የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 24

24
ስለ ከሳ​ሾች መም​ጣት
1በአ​ም​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ሊቀ ካህ​ናቱ ሐና​ንያ ከመ​ም​ህ​ራ​ኑና ጠር​ጠ​ሉስ ከሚ​ባል አንድ ጠበቃ ጋር ወረደ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም በአ​ገረ ገዢው ዘንድ ከሰ​ሱት። 2ጳው​ሎ​ስም በቀ​ረበ ጊዜ ጠር​ጠ​ሉስ እን​ዲህ እያለ ይከ​ስ​ሰው ጀመረ፤ 3“ክቡር ፊል​ክስ ሆይ፥ በዘ​መ​ንህ ብዙ ሰላ​ምን አግ​ኝ​ተ​ናል፤ በጥ​በ​ብ​ህም በየ​ጊ​ዜው በየ​ሀ​ገሩ የሕ​ዝቡ ኑሮ የተ​ሻ​ሻለ ሆኖ​አል፤ ሥር​ዐ​ት​ህ​ንም በሁሉ ዘንድ ስት​መ​ሰ​ገን አግ​ኝ​ተ​ና​ታል። 4ነገር ግን ነገር እን​ዳ​ላ​በ​ዛ​ብህ በአ​ጭሩ ትሰ​ማኝ ዘንድ#ግሪኩ “በቸ​ር​ነ​ትህ” የሚል ይጨ​ም​ራል። እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ። 5ይህን ሰው ሲሳ​ደ​ብና ወን​ጀል ሲሠራ፥ አይ​ሁ​ድ​ንም ሁሉ በየ​ሀ​ገሩ ሲያ​ውክ፥ ናዝ​ራ​ው​ያን የተ​ባ​ሉት ወገ​ኖች የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ሩ​ት​ንም ክህ​ደት ሲያ​ስ​ተ​ምር#ግሪኩ “የመ​ና​ፍ​ቃን፥ የና​ዝ​ራ​ው​ያን መሪ ሆኖ አግ​ኝ​ተ​ነ​ዋል” ይላል። አግ​ኝ​ተ​ነ​ዋል። 6ቤተ መቅ​ደ​ስ​ንም ሊያ​ረ​ክስ ሲሞ​ክር ያዝ​ነው፤ እንደ ሕጋ​ች​ንም ልን​ፈ​ር​ድ​በት ፈል​ገን ነበር። 7ነገር ግን የሻ​ለ​ቃው ሉስ​ዮስ መጥቶ በብዙ ጭንቅ ከእ​ጃ​ችን ነጥቆ ወደ አንተ ላከው። 8ከሳ​ሾ​ቹ​ንም ወደ አንተ እን​ዲ​መጡ አዘ​ዛ​ቸው፤ የከ​ሰ​ስ​ን​በ​ት​ንም ነገር ሁሉ መር​ም​ረህ ከእ​ርሱ ልት​ረዳ ትች​ላ​ለህ።” 9አይ​ሁ​ድም፥ “እው​ነት ነው፤ እን​ዲሁ ነው” ብለው መለሱ።
የጳ​ው​ሎስ መል​እ​ክት
10ሀገረ ገዢ​ውም እን​ዲ​ና​ገር ጳው​ሎ​ስን ጠቀ​ሰው፤ ጳው​ሎ​ስም እን​ዲህ አለ፥ “ከብዙ ዘመን ጀምሮ የዚህ ሕዝብ አስ​ተ​ዳ​ዳሪ እንደ ሆንህ አው​ቃ​ለሁ፤ ጠባ​ያ​ቸ​ው​ንም ታው​ቃ​ለህ። አሁ​ንም ደስ እያ​ለኝ ክር​ክ​ሬን አቀ​ር​ባ​ለሁ። 11እሰ​ግድ ዘንድ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ከወ​ጣሁ ዐሥራ ሁለት ቀን እን​ደ​ማ​ይ​ሆን ልታ​ው​ቀው ትች​ላ​ለህ፤ 12በም​ኵ​ራብ ቢሆን፥ በቤተ መቅ​ደ​ስም ቢሆን፥ በከ​ተ​ማም ቢሆን ሕዝ​ብን ሳውክ፥ ከማ​ንም ጋር ስከ​ራ​ከር አላ​ገ​ኙ​ኝም። 13በሚ​ከ​ስ​ሱኝ ሁሉ በፊ​ትህ ማስ​ረጃ ማቅ​ረብ አይ​ች​ሉም። 14ነገር ግን ይህን አረ​ጋ​ግ​ጥ​ል​ሃ​ለሁ፤ እኔ በሕግ ያለ​ውን፥ በነ​ቢ​ያ​ትም የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ አምኜ እነ​ርሱ ክህ​ደት ብለው በሚ​ጠ​ሩት ትም​ህ​ርት የአ​ባ​ቶ​ችን አም​ላክ አመ​ል​ከ​ዋ​ለሁ። 15እነ​ር​ሱም ለጻ​ድ​ቃ​ንና ለኃ​ጥ​ኣን የሙ​ታን ትን​ሣኤ ይሆን ዘንድ እን​ደ​ሚ​ጠ​ብቁ ለእ​ኔም እን​ዲሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ተስፋ አለኝ። 16እን​ዲሁ እኔም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በሰው ፊት ሁል​ጊዜ የማ​ታ​ወ​ላ​ውል ሕሊና ትኖ​ረኝ ዘንድ እጋ​ደ​ላ​ለሁ። 17ከብዙ ዓመ​ታ​ትም በኋላ ለወ​ገ​ኖች ምጽ​ዋ​ት​ንና መሥ​ዋ​ዕ​ትን ላደ​ርግ መጣሁ። 18#የሐዋ. 21፥17-28። በዚ​ያም ጊዜ ከእ​ስያ የመጡ አይ​ሁድ ከሕ​ዝብ ጋር በመ​ከ​ራ​ከር፥ ወይም በፍ​ጅት ሳይ​ሆን በመ​ቅ​ደስ ስነጻ አገ​ኙኝ። 19አሁ​ንም በእኔ ላይ ነገር ከአ​ላ​ቸው ወደ አንተ ይም​ጡና ይክ​ሰ​ሱኝ። 20ወይም እኔ በሸ​ንጎ ቆሜ ሳለሁ ያገ​ኙ​ብኝ በደል እንደ አለ እነ​ዚህ ራሳ​ቸው ይመ​ስ​ክሩ። 21#የሐዋ. 23፥6። በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ቆሜ ከአ​ስ​ተ​ማ​ር​ኋት አን​ዲት ትም​ህ​ርት በቀር ያደ​ረ​ግ​ሁት ክፉ ነገር የለም። ‘ሙታን ይነ​ሣሉ’ በማ​ለ​ቴም ዛሬ በአ​ንተ ዘንድ በእኔ ይፈ​ረ​ድ​ብ​ኛል።”
22ፊል​ክስ ግን አይ​ሁድ ከጥ​ንት ጀምሮ የክ​ር​ስ​ቲ​ያ​ንን ወገ​ኖች ሕግና ትም​ህ​ርት እን​ደ​ሚ​ቃ​ወሙ ያውቅ ነበር፤#ግሪኩ “ፊል​ክስ ግን የት​ም​ህ​ር​ቱን ነገር አጥ​ብቆ ዐው​ቆ​አ​ልና” ይላል። ስለ​ዚ​ህም “እን​ኪ​ያስ የሺ አለ​ቃው ሉስ​ዮስ በመጣ ጊዜ ነገ​ራ​ች​ሁን እና​ውቅ ዘንድ እን​መ​ረ​ም​ራ​ለን” ብሎ ቀጠ​ራ​ቸው። 23የመቶ አለ​ቃ​ው​ንም ጳው​ሎ​ስን እን​ዲ​ጠ​ብ​ቀው፥ በሰፊ ቦታም እን​ዲ​ያ​ኖ​ረው፥ እን​ዳ​ያ​ጠ​ብ​በ​ትም፥ ሊያ​ገ​ለ​ግ​ሉት በመጡ ጊዜም ከወ​ዳ​ጆቹ አን​ዱን ስንኳ እን​ዳ​ይ​ከ​ለ​ክ​ል​በት አዘዘ።
24ከጥ​ቂት ቀንም በኋላ ፊል​ክስ ከአ​ይ​ሁ​ዳ​ዊት ሚስቱ ከድ​ሩ​ሲላ ጋር መጣ። ልኮም ጳው​ሎ​ስን አስ​ጠ​ራው፤ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስለ ማመ​ንም የሚ​ና​ገ​ረ​ውን ነገር ሰማው። 25እር​ሱም ስለ ጽድ​ቅና ስለ ንጽ​ሕና፥ ስለ​ሚ​መ​ጣ​ውም ኵነኔ በነ​ገ​ራ​ቸው ጊዜ በዚህ የተ​ነሣ ፊል​ክስ ፈራና ጳው​ሎ​ስን፥ “አሁ​ንስ ሂድ፤ በተ​መ​ቸ​ኝም ጊዜ ልኬ አስ​ጠ​ራ​ሃ​ለሁ” አለው። 26ፊል​ክ​ስም እን​ዲ​ፈ​ታው ጳው​ሎስ ገን​ዘብ የሚ​ሰ​ጠው መስ​ሎት ነበር፤ ስለ​ዚህ ዘወ​ትር ይጠ​ራ​ውና ያነ​ጋ​ግ​ረው ነበር። 27ሁለት ዓመ​ትም ካለፈ በኋላ፥ ፊል​ክስ ተሻ​ረና ጶር​ቅ​ዮስ ፊስ​ጦስ የሚ​ባል ሌላ ሀገረ ገዢ በእ​ርሱ ቦታ መጣ፤ ፊል​ክ​ስም በግ​ልጥ ለአ​ይ​ሁድ ሊያ​ዳላ ወደደ፤ ስለ​ዚ​ህም ጳው​ሎ​ስን እንደ ታሰረ ተወው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ