የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 48

48
የም​ድ​ሪቱ አከ​ፋ​ፈል
1“የነ​ገ​ዶ​ችም ስም ይህ ነው። በሔ​ት​ሎን መን​ገድ አጠ​ገብ ወደ ሐማት መግ​ቢያ፥ በደ​ማ​ስ​ቆም ድን​በር በአ​ለው በሐ​ጸ​ር​ዔ​ናን በሐ​ማ​ትም አጠ​ገብ በሰ​ሜን በኩል ይጀ​ም​ራል። ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ይሆ​ናል። ለዳን አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል። 2ከዳ​ንም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለአ​ሴር አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል። 3ከአ​ሴ​ርም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለን​ፍ​ታ​ሌም አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል። 4ከን​ፍ​ታ​ሌም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለም​ናሴ አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል። 5ከም​ና​ሴም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለኤ​ፍ​ሬም አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል። 6ከኤ​ፍ​ሬ​ምም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለሮ​ቤል አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል። 7ከሮ​ቤ​ልም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለይ​ሁዳ አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል።
8“ከይ​ሁ​ዳም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለመባ የተ​ለየ ክፍል ይሆ​ናል፤ ወርዱ ሃያ አም​ስት ሺህ ክንድ ይሆ​ናል፤ ርዝ​መ​ቱም ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ከዕጣ ክፍ​ሎች እንደ አንዱ ይሆ​ናል፤ ቤተ መቅ​ደ​ሱም በመ​ካ​ከሉ ይሆ​ናል። 9ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ት​ለ​ዩት መባ ርዝ​መቱ ሃያ አም​ስት ሺህ ወር​ዱም ዐሥር ሺህ#ዕብ. “ሃያ ሺህ” ይላል። ክንድ ይሆ​ናል። 10የመ​ቅ​ደ​ሱም ቀዳ​ም​ያት ለካ​ህ​ናቱ ይሆ​ናል፤ በሰ​ሜን በኩል ርዝ​መቱ ሃያ አም​ስት ሺህ፥ በም​ዕ​ራ​ብም በኩል ወርዱ ዐሥር ሺህ፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ወርዱ ዐሥር ሺህ፥ በደ​ቡ​ብም በኩል ርዝ​መቱ ሃያ አም​ስት ሺህ ክንድ ይሆ​ናል። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤተ መቅ​ደስ በመ​ካ​ከሉ ይሆ​ናል። 11የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በሳቱ ጊዜ፥ ሌዋ​ው​ያን እንደ ሳቱ ላል​ሳ​ቱት፥ ሥር​ዐ​ቴን ለጠ​በ​ቁት፥ ከሳ​ዶቅ ልጆች ወገን ለተ​ቀ​ደ​ሱት ካህ​ናት ይሆ​ናል። 12ከም​ድ​ርም መባ የተ​ለየ ሌላ መባ ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል፤ ከተ​ቀ​ደ​ሱ​ትም ይልቅ የተ​ቀ​ደሰ ይሆ​ናል፤ በሌ​ዋ​ው​ያን ድን​በር አጠ​ገብ ይሆ​ናል።
13በካ​ህ​ና​ቱም ድን​በር አቅ​ራ​ቢያ ርዝ​መቱ ሃያ አም​ስት ሺህ፥ ወር​ዱም ዐሥር ሺህ የሆነ ዕጣ ለሌ​ዋ​ው​ያን ይሆ​ናል፤ ርዝ​መቱ ሁሉ ሃያ አም​ስት ሺህ፥ ወር​ዱም ሃያ ሺህ ክንድ ይሆ​ናል። 14ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ቀ​ደሰ ነውና ከእ​ርሱ ምንም አይ​ሸ​ጡም፤ አይ​ለ​ው​ጡ​ምም፤ የም​ድ​ሩም ቀዳ​ም​ያት አይ​ፋ​ለ​ስም።
15በሃያ አም​ስቱ ሺህ አን​ጻር አም​ስት ሺህ ወርድ ያለው የቀረ ቅዱስ ያይ​ደለ ስፍራ ለከ​ተ​ማ​ዪቱ ለጋራ ጉዳ​ይዋ፥ ለመ​ኖ​ሪያ፥ ለማ​ሰ​ማ​ር​ያም ይሆ​ናል፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱም በመ​ካ​ከሉ ትሆ​ና​ለች። 16ልክ​ዋም ይህ ነው፤ በሰ​ሜን በኩል አራት ሺህ አም​ስት መቶ፥ በደ​ቡ​ብም በኩል አራት ሺህ አም​ስት መቶ፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል አራት ሺህ አም​ስት መቶ፥ በም​ዕ​ራ​ብም በኩል አራት ሺህ አም​ስት መቶ ክንድ ይሆ​ናል። 17ለከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ማሰ​ማ​ርያ ይኖ​ራ​ታል፤ በሰ​ሜን በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በደ​ቡ​ብም በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በም​ዕ​ራ​ብም በኩል ሁለት መቶ አምሳ ክንድ ይሆ​ናል። 18“በተ​ቀ​ደ​ሰው መባ አን​ጻር የተ​ረ​ፈው ርዝ​መቱ ወደ ምሥ​ራቅ ዐሥር ሺህ፥ ወደ ምዕ​ራ​ብም ዐሥር ሺህ ክንድ ይሆ​ናል። በተ​ቀ​ደ​ሰው መባ አን​ጻር ይሆ​ናል። ፍሬ​ውም ከተ​ማ​ዪ​ቱን ለሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ መብል ይሆ​ናል። 19ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ ከተ​ማ​ዪ​ቱን የሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ያር​ሱ​ታል። 20መባው ሁሉ ርዝ​መቱ ሃያ አም​ስት ሺህ፥ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ሺህ ክንድ ይሆ​ናል፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን መባ ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ይዞታ ጋር አራት ማዕ​ዘን አድ​ር​ጋ​ችሁ ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ።
21“በተ​ቀ​ደ​ሰው መባና በከ​ተ​ማ​ዪቱ ይዞታ፥ በዚ​ህና በዚያ ወገን የቀ​ረው ለአ​ለ​ቃው ይሆ​ናል፤ በመ​ባው በሃያ አም​ስት ሺህ ፊት እስከ ምሥ​ራቁ ድን​በር፥ በም​ዕ​ራ​ብም በኩል በሃያ አም​ስት ሺህ ፊት እስከ ምዕ​ራቡ ድን​በር፥ እንደ ዕጣ ክፍል ሁሉ መጠን፥ ለአ​ለ​ቃው ይሆ​ናል፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም መባና ቤተ መቅ​ደሱ በመ​ካ​ከሉ ይሆ​ናል። 22የሌ​ዋ​ው​ያን ርስት፥ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ይዞታ ለአ​ለ​ቃው በሆ​ነው መካ​ከል ይሆ​ናል፤ በይ​ሁዳ ድን​በ​ርና በብ​ን​ያም ድን​በር መካ​ከል የአ​ለ​ቃው ዕጣ ክፍል ይሆ​ናል።
23“ለቀ​ሩ​ትም ነገ​ዶች እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለብ​ን​ያም አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል። 24ከብ​ን​ያ​ምም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለስ​ም​ዖን አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል። 25ከስ​ም​ዖ​ንም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለይ​ሳ​ኮር አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል። 26ከይ​ሳ​ኮ​ርም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለዛ​ብ​ሎን አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል። 27ከዛ​ብ​ሎ​ንም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለጋድ አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል። 28ከጋ​ድም ድን​በር ቀጥሎ በደ​ቡብ በኩል ድን​በሩ ከታ​ማር ጀምሮ እስከ ሜሪባ ቃዴስ ውኃ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ይሆ​ናል። 29ርስት አድ​ር​ጋ​ችሁ ለእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች በዕጣ የም​ታ​ካ​ፍ​ሉ​አት ምድር ይህች ናት፤ የእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ዕጣ እን​ደ​ዚህ ነው፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቅጽር በሮች
30“የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም መው​ጫ​ዎች እነ​ዚህ ናቸው። በሰ​ሜን ወገን ልኩ አራት ሺህ አም​ስት መቶ ክንድ ነው። 31የከ​ተ​ማ​ዪቱ በሮች እንደ እስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ስም ይሆ​ናሉ፤ በሰ​ሜን በኩል አንዱ የሮ​ቤል በር፤ አን​ዱም የይ​ሁዳ በር፥ አን​ዱም የሌዊ በር ሦስት በሮች ይሆ​ናሉ። 32በም​ሥ​ራ​ቁም ወገን አራት ሺህ አም​ስት መቶ ክንድ፥ ሦስ​ትም በሮች አሉ፤ አንዱ የዮ​ሴፍ በር፥ አን​ዱም የብ​ን​ያም በር፥ አን​ዱም የዳን በር ነው። 33በደ​ቡ​ቡም ወገን ልኩ አራት ሺህ አም​ስት መቶ ክንድ፥ ሦስ​ትም በሮች አሉ፤ አንዱ የስ​ም​ዖን በር፥ አን​ዱም የይ​ሳ​ኮር በር፥ አን​ዱም የዛ​ብ​ሎን በር ነው። 34በም​ዕ​ራ​ቡም ወገን ልኩ አራት ሺህ አም​ስት መቶ ክንድ፥ ሦስ​ትም በሮች አሉ፤ አንዱ የጋድ በር፥ አን​ዱም የአ​ሴር በር፥ አን​ዱም የን​ፍ​ታ​ሌም በር ነው። 35ዙሪ​ያ​ዋም ዐሥራ ስም​ንት ሺህ ክንድ ይሆ​ናል፥ ከዚ​ያም ቀን ጀምሮ የከ​ተ​ማ​ዪቱ ስም፦ ‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ አለ’ ተብሎ ይጠ​ራል።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ