ትን​ቢተ ዳን​ኤል 11

11
1“እኔም በሜ​ዶ​ና​ዊው በዳ​ር​ዮስ መጀ​መ​ሪያ ዓመት አጸ​ና​ውና አበ​ረ​ታው ዘንድ ቆሜ ነበር።
2“አሁ​ንም እው​ነ​ትን እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ። እነሆ ሦስት ነገ​ሥ​ታት ደግሞ በፋ​ርስ ይነ​ሣሉ፤ አራ​ተ​ኛ​ውም ከሁሉ ይልቅ እጅግ ባለ​ጸጋ ይሆ​ናል፤ በባ​ለ​ጸ​ግ​ነ​ቱም በበ​ረታ ጊዜ በግ​ሪክ መን​ግ​ሥት ላይ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በግ​ሪ​ኮች መን​ግ​ሥ​ታት ላይ” ይላል። ሁሉን ያስ​ነ​ሣል። 3ኀያ​ልም ንጉሥ ይነ​ሣል፤ ትልቅ አገ​ዛ​ዝ​ንም ይገ​ዛል፤ እንደ ፈቃ​ዱም ያደ​ር​ጋል። 4በተ​ነ​ሣም ጊዜ መን​ግ​ሥቱ ትሰ​በ​ራ​ለች፤ በአ​ራ​ቱም ነፋ​ሳት ትበ​ተ​ና​ለች፤ ለዘሩ ግን አይ​ከ​ፋ​ፈ​ልም፤ ከእ​ር​ሱም በኋላ እርሱ እንደ ገዛ​በት አገ​ዛዝ አይ​ሆ​ንም፤ መን​ግ​ሥቱ ታል​ፋ​ለች፤ ከእ​ነ​ዚ​ህም ለሌ​ሎች ትሰ​ጣ​ለች።
5“የአ​ዜ​ብም ንጉሥ ይበ​ረ​ታል፤ ከአ​ለ​ቆ​ቹም አንዱ በእ​ርሱ ላይ ይበ​ረ​ታል፤ ከእ​ር​ሱም ይልቅ ብዙ ግዛ​ትን ይገ​ዛል። 6ከዘ​መ​ና​ትም በኋላ ይቀ​ላ​ቀ​ላሉ፤ የአ​ዜ​ብም ንጉሥ ሴት ልጅ ቃል ኪዳን ለማ​ድ​ረግ ወደ መስዕ ንጉሥ ትመ​ጣ​ለች። የክ​ን​ድዋ ኀይል ግን አይ​ጸ​ናም፤ ዘሩም#ዕብ. “እር​ሱና ክንዱ” ይላል። አይ​ጸ​ናም፤ እር​ስ​ዋና እር​ስ​ዋን ያመጡ፥ የወ​ለ​ዳ​ትም፥ በዚ​ያም ዘመን ያጸ​ናት አል​ፈው ይሰ​ጣሉ።
7ነገር ግን ከሥ​ርዋ ቍጥ​ቋጥ አንዱ በስ​ፍ​ራው ይነ​ሣል፤ ወደ ሠራ​ዊ​ቱም ይመ​ጣል፤ ወደ መስ​ዕም ንጉሥ አምባ ይገ​ባል፤ በላ​ያ​ቸ​ውም ያደ​ር​ጋል፤ ያሸ​ን​ፍ​ማል። 8አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ትን ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን ከብ​ርና ከወ​ር​ቅም የተ​ሠ​ሩ​ትን የከ​በ​ሩ​ትን ዕቃ​ዎች ወደ ግብፅ ይማ​ር​ካል፤#ግእዝ “አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውን ከአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ከመ​ኳ​ን​ን​ቶ​ቻ​ቸው ከተ​ወ​ደደ ገን​ዘ​ባ​ቸው ሁሉ ጋር ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል ወር​ቃ​ቸ​ውና ብራ​ቸ​ውም በም​ርኮ ወደ ግብፅ ይወ​ሰ​ዳል” ይላል። እር​ሱም ከመ​ስዕ ንጉሥ በላይ ሆኖ ይቆ​ማል።#ዕብ. “እስከ ጥቂ​ትም ዓመት ድረስ ከሰ​ሜን ንጉሥ ጋር ሳይ​ዋጋ ይቀ​መ​ጣል” ይላል። 9ይህም ወደ አዜብ ንጉሥ መን​ግ​ሥት ይገ​ባል፥ ነገር ግን ወደ ገዛ ምድሩ ይመ​ለ​ሳል።
10“ልጆ​ቹም ይዋ​ጋሉ፤ ብዙ ሕዝ​ብ​ንና ሠራ​ዊ​ትን ይሰ​በ​ስ​ባሉ፤ እር​ሱም ይመ​ጣል፤ ይበ​ረ​ታ​ማል፤ ያል​ፍ​ማል፤ ተመ​ል​ሶም እስከ አም​ባው ድረስ ይዋ​ጋል። 11የአ​ዜ​ብም ንጉሥ ይቈ​ጣል፤ ወጥ​ቶም ከመ​ስዕ ንጉሥ ጋር ይዋ​ጋል፤ ብዙ ሕዝ​ብ​ንም ለሰ​ልፍ ያቆ​ማል፤ ሕዝ​ቡም አልፎ በእጁ ይሰ​ጣል። 12ሕዝ​ቡ​ንም ይወ​ስ​ዳል፤ ልቡ​ንም ያስ​ታ​ብ​ያል፤ አእ​ላ​ፋ​ት​ንም ይጥ​ላል፤ ነገር ግን አያ​ሸ​ን​ፍም። 13የመ​ስ​ዕም ንጉሥ ይመ​ለ​ሳል፥ ከቀ​ደ​መ​ውም የበ​ለጠ ብዙ ሕዝ​ብን ያቆ​ማል፤ በዘ​መ​ና​ትና በዓ​መ​ታ​ትም ፍጻሜ ከታ​ላቅ ሠራ​ዊ​ትና ከብዙ ሀብት ጋር ይመ​ጣል። 14በዚ​ያም ዘመን ብዙ ሰዎች በአ​ዜብ ንጉሥ ላይ ይነ​ሣሉ፤ ከሕ​ዝ​ብ​ህም መካ​ከል የዐ​መፅ ልጆች ራእ​ዩን ያጸኑ ዘንድ ይነ​ሣሉ፤ ነገር ግን ይወ​ድ​ቃሉ። 15የመ​ስ​ዕም ንጉሥ ይመ​ጣል፤ አፈ​ር​ንም ይደ​ለ​ድ​ላል፤ የተ​መ​ሸ​ገ​ች​ንም ከተማ ይይ​ዛል፤ የአ​ዜ​ብም ክንድ የተ​መ​ረ​ጡ​ትም ሕዝብ አይ​ቆ​ሙም፤ ለመ​ቋ​ቋ​ምም ኀይል የላ​ቸ​ውም። 16ወደ እርሱ የሚ​መ​ጣው እንደ ፈቃዱ ያደ​ር​ጋል፤ በፊ​ቱም የሚ​ቆም የለም፤ በመ​ል​ካ​ሚ​ቱም ምድር ይቆ​ማል፤ ሁሉም በእጁ ይፈ​ጸ​ማል። 17ከመ​ን​ግ​ሥ​ቱም ሁሉ ኀይል ጋር ይመጣ ዘንድ ፊቱን ያቀ​ናል፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አን​ድ​ነ​ትን ያደ​ር​ጋል፤ ለጥ​ፋ​ቱም ሴት ልጅ ትሰ​ጠ​ዋ​ለች፤ እር​ስ​ዋም አት​ጸ​ናም፤ ለእ​ር​ሱም አት​ሆ​ንም። 18ከዚ​ህም በኋላ ፊቱን ወደ ደሴ​ቶች ይመ​ል​ሳል፤ ብዙ​ዎ​ች​ንም ይወ​ስ​ዳል፤ የኀ​ፍ​ረት አለ​ቆ​ቹ​ንም ይሽ​ራል፤ ኀፍ​ረ​ቱም በላዩ ይመ​ለ​ሳል። 19ፊቱ​ንም ወደ ገዛ ምድሩ አን​ባ​ዎች ይመ​ል​ሳል፤ ደክ​ሞም ይወ​ድ​ቃል፤ አይ​ገ​ኝ​ምም።
20“የመ​ን​ግ​ሥ​ትን ሥል​ጣ​ንና ክብር የሚ​ሽር ይነ​ሣል፤ በመ​ን​በ​ሩም ይቀ​መ​ጣል፤ ነገር ግን በቍ​ጣም ሳይ​ሆን፥ በጦ​ር​ነ​ትም ሳይ​ሆን ከጥ​ቂት ቀን በኋላ ይሰ​በ​ራል።
ጨካኙ የሶ​ርያ ንጉሥ
21በእ​ር​ሱም ስፍራ የተ​ጠቃ ሰው ይነ​ሣል፤ የመ​ን​ግ​ሥ​ቱ​ንም ክብር አይ​ሰ​ጡ​ትም፤ በቀ​ስታ ይመ​ጣል፤ መን​ግ​ሥ​ት​ንም በማ​ታ​ለል ይይ​ዛል። 22የሚ​ጐ​ርፉ ተዋ​ጊ​ዎ​ቹም ክን​ዶች ከፊቱ ይሰ​በ​ራሉ፤ እር​ሱና የቃል ኪዳኑ አለ​ቃም ይሰ​በ​ራሉ። 23ከእ​ር​ሱም ጋር ከተ​ወ​ዳጀ በኋላ ተን​ኰ​ልን ያደ​ር​ጋል፤ ከጥ​ቂ​ትም ሕዝብ ጋር ወጥቶ ይበ​ረ​ታል። 24በቀ​ስ​ታም ከሀ​ገር ሁሉ ወደ ለመ​ለ​መ​ችው ክፍል ይገ​ባል፤ አባ​ቶ​ቹና የአ​ባ​ቶቹ አባ​ቶች ያላ​ደ​ረ​ጉ​ት​ንም ያደ​ር​ጋል፤ ብዝ​በ​ዛ​ው​ንና ምር​ኮ​ውን፥ ሀብ​ቱ​ንም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ይበ​ት​ናል፤ በም​ሽ​ጎ​ችም ላይ እስከ ጊዜው ድረስ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በግ​ብፅ ላይ” የሚል ይጨ​ም​ራል። ዐሳ​ቡን ይፈ​ጥ​ራል። 25በታ​ላ​ቅም ሠራ​ዊት ሆኖ ኀይ​ሉ​ንና ልቡን በአ​ዜብ ንጉሥ ላይ ያስ​ነ​ሣል፤ የአ​ዜ​ብም ንጉሥ በታ​ላ​ቅና በብዙ ሠራ​ዊት ይበ​ረ​ታል፤ ነገር ግን ዐሳብ በእ​ርሱ ላይ ይፈ​ጥ​ራ​ሉና አይ​ጸ​ናም። 26መብ​ሉ​ንም የሚ​በሉ ሰዎች ይሰ​ብ​ሩ​ታል፤ ሠራ​ዊ​ቱም ይጐ​ር​ፋል፤ ብዙ​ዎ​ችም ተገ​ድ​ለው ይወ​ድ​ቃሉ። 27እነ​ዚ​ህም ሁለት ነገ​ሥ​ታት በል​ባ​ቸው ክፋ​ትን ያደ​ር​ጋሉ፤ በአ​ንድ ገበ​ታም ተቀ​ም​ጠው ሐሰ​ትን ይና​ገ​ራሉ፤ ገና ጊዜው አል​ደ​ረ​ሰ​ምና አይ​ከ​ና​ወ​ን​ላ​ቸ​ውም።
28“ከብ​ዙም ሀብት ጋር ወደ ምድሩ ይመ​ለ​ሳል፥ ልቡም በተ​ቀ​ደ​ሰው ቃል ኪዳን ላይ ይሆ​ናል፤ ፈቃ​ዱ​ንም ያደ​ር​ጋል፥ ወደ ገዛ ምድ​ሩም ይመ​ለ​ሳል። 29በተ​ወ​ሰ​ነ​ውም ጊዜ ይመ​ለ​ሳል፤ ወደ አዜ​ብም ይመ​ጣል፤ ነገር ግን የኋ​ለ​ኛው እንደ ፊተ​ኛው አይ​ሆ​ንም። 30ጺም፥ ከይ​ተ​ምና ኔባእ በእ​ርሱ ላይ ይመ​ጣሉ#ዕብ. “የኪ​ትም መር​ከ​ቦች ይመ​ጡ​በ​ታል” ይላል። ስለ​ዚህ አዝኖ#“ስለ​ዚህ አዝኖ” የሚ​ለው በግ​እዝ የለም። ይመ​ለ​ሳል፥ በቅ​ዱ​ሱም ቃል ኪዳን ላይ ይቈ​ጣል፤ ፈቃ​ዱ​ንም ያደ​ር​ጋል፤ ተመ​ል​ሶም ቅዱ​ሱን ቃል ኪዳን የተ​ዉ​ትን ሰዎች ይመ​ለ​ከ​ታል። 31ዘሮ​ችም ከእ​ርሱ ይነ​ሣሉ፤ ቤተ መቅ​ደ​ሱ​ንም ያረ​ክ​ሳሉ፤ የዘ​ወ​ት​ሩ​ንም መሥ​ዋ​ዕት ያስ​ቀ​ራሉ፤ የጥ​ፋ​ት​ንም ርኵ​ሰት ያቆ​ማሉ። 32ቃል ኪዳ​ኑን የሚ​በ​ድ​ሉ​ት​ንም በማ​ታ​ለል ያስ​ታሉ፤ ነገር ግን አም​ላ​ካ​ቸ​ውን የሚ​ያ​ውቁ ሕዝብ ይበ​ረ​ታሉ፤ ያደ​ር​ጋ​ሉም። 33በሕ​ዝ​ቡም መካ​ከል ያሉ ጥበ​በ​ኞች ብዙ ሰዎ​ችን ያስ​ተ​ም​ራሉ፤ ነገር ግን በሰ​ይ​ፍና በእ​ሳት ነበ​ል​ባል በም​ር​ኮና በብዙ ዘመን ብዝ​በዛ ይደ​ክ​ማሉ። 34በመ​ከ​ራም ጊዜ በጥ​ቂት ርዳታ ይረ​ዳሉ፤ ብዙ ሰዎ​ችም በግ​ብ​ዝ​ነት ወደ እነ​ርሱ ይጨ​መ​ራሉ። 35ጊዜው ገና አል​ደ​ረ​ሰ​ምና ያግ​ሏ​ቸው፥ ያነ​ጿ​ቸ​ውና ያጠ​ሯ​ቸው ዘንድ ከዐ​ዋ​ቂ​ዎች እኩ​ሌ​ቶቹ እስከ ጊዜው ድረስ መከራ ይቀ​በ​ላሉ፤ በከ​በረ ቦታ የሚ​ቆም፥ መጽ​ሐ​ፍ​ንም የሚ​ያ​ነ​ብብ ሰው ይህን ነገር ልብ ያድ​ርግ።#ምዕ. 11 ቍ. 35 በዕብ. እና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. አጭር ነው።
36“ንጉ​ሡም እንደ ፈቃዱ ያደ​ር​ጋል፤ ራሱ​ንም ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጋል፤ በአ​ማ​ል​ክት ሁሉ ላይ ራሱን ታላቅ ያደ​ር​ጋል፤ በአ​ማ​ል​ክ​ትም አም​ላክ ላይ በት​ዕ​ቢት ይና​ገ​ራል፤ ቍጣም እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ ይከ​ና​ወ​ን​ለ​ታል፤ የተ​ወ​ሰ​ነው ይደ​ረ​ጋ​ልና። 37የአ​ባ​ቶ​ቹ​ንም አም​ላክ፥ የሴ​ቶ​ች​ንም ምኞት አያ​ከ​ብ​ርም፤ ራሱ​ንም በሁሉ ላይ ታላቅ ያደ​ር​ጋ​ልና አማ​ል​ክ​ትን ሁሉ አያ​ው​ቅም። 38ጽኑዕ በሆነ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥል​ጣ​ንም ይኰ​ራል፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በእ​ነ​ዚህ ፋንታ ግን የአ​ም​ባ​ዎ​ቹን አም​ላክ ያከ​ብ​ራል” ይላል። አባ​ቶ​ቹም ያላ​ወ​ቁ​ትን አም​ላክ በወ​ር​ቅና በብር፥ በዕ​ን​ቍና በከ​በረ ነገር ያከ​ብ​ረ​ዋል። 39ከባ​ዕ​ድም አም​ላክ ጋር የተ​መ​ሸጉ ጽኑ አም​ባ​ዎ​ችን ያደ​ር​ጋል፤ ክብ​ርን ያበ​ዛ​ላ​ቸ​ዋል፤ በብ​ዙም ላይ ያስ​ገ​ዛ​ቸ​ዋል፤ ምድ​ር​ንም በዋጋ ይከ​ፍ​ላል።
40“በፍ​ጻሜ ዘመ​ንም የዐ​ዜብ ንጉሥ ከእ​ርሱ ጋር ይዋ​ጋል፤ የመ​ስ​ዕም ንጉሥ ከሠ​ረ​ገ​ሎ​ችና ከፈ​ረ​ሰ​ኞች፥ ከብዙ መር​ከ​ቦ​ችም ጋር ይመ​ጣ​በ​ታል፤ ወደ ሀገ​ሮ​ችም ይገ​ባል፤ ይጐ​ር​ፍ​ማል፥#“ይጐ​ር​ፍ​ማል” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። ያል​ፍ​ማል። 41ወደ መል​ካ​ሚ​ቱም ምድር ይገ​ባል፤ ብዙ ሀገ​ሮ​ችም ይወ​ድ​ቃሉ፤ ነገር ግን ኤዶ​ም​ያ​ስና ሞዓብ፥ ከአ​ሞ​ንም ልጆች የበ​ለ​ጡት ከእጁ ይድ​ናሉ። 42እጁን በሀ​ገ​ሮች ላይ ይዘ​ረ​ጋል፤ የግ​ብ​ፅም ምድር ከእጁ አታ​መ​ል​ጥም። 43በወ​ር​ቅና በብ​ርም መዝ​ገብ ላይ ፥ በከ​በ​ረ​ችም በግ​ብፅ ዕቃ ሁሉ ላይ ይሠ​ለ​ጥ​ናል፤ የሊ​ብ​ያና#ግእዝ “የኖ​ብ​ያና” ይላል። የኢ​ት​ዮ​ጵያ ሰዎ​ችም ረዳ​ቶች ይሆ​ኑ​ታል። 44ከም​ሥ​ራ​ቅና ከሰ​ሜን ግን ወሬ ይደ​ር​ሰ​ዋል፤ ይቸ​ኩ​ላ​ልም፤ ብዙ ሰዎ​ች​ንም ይገ​ድ​ልና ፈጽሞ ያጠፋ ዘንድ በታ​ላቅ ቍጣ ይወ​ጣል። 45ንጉ​ሣዊ ድን​ኳ​ኑ​ንም በባ​ሕ​ርና በከ​በ​ረው በቅ​ዱሱ ተራራ መካ​ከል ይተ​ክ​ላል፤ እስከ ጊዜ​ውም ይበ​ረ​ታል። የሚ​ረ​ዳ​ውም የለም።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ