ትን​ቢተ ዳን​ኤል 12

12
የዓ​ለም ፍጻሜ
1“በዚ​ያም ዘመን ስለ ሕዝ​ብህ ልጆች የሚ​ቆ​መው ታላቁ አለቃ ሚካ​ኤል ይነ​ሣል፤ ሕዝ​ብም በም​ድር ከተ​ፈ​ጠረ ጀምሮ እስ​ከ​ዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያል​ሆነ የመ​ከራ ዘመን ይሆ​ናል፤ በዚ​ያም ዘመን በመ​ጽ​ሐፉ ተጽፎ የተ​ገ​ኘው ሕዝ​ብህ ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ ይድ​ናል። 2በም​ድ​ርም ትቢያ ውስጥ ከአ​ን​ቀ​ላ​ፉት ብዙ​ዎች እኩ​ሌ​ቶቹ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት፥ እኩ​ሌ​ቶ​ቹም ለእ​ፍ​ረ​ትና ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጕስ​ቍ​ልና ይነ​ሣሉ። 3ጥበ​በ​ኞ​ቹም እንደ ሰማይ ፀዳል፥ ከጻ​ድ​ቃ​ንም ብዙ​ዎች#ዕብ. “ብዙ ሰዎ​ች​ንም ወደ ጽድቅ የሚ​መ​ልሱ” ይላል። እንደ ከዋ​ክ​ብት ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያበ​ራሉ። 4ዳን​ኤል ሆይ! አንተ ግን እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ ቃሉን ዝጋ፤ መጽ​ሐ​ፉ​ንም አትም፤ ብዙ ሰዎች ይመ​ረ​ም​ራሉ፤ እው​ቀ​ትም ይበ​ዛል።”
5እኔም ዳን​ኤል አየሁ፤ እነ​ሆም ሁለት ሌሎች ቆመው ነበር፤ አንዱ በዚህ በወ​ንዙ ዳር፥ ሌላ​ውም በዚያ በወ​ንዙ ዳር። 6አን​ዱም ከወ​ንዙ ውኃ በላይ የነ​በ​ረ​ውን በፍ​ታም የለ​በ​ሰ​ውን፥ “የዚህ ምል​ክት ፍጻሜ እስከ መቼ ነው?” አለው። 7ከወ​ን​ዙም ውኃ በላይ የነ​በ​ረው፥ በፍ​ታም የለ​በ​ሰው ሰው ቀኝና ግራ እጁን ወደ ሰማይ አን​ሥቶ፥ “ለዘ​መ​ንና ለዘ​መ​ናት፥ ለዘ​መ​ንም እኩ​ሌታ ነው ፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ሕዝብ ኀይል መበ​ተን በተ​ጨ​ረሰ ጊዜ ይህ ሁሉ ይፈ​ጸ​ማል” ብሎ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕያው ሆኖ በሚ​ኖ​ረው ሲምል ሰማሁ። 8ሰማ​ሁም፤ ነገር ግን አላ​ስ​ተ​ዋ​ል​ሁም፤ የዚ​ያን ጊዜም፥ “ጌታዬ ሆይ! የዚህ ሁሉ ፍጻሜ ምን​ድን ነው?” አልሁ። 9እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “ዳን​ኤል ሆይ! ቃሉ እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ የተ​ዘ​ጋና የታ​ተመ ነውና ሂድ፤ 10ብዙ ሰዎ​ችም ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን ያጠ​ራሉ፤ ያነ​ጡ​ማል፤ ይፈ​ተ​ኑ​ማል፤ ክፉ​ዎች ግን ክፋ​ትን ያደ​ር​ጋሉ፤ ክፉ​ዎ​ችም ሁሉ አያ​ስ​ተ​ው​ሉም፤ ጥበ​በ​ኞች ግን ያስ​ተ​ው​ላሉ። 11ለጥ​ፋት ርኵ​ሰት ለመ​ስ​ጠት የዘ​ወ​ትሩ መሥ​ዋ​ዕት ከቀረ ጀምሮ፥ ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ቀን ይሆ​ናል። 12የሚ​ታ​ገሥ፥ እስከ ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ አም​ስት ቀንም የሚ​ደ​ርስ ምስ​ጉን ነው። 13አንተ ግን ሂድና እረፍ፤ ለፍ​ጻ​ሜው ገና ቀንና ዘመን አለ፤ በቀ​ኑም መጨ​ረሻ ትነ​ሣ​ለህ፤ በዕጣ ክፍ​ል​ህም ትቆ​ማ​ለህ።”

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ