የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 47

47
ከቤተ መቅ​ደሱ ሥር የሚ​ፈ​ል​ቀው ምንጭ
1ወደ መቅ​ደ​ሱም መዝ​ጊያ መለ​ሰኝ፤ እነ​ሆም ውኃ ከቤቱ መድ​ረክ በታች ወደ ምሥ​ራቅ ይወጣ ነበር፤ የቤቱ ፊት ወደ ምሥ​ራቅ ይመ​ለ​ከት ነበ​ርና፤ ውኃ​ውም ከቤቱ ከቀኝ ወገን በታች በመ​ሠ​ዊ​ያው በደ​ቡብ በኩል ይወ​ርድ ነበር። 2በሰ​ሜ​ኑም በር በኩል አወ​ጣኝ፤ በስተ ውጭ በአ​ለው መን​ገድ፥ ወደ ምሥ​ራቅ ወደ​ሚ​መ​ለ​ከት በስተ ውጭ ወዳ​ለው በር አዞ​ረኝ፤ እነ​ሆም ውኃው በቀኝ በኩል ይፈ​ስስ ነበር።
3ሰው​ዮ​ውም የመ​ለ​ኪያ ገመድ በእጁ ይዞ ወደ ምሥ​ራቅ ወጣ፤ አንድ ሺህም ክንድ ለካ፤ በው​ኃ​ውም ውስጥ አሻ​ገ​ረኝ፤ ውኃ​ውም እስከ ቍር​ጭ​ም​ጭ​ሚት ደረሰ። 4ደግሞ አንድ ሺህ ለካ፤ በው​ኃ​ውም ውስጥ አሻ​ገ​ረኝ፤ ውኃ​ውም እስከ ጉል​በት ደረሰ፤ ደግ​ሞም አንድ ሺህ ለካ፤ በው​ኃ​ውም ውስጥ አሻ​ገ​ረኝ፤ ውኃ​ውም እስከ ወገብ ደረሰ። 5ደግሞ አንድ ሺህ ለካ ልሻ​ገ​ረ​ውም የማ​ል​ች​ለው ወንዝ ሆነ፤ ውኃ​ውም ጥልቅ ነበረ፤ የሚ​ዋ​ኝ​በ​ትም ውኃ ነበረ፤ ሰው ሊሻ​ገ​ረው የማ​ይ​ች​ለው ወንዝ ነበረ።
6እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! አይ​ተ​ሃ​ልን?” አለኝ። አመ​ጣ​ኝም፤ ወደ ወን​ዙም ዳር መለ​ሰኝ። 7በተ​መ​ለ​ስ​ሁም ጊዜ፥ እነሆ በወ​ንዙ ዳር በዚ​ህና በዚያ እጅግ ብዙ ዛፎች ነበሩ። 8እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “ይህ ውኃ ወደ ምሥ​ራቅ ወደ ገሊላ ይወ​ጣል፤ ወደ ዓረ​ባም ይወ​ር​ዳል፤ ወደ ባሕ​ሩም ይገ​ባል፤ ወደ ባሕ​ሩም ወደ ረከ​ሰው ውኃ በገባ ጊዜ ውኃ​ውን ይፈ​ው​ሰ​ዋል። 9ሕያው ነፍስ ያለው ተን​ቀ​ሳ​ቃሽ ሁሉ ወንዙ በሚ​ገ​ባ​በት ስፍራ ሁሉ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፤ ይህም ውኃ በዚያ ስለ ደረሰ ዓሣ​ዎች እጅግ ይበ​ዛሉ፤ የባ​ሕ​ሩም ውኃ ይፈ​ወ​ሳል፤ ወን​ዙም በሚ​መ​ጣ​በት ያለው ሁሉ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል። 10ዓሣ አጥ​ማ​ጆ​ችም ከዓ​ይ​ን​ጋዲ ጀምሮ እስከ ዓይ​ን​ኤ​ግ​ላ​ይም ድረስ በዚያ ይቆ​ማሉ። ያም መረብ መዘ​ር​ጊያ ይሆ​ናል፤ ዓሣ​ዎ​ችም እንደ ታላቁ ባሕር ዓሣ​ዎች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው እጅግ ይበ​ዛሉ። 11ረግ​ረ​ጉና ዕቋ​ሪው ውኃ ግን ጨው እንደ ሆነ ይኖ​ራል እንጂ አይ​ፈ​ወ​ስም። 12በወ​ን​ዙም አጠ​ገብ በዳሩ ላይ በዚ​ህና በዚያ ፍሬው የሚ​በላ ዛፍ ሁሉ ይበ​ቅ​ላል፤ ቅጠ​ሉም አይ​ረ​ግ​ፍም፤ ፍሬ​ውም አይ​ጐ​ድ​ልም፤ ውኃ​ውም ከመ​ቅ​ደስ ይወ​ጣ​ልና በየ​ወሩ ሁሉ የፍሬ በኵር ያገ​ኛል፤ ፍሬ​ውም ለመ​ብል፥ ቅጠ​ሉም ለመ​ድ​ኀ​ኒት ይሆ​ናል።”
የም​ድ​ሪቱ ወሰ​ኖች
13ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ርስት አድ​ር​ጋ​ችሁ ለዐ​ሥራ ሁለቱ የእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ምድ​ሪ​ቱን የም​ት​ከ​ፍ​ሉ​በት ድን​በር ይህ ነው። ለዮ​ሴፍ ሁለት ዕጣ ይሆ​ናል።#“ለዮ​ሴፍ ሁለት ዕጣ ይሆ​ናል” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 14ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ እሰ​ጣ​ቸው ዘንድ እጄን አን​ሥቼ#ዕብ. “ምዬ” ይላል። ነበ​ርና እና​ንተ እኩል አድ​ር​ጋ​ችሁ ተካ​ፈ​ሉት፤ ይህ​ችም ምድር ርስት ትሆ​ና​ች​ኋ​ለች።
15“የም​ድ​ሪ​ቱም ድን​በር ይህ ነው። በሰ​ሜኑ ወገን ከታ​ላቁ ባሕር ጀምሮ በሔ​ት​ሎን መን​ገድ ወደ ጽዳድ መግ​ቢያ፤ 16ሐማት፥ ቤሮታ፥ በደ​ማ​ስቆ ድን​በ​ርና በሐ​ማት ድን​በር መካ​ከል ያለው ሲብ​ራ​ይም፥ በሐ​ው​ራን ድን​በር አጠ​ገብ ያለው ሐጸ​ር​ሃ​ቲ​ኮን። 17ድን​በሩ ከባ​ሕሩ በደ​ማ​ስቆ ድን​በር ላይ ያለው ሐጽ​ር​ዔ​ናን ይሆ​ናል፥ በሰ​ሜን በኩል የሐ​ማት ድን​በር አለ። የሰ​ሜኑ ድን​በር ይህ ነው። 18የም​ሥ​ራ​ቁም ድን​በር በሐ​ው​ራን በደ​ማ​ስ​ቆና በገ​ለ​ዓድ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ምድር መካ​ከል ዮር​ዳ​ኖስ ይሆ​ናል። ከሰ​ሜኑ ድን​በር ጀምሮ እስከ ምሥ​ራቁ ባሕር እስከ ታማር#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ፊን​ቂን” ይላል። ድረስ የም​ሥ​ራቁ ድን​በር ይህ ነው። 19የደ​ቡ​ቡም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሌብ” የሚል ይጨ​ም​ራል። ድን​በር ከታ​ማር ጀምሮ እስከ ሜሪባ ቃዴስ ውኃ እስከ ግብፅ ወንዝ#“እስከ ግብፅ ወንዝ” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። እስከ ታላቁ ባሕር ይሆ​ናል። የደ​ቡ​ቡም ድን​በር ይህ ነው። 20የም​ዕ​ራ​ቡም ድን​በር ከደ​ቡቡ ድን​በር ጀምሮ እስከ ሐማት መግ​ቢያ አን​ጻር ድረስ ታላቁ ባሕር ይሆ​ናል። የም​ዕ​ራቡ ድን​በር ይህ ነው።
21“ይህ​ችን ምድር እና​ንተ ዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስ​ራ​ኤል ትከ​ፋ​ፈ​ላ​ላ​ችሁ። 22ለእ​ና​ን​ተና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ለሚ​ቀ​መጡ፥ በእ​ና​ን​ተም መካ​ከል ልጆ​ችን ለሚ​ወ​ልዱ መጻ​ተ​ኞች ርስት አድ​ር​ጋ​ችሁ በዕጣ ትካ​ፈ​ሉ​አ​ታ​ላ​ችሁ፤ እነ​ር​ሱም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል እንደ አሉ የሀ​ገር ልጆች ይሆ​ኑ​ላ​ች​ኋል፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገ​ዶች መካ​ከል ከእ​ና​ንተ ጋር ርስ​ትን ይወ​ር​ሳሉ። 23መጻ​ተ​ኛ​ውም በማ​ና​ቸ​ውም ነገድ መካ​ከል ቢቀ​መጥ በዚያ ርስ​ትን ትሰ​ጡ​ታ​ላ​ችሁ፤ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ