ትንቢተ ዳንኤል 12
12
የዓለም ፍጻሜ
1“በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል፤ ሕዝብም በምድር ከተፈጠረ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመን ይሆናል፤ በዚያም ዘመን በመጽሐፉ ተጽፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ እያንዳንዱ ይድናል። 2በምድርም ትቢያ ውስጥ ከአንቀላፉት ብዙዎች እኩሌቶቹ ለዘለዓለም ሕይወት፥ እኩሌቶቹም ለእፍረትና ለዘለዓለም ጕስቍልና ይነሣሉ። 3ጥበበኞቹም እንደ ሰማይ ፀዳል፥ ከጻድቃንም ብዙዎች#ዕብ. “ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ” ይላል። እንደ ከዋክብት ለዘለዓለም ያበራሉ። 4ዳንኤል ሆይ! አንተ ግን እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ ቃሉን ዝጋ፤ መጽሐፉንም አትም፤ ብዙ ሰዎች ይመረምራሉ፤ እውቀትም ይበዛል።”
5እኔም ዳንኤል አየሁ፤ እነሆም ሁለት ሌሎች ቆመው ነበር፤ አንዱ በዚህ በወንዙ ዳር፥ ሌላውም በዚያ በወንዙ ዳር። 6አንዱም ከወንዙ ውኃ በላይ የነበረውን በፍታም የለበሰውን፥ “የዚህ ምልክት ፍጻሜ እስከ መቼ ነው?” አለው። 7ከወንዙም ውኃ በላይ የነበረው፥ በፍታም የለበሰው ሰው ቀኝና ግራ እጁን ወደ ሰማይ አንሥቶ፥ “ለዘመንና ለዘመናት፥ ለዘመንም እኩሌታ ነው ፤ የተቀደሰውም ሕዝብ ኀይል መበተን በተጨረሰ ጊዜ ይህ ሁሉ ይፈጸማል” ብሎ ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ በሚኖረው ሲምል ሰማሁ። 8ሰማሁም፤ ነገር ግን አላስተዋልሁም፤ የዚያን ጊዜም፥ “ጌታዬ ሆይ! የዚህ ሁሉ ፍጻሜ ምንድን ነው?” አልሁ። 9እርሱም እንዲህ አለኝ፥ “ዳንኤል ሆይ! ቃሉ እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ የተዘጋና የታተመ ነውና ሂድ፤ 10ብዙ ሰዎችም ሰውነታቸውን ያጠራሉ፤ ያነጡማል፤ ይፈተኑማል፤ ክፉዎች ግን ክፋትን ያደርጋሉ፤ ክፉዎችም ሁሉ አያስተውሉም፤ ጥበበኞች ግን ያስተውላሉ። 11ለጥፋት ርኵሰት ለመስጠት የዘወትሩ መሥዋዕት ከቀረ ጀምሮ፥ ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ቀን ይሆናል። 12የሚታገሥ፥ እስከ ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ አምስት ቀንም የሚደርስ ምስጉን ነው። 13አንተ ግን ሂድና እረፍ፤ ለፍጻሜው ገና ቀንና ዘመን አለ፤ በቀኑም መጨረሻ ትነሣለህ፤ በዕጣ ክፍልህም ትቆማለህ።”
Currently Selected:
ትንቢተ ዳንኤል 12: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ