የተወደደ ወንድማችንና የታመነ አገልጋይ፥ በጌታ ሥራም ተባባሪያችን የሆነ ቲኪቆስ የእኔን ዜና ይነግራችኋል። ስለዚህ ሥራ ወደ እናንተ የላክሁት ዜናዬን ታውቁ ዘንድ፥ ልባችሁንም ያጽናና ዘንድ ነው። ወገናችሁ ከሆነው ከምንወደውና ከታመነው ወንድማችን ከአናሲሞስ ጋር፥ እነርሱ ሥራችንንና ያለንበትን ያስረዱአችኋል። ከእኔ ጋር የተማረከው አርስጥሮኮስ፥ ወደ እናንተ በሚመጣ ጊዜ ትቀበሉት ዘንድ ስለ እርሱ ያዘዝኋችሁ የበርናባስ የአባቱ ወንድም ልጅ ማርቆስም፥ ኢዮስጦስ የተባለ ኢያሱም፥ ከግዙራን ሰዎች ወገን የሚሆኑ እነዚህ ሰላም ይሏችኋል። በእግዚአብሔር መንግሥት ሥራ ረዳቶች እነዚህ ብቻ ናቸው፤ እነርሱም እኔን አጽናንተውኛል። ከእናንተ ወገን የሚሆን ኤጳፍራስም ሰላም ይላችኋል፥ እርሱ የክርስቶስ አገልጋይ ነው፤ እግዚአብሔር በሚወደው ነገር ሁሉ ምሉኣንና ፍጹማን እንድትሆኑ፥ ስለ እናንተ ዘወትር ይጸልያል፤ ይማልዳልም። እጅግ እንደሚወዳችሁና ስለ እናንተ በሎዶቅያና በኢያራ ከተማ ስላሉትም እንደሚቈረቈር እኔ ምስክሩ ነኝ። ወዳጃችን ባለ መድኃኒቱ ሉቃስም ሰላም ብሎአችኋል፤ ዴማስም ሰላም ይላችኋል።
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 4 ያንብቡ
ያዳምጡ ወደ ቈላስይስ ሰዎች 4
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ቈላስይስ ሰዎች 4:7-14
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos