የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ዳን​ኤል 1

1
ዳን​ኤ​ልና ሠለ​ስቱ ደቂቅ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ቤተ መን​ግ​ሥት
1የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​አ​ቄም በነ​ገሠ በሦ​ስ​ተ​ኛው ዓመት የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጥቶ ከበ​ባት። 2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ኢዮ​አ​ቄ​ምን፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ዕቃ ከፍሎ በእጁ አሳ​ልፎ ሰጠው፤ እር​ሱም ወደ ሰና​ዖር ምድር ወደ ጣዖቱ ቤት ወሰ​ደው፥ ዕቃ​ው​ንም ወደ ጣዖቱ ግምጃ ቤት አገ​ባው። 3ንጉ​ሡም ለጃ​ን​ደ​ረ​ቦቹ አለቃ ለአ​ስ​ፋ​ኒዝ፦ ከተ​ማ​ረ​ኩት ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከነ​ገ​ሥ​ታ​ቱና ከመ​ሳ​ፍ​ንቱ ዘር፥ 4ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ው​ንና መልከ መል​ካ​ሞ​ቹን፥ በጥ​በብ ሁሉ የሚ​ያ​ስ​ተ​ው​ሉ​ትን፥ ዕው​ቀ​ትም የሞ​ላ​ባ​ቸ​ውን፥ አስ​ተ​ዋ​ዮች የሆ​ኑ​ትን፥ በን​ጉ​ሡም ቤት መቆም የሚ​ች​ሉ​ትን ብላ​ቴ​ኖች ያመ​ጣና የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ን​ንም ትም​ህ​ር​ትና ቋንቋ ያስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው ዘንድ ነገ​ረው። 5ንጉ​ሡም ሦስት ዓመት ያሳ​ድ​ጉ​አ​ቸው ዘንድ፥ ከዚ​ያም በኋላ በን​ጉሡ ፊት ይቆሙ ዘንድ ከን​ጉሡ ማዕድ፥ ከሚ​ጠ​ጣ​ውም ጠጅ በየ​ዕ​ለቱ ድር​ጎ​አ​ቸ​ውን አዘ​ዘ​ላ​ቸው። 6ከእ​ነ​ዚ​ህም መካ​ከል ከይ​ሁዳ ልጆች ዳን​ኤ​ልና አና​ንያ ሚሳ​ኤ​ልና አዛ​ርያ ነበሩ። 7የጃ​ን​ደ​ረ​ቦ​ቹም አለቃ ስማ​ቸ​ውን ለውጦ፤ ዳን​ኤ​ልን ብል​ጣ​ሶር፥ አና​ን​ያ​ንም ሲድ​ራቅ፥ ሚሳ​ኤ​ል​ንም ሚሳቅ፥ አዛ​ር​ያ​ንም አብ​ደ​ናጎ ብሎ ጠራ​ቸው።
8ዳን​ኤ​ልም ከን​ጉሡ ማዕድ እን​ዳ​ይ​በላ፥ ከሚ​ጠ​ጣ​ውም ጠጅ እን​ዳ​ይ​ጠጣ በልቡ ጨከነ፤ እን​ዳ​ያ​በ​ላ​ውም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እን​ዳ​ያ​ረ​ክ​ሰው” ይላል። የጃ​ን​ደ​ረ​ቦ​ቹን አለቃ ለመ​ነው። 9እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጃ​ን​ደ​ረ​ቦቹ አለቃ ፊት ለዳ​ን​ኤል ሞገ​ስ​ንና ምሕ​ረ​ትን ሰጠው። 10የጃ​ን​ደ​ረ​ቦ​ቹም አለቃ ዳን​ኤ​ልን፥ “መብ​ሉ​ንና መጠ​ጡን ያዘ​ዘ​ላ​ች​ሁን ጌታ​ዬን ንጉ​ሡን እፈ​ራ​ለሁ፤ በዕ​ድሜ እንደ እና​ንተ ከአሉ ብላ​ቴ​ኖች ይልቅ ፊታ​ችሁ ከስቶ ያየ እንደ ሆነ፥ ከን​ጉሡ ዘንድ በራሴ ታስ​ፈ​ር​ዱ​ብ​ኛ​ላ​ችሁ” አለው። 11ዳን​ኤ​ልም የጃ​ን​ደ​ረ​ቦቹ አለቃ በዳ​ን​ኤ​ልና በአ​ና​ንያ፥ በሚ​ሳ​ኤ​ልና በአ​ዛ​ርያ ላይ የሾ​መ​ውን አሚ​ሳ​ድን፦ 12“እኛን አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን ዐሥር ቀን ያህል ፈት​ነን፤ የም​ን​በ​ላ​ው​ንም ጥራ​ጥሬ፥ የም​ን​ጠ​ጣ​ው​ንም ውኃ ይስ​ጡን፤ 13ከዚ​ያም በኋላ የእ​ኛን ሰው​ነ​ትና ከን​ጉሡ ማዕድ የሚ​በ​ሉ​ትን የብ​ላ​ቴ​ኖ​ችን ሰው​ነት ተመ​ል​ከት፤ እንደ አየ​ኸ​ውም ሁሉ ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ጋር የወ​ደ​ድ​ኸ​ውን አድ​ርግ” አለው።
14ይህ​ንም ነገ​ራ​ቸ​ውን ሰምቶ ዐሥር ቀን ፈተ​ና​ቸው። 15ከዐ​ሥር ቀንም በኋላ ከን​ጉሡ ማዕድ ከበሉ ብላ​ቴ​ኖች ሁሉ ይልቅ ሰው​ነ​ታ​ቸው አምሮ፥ ሥጋ​ቸ​ውም ወፍሮ ታየ። 16አሚ​ሳ​ድም መብ​ላ​ቸ​ው​ንና የሚ​ጠ​ጡ​ትን ጠጅ አስ​ቀ​ርቶ ጥራ​ጥ​ሬ​ውን ሰጣ​ቸው።
17ለእ​ነ​ዚ​ህም ለአ​ራቱ ብላ​ቴ​ኖች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በት​ም​ህ​ር​ትና በጥ​በብ ሁሉ ዕው​ቀ​ት​ንና ማስ​ተ​ዋ​ልን ሰጣ​ቸው፤ ዳን​ኤ​ልም በራ​እ​ይና ሕል​ምን በመ​ተ​ር​ጐም ሁሉ አስ​ተ​ዋይ ነበረ። 18እነ​ርሱ ይገቡ ዘንድ ንጉሡ ያዘ​ዘው ቀን በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፥ የጃ​ን​ደ​ረ​ቦቹ አለቃ ወደ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር አገ​ባ​ቸው። 19ንጉ​ሡም በአ​ነ​ጋ​ገ​ራ​ቸው ጊዜ ከብ​ላ​ቴ​ኖቹ ሁሉ እንደ ዳን​ኤ​ልና እንደ አና​ንያ እንደ ሚሳ​ኤ​ልና እንደ አዛ​ርያ ያለ አል​ተ​ገ​ኘም፤ በን​ጉ​ሡም ፊት ቆሙ። 20ንጉ​ሡም በጠ​የ​ቃ​ቸው ጊዜ በጥ​በ​ብና በማ​ስ​ተ​ዋል ነገር ሁሉ፥ በግ​ዛቱ ሁሉ ከሚ​ኖሩ የሕ​ልም ተር​ጓ​ሚ​ዎ​ችና አስ​ማ​ተ​ኞች ሁሉ እነ​ርሱ ዐሥር እጅ የበ​ለጡ ሆነው አገ​ኛ​ቸው። 21ዳን​ኤ​ልም እስከ ንጉሡ እስከ ቂሮስ መጀ​መ​ሪያ ዓመተ መን​ግ​ሥት ተቀ​መጠ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ