የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 27

27
ጳው​ሎስ ወደ ሮም በመ​ር​ከብ ስለ መሔዱ
1ከዚ​ህም በኋላ ፊስ​ጦስ ወደ ቄሣር ወደ ኢጣ​ልያ በመ​ር​ከብ እን​ሄድ ዘንድ ባዘዘ ጊዜ ጳው​ሎስ ከሌ​ሎች እስ​ረ​ኞች ጋር አብሮ የአ​ው​ግ​ስ​ጦስ ጭፍራ ለነ​በረ ዩል​ዮስ ለሚ​ባል የመቶ አለቃ ተሰጠ። 2በተ​ነ​ሣ​ንም ጊዜ ወደ እስያ በም​ት​ሄድ በአ​ድ​ራ​ማ​ጢስ መር​ከብ ተሳ​ፈ​ርን፤ የተ​ሰ​ሎ​ንቄ ሀገር ሰው የሚ​ሆን መቄ​ዶ​ን​ያ​ዊው አር​ስ​ጥ​ሮ​ኮ​ስም አብ​ሮን ሄደ። 3በማ​ግ​ሥ​ቱም ወደ ሲዶና ደረ​ስን፤ ዩል​ዮ​ስም ለጳ​ው​ሎስ አዘ​ነ​ለት፤ ወደ ወዳ​ጆቹ እን​ዲ​ሄ​ድና በእ​ነ​ርሱ ዘንድ እን​ዲ​ያ​ር​ፍም ፈቀ​ደ​ለት። 4ከዚ​ያም ወጥ​ተን ነፋስ ፊት ለፊት ነበ​ርና በቆ​ጵ​ሮስ በኩል ዐለ​ፍን። 5ወደ ኪል​ቅ​ያና ወደ ጵን​ፍ​ልያ ባሕ​ርም ገብ​ተን የሉ​ቅያ ክፍል ወደ​ም​ት​ሆ​ነው ወደ ሙራ ሄድን። 6በዚ​ያም የመቶ አለ​ቃው ወደ ኢጣ​ልያ የም​ት​ሄድ የእ​ስ​ክ​ን​ድ​ር​ያን መር​ከብ አገኘ፤ ወደ እር​ስ​ዋም አስ​ገ​ባን። 7ብዙ ቀንም እያ​ዘ​ገ​ምን ሄድን፤ በጭ​ን​ቅም ወደ ቀኒ​ዶስ አን​ጻር ደረ​ስን፤ ወደ​ዚ​ያም በቀ​ጥታ ለመ​ድ​ረስ ነፋስ ቢከ​ለ​ክ​ለን በቀ​ር​ጤስ በኩል በሰ​ል​ሙና ፊት ለፊት ዐለ​ፍን። 8ባጠ​ገ​ብ​ዋም በጭ​ንቅ ስና​ልፍ ላሲያ ለም​ት​ባ​ለው ከተማ አቅ​ራ​ቢያ ወደ ሆነ​ችው መል​ካም ወደብ ወደ​ም​ት​ባ​ለው ቦታ ደረ​ስን።
9በዚ​ያም ብዙ ቀን ቈየን፤ የአ​ይ​ሁ​ድም የጾም ወራት አልፎ ስለ ነበረ#ግእዙ “የአ​ይ​ሁድ ጾም እን​ዳ​ለፈ ክረ​ምቱ ስለ​ሚ​ገባ የባ​ሕር ላይ ጕዞ አስ​ቸ​ጋሪ ነበር” ይላል። በመ​ር​ከብ ለመ​ሄድ የሚ​ያ​ስ​ፈራ ነበ​ርና ጳው​ሎስ እን​ዲህ ብሎ መከ​ራ​ቸው። 10“እና​ንተ ሰዎች ሆይ፥ ስሙኝ፤ ጕዞ​አ​ችን በብዙ ጭን​ቀ​ትና በከ​ባድ ጥፋት ላይ ሆኖ አያ​ለሁ፤ ይህ​ንም የም​ለው ጥፋቱ በራ​ሳ​ች​ንም ሕይ​ወት እንጂ በጭ​ነ​ቱና በመ​ር​ከቡ ብቻ ስላ​ል​ሆነ ነው።” 11የመቶ አለ​ቃው ግን ለመ​ር​ከቡ ባለ​ቤ​ትና ለመ​ሪው ይታ​ዘዝ ነበር፤ የጳ​ው​ሎ​ስን ቃል ግን አይ​ቀ​በ​ልም ነበር። 12ያም ወደብ ክረ​ም​ቱን ሊከ​ር​ሙ​በት የማ​ይ​መች ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም ብዙ​ዎች ከዚያ ይወጡ ዘንድ ይቻ​ላ​ቸው እንደ ሆነ በቀኝ በኩል ወደ አለው ፊንቄ ወደ​ሚ​ባ​ለው ወደ ሁለ​ተ​ኛው የቀ​ር​ጤስ ወደብ ይደ​ርሱ ዘንድ ወደዱ።
ስለ ማዕ​በሉ ጽናት
13ልከኛ የአ​ዜብ ነፋ​ስም ነፈሰ፤ እነ​ር​ሱም እንደ ወደዱ የሚ​ደ​ርሱ መስ​ሎ​አ​ቸው ነበር፤ መል​ሕ​ቁ​ንም አነሡ፤ በቀ​ር​ጤ​ስም አጠ​ገብ ሄዱ። 14ከጥ​ቂት ጊዜ በኋ​ላም አው​ራ​ቂስ#“አው​ራ​ቂስ” በግ​እዝ “ሰል​ቢባ” ተብሎ ተተ​ር​ጕ​ሞ​አል። የሚ​ሉት ጽኑዕ ዓውሎ ነፋስ መጣ። 15መር​ከ​ባ​ች​ንም ተመ​ትታ ተነ​ጠ​ቀች፤ ቀዛ​ፊ​ዎ​ችም በነ​ፋሱ ፊት ለፊት መቆም አል​ተ​ቻ​ላ​ቸ​ው​ምና ተዉ​አት፤ ብቻ​ዋ​ንም ሄደች። 16ከዚ​ህም በኋላ ቄዳ#ግሪኩ “ቀላ​ሙዳ” ይላል። ወደ​ም​ት​ባል ደሴት እስ​ክ​ን​ገባ ድረስ ነፋሱ ነፈሰ፤ በጭ​ን​ቅም ታን​ኳ​ች​ንን ለመ​ግ​ታት ቻልን። 17ከዚህ በኋላ ተጋ​ግ​ዘን በገ​መድ አጠ​ና​ከ​ር​ናት፤ ከዚ​ህም ቀጥሎ ቀዛ​ፊ​ዎች ወደ ጥልቁ ባሕር እን​ዳ​ይ​ወ​ድቁ በፈሩ ጊዜ ሸራ​ውን አወ​ረዱ፤እን​ዲ​ሁም እን​ድ​ን​ሄድ አደ​ረ​ግን። 18በማ​ግ​ሥ​ቱም ማዕ​በል ጸና​ብን፤ ከጭ​ነ​ቱም ወደ ባሕር ጣልን። 19በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን በመ​ር​ከብ ያለ​ውን ሁሉ በእ​ጃ​ችን እያ​ነ​ሣን በባ​ሕር ላይ ጣልን። 20ብዙ ቀንም ፀሐ​ይ​ንና ጨረ​ቃን#“ጨረ​ቃን” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ከዋ​ክ​ብ​ት​ንም ሳናይ ማዕ​በሉ ጸና​ብን፤ ለመ​ዳ​ንም ተስፋ ቈር​ጠን ነበር።
ጳው​ሎስ በመ​ር​ከብ ላሉት ሰዎች ስለ ተና​ገ​ረው ነገር
21ከእ​ኛም መብል የበላ አል​ነ​በ​ረም። ጳው​ሎ​ስም ተነ​ሥቶ በመ​ካ​ከል ቆመና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ ሰዎች ሆይ፥ ቀድሞ ቃሌን ሰም​ታ​ች​ሁኝ ቢሆን ከቀ​ር​ጤ​ስም ባት​ወጡ ኖሮ ከዚህ ጕዳ​ትና መከራ በዳ​ና​ችሁ ነበር። 22አሁ​ንም እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ መር​ከ​ባ​ችን እንጂ ከመ​ካ​ከ​ላ​ችን አንድ ሰው ስንኳ አይ​ጠ​ፋ​ምና አት​ፍሩ። 23እኔ ለእ​ርሱ የም​ሆ​ንና የማ​መ​ል​ከው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የላ​ከው መል​አክ በዚች ሌሊት በአ​ጠ​ገቤ ቆሞ ነበ​ርና። 24እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፦ ‘ጳው​ሎስ ሆይ፥ አት​ፍራ፤ በቄ​ሣር ፊት ልት​ቆም ይገ​ባ​ሃል፤ ከአ​ን​ተም ጋር የሚ​ሄ​ዱ​ትን ሁሉ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ንተ ሰጥ​ቶ​ሃል።’ 25አሁ​ንም ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ እንደ ነገ​ረኝ እን​ደ​ሚ​ሆን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ና​ለ​ሁና። 26ነገር ግን ወደ አን​ዲት ደሴት እን​ደ​ር​ሳ​ለን።”
27በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛ​ውም ቀን በመ​ን​ፈቀ ሌሊት በአ​ድ​ርያ ባሕር ስን​ጓዝ ቀዛ​ፊ​ዎች ወደ የብሱ የደ​ረሱ መሰ​ላ​ቸው። 28መለ​ኪያ ገመድ ጣሉ፤ በሰው ቁመ​ትም ሃያ አገኙ፤ ከዚ​ያም ጥቂት ፈቀቅ ብለው ዳግ​መኛ ጣሉ፤ በሰው ቁመ​ትም ዐሥራ አም​ስት አገኙ። 29ድን​ጋ​ያማ በሆነ ቦታም እን​ዳ​ይ​ወ​ድቁ ፈሩ፤ ስለ​ዚ​ህም ከመ​ር​ከቡ በስ​ተ​ኋላ አራት መል​ሕቅ በባ​ሕሩ ላይ ጣሉ፤ ፈጥኖ እን​ዲ​ነ​ጋም ጸለዩ። 30ከዚህ በኋ​ላም ቀዛ​ፊ​ዎቹ ከመ​ር​ከብ ሊኮ​በ​ልሉ በወ​ደዱ ጊዜ ወደ ኋላ ሊመ​ለሱ ከም​ድር ላይ ሆነው መር​ከ​ባ​ቸ​ውን የሚ​ያ​ጠ​ና​ክሩ መስ​ለው ጀል​ባ​ቸ​ውን ወደ ባሕር አወ​ረዱ። 31ጳው​ሎ​ስም ይህን ባየ ጊዜ ለመቶ አለ​ቃ​ውና ለወ​ታ​ደ​ሮቹ፥ “እነ​ዚህ ቀዛ​ፊ​ዎች በመ​ር​ከብ ውስጥ ከሌሉ መዳን አት​ች​ሉም” አላ​ቸው። 32ወታ​ደ​ሮ​ችም ወዲ​ያ​ውኑ ተነ​ሥ​ተው የታ​ን​ኳ​ዪ​ቱን ገመድ ቈር​ጠው ትወ​ድቅ ዘንድ ተዉ​አት።
33ሊነ​ጋም በጀ​መረ ጊዜ ጳው​ሎስ እህል እን​ዲ​በሉ ሁሉ​ንም ማለ​ዳ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እህል ከተ​ዋ​ችሁ ዛሬ ዐሥራ አራት ቀን ነው። 34አሁ​ንም እሺ በሉ​ኝና ምግብ ብሉ፤ ራሳ​ች​ሁ​ንም አድኑ፥ ከእ​ና​ንተ ከአ​ንዱ የራስ ጠጕር እንኳ አት​ጠ​ፋ​ምና።” 35ይህ​ንም ተና​ግሮ ኅብ​ስ​ቱን አን​ሥቶ በሁ​ሉም ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገነ፤ ቈር​ሶም ይበላ ዘንድ ጀመረ። 36ሁሉም ተጽ​ናኑ፤ እህ​ልም ቀመሱ። 37በመ​ር​ከቡ ውስጥ የነ​በ​ሩ​ትም ቍጥ​ራ​ቸው ሁለት መቶ ሰባ ስድ​ስት ነፍስ ነበር። 38በል​ተ​ውም በጠ​ገቡ ጊዜ በመ​ር​ከቡ ውስጥ የነ​በ​ረ​ውን ስንዴ ወደ ባሕር ጣሉት፤ መር​ከ​ቡ​ንም አቃ​ለሉ።
39በነጋ ጊዜም ቀዛ​ፊ​ዎች ቦታ​ውን አል​ለ​ዩም፤ የሚ​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም አላ​ወ​ቁም፤ ነገር ግን ለባ​ሕሩ አቅ​ራ​ቢያ የሆ​ነ​ውን የደ​ሴት ተራ​ሮች አዩ፤ መር​ከ​ባ​ቸ​ው​ንም ወደ እዚያ ሊያ​ስ​ጠጉ ፈለጉ። 40መል​ሕ​ቁ​ንም ፈት​ተው በባ​ሕር ላይ ጣሉት፤ የሚ​ያ​ቆ​ሙ​በ​ት​ንም አመ​ቻ​ች​ተው እንደ ነፋሱ አነ​ፋ​ፈስ መጠን ትን​ሹን ሸራ ሰቀሉ፤ ወደ ባሕሩ ዳር​ቻም ሄድን። 41መር​ከ​ቢ​ቱም በሁ​ለት ታላ​ላቅ ድን​ጋ​ዮች መካ​ከል ተቀ​ረ​ቀ​ረች፤ ባሕ​ሩም ጥልቅ ነበረ። ከወ​ደ​ፊ​ቷም ተያ​ዘች፤ አል​ተ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰ​ች​ምም፤ ከሞ​ገ​ዱም የተ​ነሣ በስ​ተ​ኋላ በኩል ጎን​ዋን ተሰ​ብራ ተጐ​ረ​ደች፤ ቀዛ​ፊ​ዎ​ችም ወደ​ፊት ሊገ​ፉ​አት አል​ቻ​ሉም።#“ቀዛ​ፊ​ዎ​ችም ወደ​ፊት ሊገ​ፉ​አት አል​ቻ​ሉም” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። 42ወታ​ደ​ሮ​ቹም ዋኝ​ተው እን​ዳ​ያ​መ​ልጡ እስ​ረ​ኞ​ችን ለመ​ግ​ደል ተማ​ከሩ። 43የመቶ አለ​ቃው ግን ጳው​ሎ​ስን ሊያ​ድ​ነው ወድ​ዶ​አ​ልና ምክ​ራ​ቸ​ውን እንቢ አለ፤ ዋና የሚ​ያ​ው​ቁ​ት​ንም ዋኝ​ተው ወደ ምድር እን​ዲ​ወጡ አዘ​ዛ​ቸው። 44የቀ​ሩ​ትም በመ​ር​ከቡ ስብ​ር​ባሪ ዕን​ጨ​ትና በሳ​ን​ቃው ላይ ተሻ​ገሩ፤ ሌሎ​ችም በመ​ር​ከቡ ገመድ ላይ እየ​ተ​ን​ጠ​ላ​ጠሉ ተሻ​ገሩ፤ ሁሉም እን​ዲህ ባለ ሁኔታ በደ​ኅና ወደ ምድር ደረሱ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ