምትመረምረው መስለህ ጳውሎስን ነገ ወደ ሸንጎ ታወርድላቸው ዘንድ ሊማልዱህ እንዲህ መክረዋል። 21አንተ ግን እሽ አትበላቸው፤ ሊገድሉት ሽምቀዋልና፤ እስኪገድሉትም ድረስ እንዳይበሉና እንዳይጠጡ እንዲህ የተማማሉ ሰዎች ከአርባ ይበዛሉ፤ አሁንም እስክትልክላቸው ይጠብቃሉ እንጂ እነርሱ ቈርጠዋል።” 22ከዚህም በኋላ፤ የሻለቃው፥ “ይህን ነገር ለእኔ መንገርህን ለማንም እንዳትገልጽ” ብሎ አሰናበተው።
23ከመቶ አለቆችም ሁለቱን ጠርቶ፥ “ከወታደሮች ሁለት መቶ ሰውና ሰባ ፈረሰኞች፥ ሁለት መቶ ቀስተኞችም ምረጡ፤ ከሌሊቱም በሦስት ሰዓት ወደ ቂሣርያ ይሂዱ” አላቸው። 24አህያም አምጥተው ጳውሎስን በዚያ አስቀምጠው ወደ ቂሣርያ አገረ ገዢ ወደ ፊልክስ እንዲወስዱት አዘዛቸው። 25እንዲህ የምትል ደብዳቤም ጻፈለት።
26“ከሉስዮስ ቀላውዴዎስ፥ ለክቡር አገረ ገዢ ፊልክስ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን። 27ይህን ሰው አይሁድ ያዙት፤ ሊገድሉትም ፈለጉ፤ ከወታደሮችም ጋር ተከላከልሁለት፥ የሮም ሰው መሆኑንም ዐውቄ አዳንሁት። 28በምን ምክንያትም እንደሚከሱት በደሉን አውቅ ዘንድ ወደ ሸንጎ አቅርቤ መረመርሁት። 29ስለ ሕጋቸውም ብቻ እንደ ከሰሱት ተረዳሁ፤ ለሞትና ለመታሰር የሚያበቃ ሌላ በደል ግን የለበትም። 30አይሁድም በዚህ ሰው ላይ በመሸመቅ የሚያደርጉትን በዐወቅሁ ጊዜ ወደ አንተ ላክሁት፤ ከሳሾቹንም ወደ አንተ እንዲመጡና በፊትህ እንዲፋረዱት አዝዣቸዋለሁ፤ ደኅና ሁን።”
31ጭፍሮችም እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ ጳውሎስንም በሌሊት ወሰዱት፤ ወደ አንቲጳጥሪስም አደረሱት። 32በማግሥቱም ከእርሱ ጋር ይሄዱ ዘንድ ፈረሰኞችን ትተው እነርሱ ወደ ሰፈር ተመለሱ። 33ከዚህም በኋላ ወደ ቂሣርያ ገቡ፤ ወደ አገረ ገዢውም ደረሱ፤ የተላከውንም ደብዳቤ ለአገረ ገዢው ሰጡት፤ ጳውሎስንም ወደ እርሱ አቀረቡት። 34ደብዳቤውንም ካነበበ በኋላ ከማን ግዛት እንደ ሆነ ጠየቀው። ከኪልቅያ የመጣ መሆኑንም ባወቀ ጊዜ፦ 35“እንኪያስ ከሳሾችህ ሲመጡ እንሰማሃለን” አለው፤ በሄሮድስም ግቢ እንዲጠብቁት አዘዘ።
Currently Selected:
የሐዋርያት ሥራ 23: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ