ትንቢተ ዳንኤል 14
14
ምዕራፍ 14
ዳንኤልና የቤል ካህናት
1ንጉሡ አስጢያጊስም ሞቶ በአባቶቹ መቃብር ከተቀበረ በኋላ የፋርሱ ንጉሥ ቂሮስ መንግሥቱን ያዘ። 2ዳንኤልም የንጉሡ እልፍኝ አሽከር ነበረ፤ ከጓደኞቹም ሁሉ እርሱ ይከብር ነበር።
3የባቢሎን ሰዎች የሚያመልኩት ስሙ ቤል የሚባል ጣዖት ነበር፤ ምግቡንም ሁልጊዜ ዐሥራ ሁለት ጫን በሚፈጅ ቻል ዐሥራ ሁለት መስፈሪያ ስንዴ፥ አርባ በግ፥ ስድስት ፊቀንም ወይን እያውጣጡ ይሰጡት ነበር። 4ንጉሡም ያመልከው ነበር፤ ሁልጊዜም ወደ እርሱ እየሄደ ይሰግድለት ነበር፤ ዳንኤል ግን ለፈጣሪው ይሰግድ ነበር። ንጉሡም ዳንኤልን፥ “ለቤል የማትሰግድ ለምንድን ነው?” አለው። 5ዳንኤልም ንጉሡን፥ “እኔስ ሰማይንና ምድርን የፈጠረ፥ ፍጥረትን ሁሉ የሚገዛ ሕያው አምላክን አመልካለሁ እንጂ የሰው እጅ የሠራው ጣዖትን አላመልክም” አለው።
6ንጉሡም፥ “ቤል ሕያው ያልሆነ አምላክ ይመስልሃልን? በየቀኑ እንደሚበላና እንደሚጠጣ አታይምን?” አለው። 7ዳንኤልም ሳቀና፥ “ንጉሥ ሆይ! አያስቱህ፤ ይህስ ውስጡ ጭቃ፥ ላዩም ናስ ነው፤ ፈጽሞም አይበላም፥ አይጠጣምም” አለው። 8ንጉሡም ተቈጣ፤ የቤልን ካህናት ጠርቶ፥ “ይህን የቤልን ምግብ ማን እንደሚበላው ካልነገራችሁኝ ትሞታላችሁ። 9ቤል እንደሚበላ ብታረጋግጡልኝ ግን ቤልን የፀረፈ ዳንኤል ይሞታል” አላቸው። ዳንኤልም ንጉሡን፥ “እንዳልኸው ይሁን” አለው።
10ከሴቶቻቸውና ከልጆቻቸው በቀር የቤል ካህናት ሰባ ይሆኑ ነበር፤ ዳንኤልና ንጉሡም ወደ ቤል ቤት ሄዱ። 11የቤል ካህናትም እንዲህ አሉ፥ “እነሆ እኛ ወደ ውጭ እንሄዳለን፤ ንጉሥ ሆይ! አንተም ማዕዱን ሥራ፤ ወይኑንም ቀድተህ አዘጋጅተህ አኑር፤ ደጃፉንም ዝጋ፤ በማኅተምህም አትመው። 12ሲነጋም ሂድ፤ ቤል ሁሉን ሳይበላ ቢገኝ እኛ እንሞታለን፤ ካልሆነ ግን በእኛ ላይ ሐሰትን የተናገረ ዳንኤል ይሞታል” አሉት። 13እነርሱ ግን የሚያደርጉትን ያውቁ ነበር፤ በማዕዱ በታች ስውር መግቢያ ነበራቸው፤ ሁልጊዜም በዚያ እየገቡ ይበሉ ነበር።
14እነርሱም ከወጡ በኋላ ንጉሡ ለቤል የሚበላውን አዘጋጀ፤ ዳንኤልም ብላቴናውን አመድ ያመጣ ዘንድ አዘዘው፤ በንጉሡ ፊት ብቻ በቤቱ ሁሉ ነሰነሰው፤ ከወጡም በኋላ ደጃፉን ዘግተው በንጉሡ ማኅተም አተሙት። 15እነርሱም ከሄዱ በኋላ የቤል ካህናት እንደ ልማዳቸው ከልጆቻቸውና ከሚስቶቻቸው ጋር በሌሊት ገብተው ሁሉንም በሉ፤ ጠጡም።
16ንጉሡና ዳንኤልም በማለዳ ሄዱ። 17ንጉሡም ዳንኤልን፥ “ማኅተሙ ደኅና ነውን?” አለው። ዳንኤልም፥ “ንጉሥ ሆይ፥ አወን ደኅና ነው” አለው። 18ከዚህም በኋላ ደጃፉን በከፈተ ጊዜ ንጉሡ ማዕዱን እንደ ጨረሱት አገኘ፤ በታላቅ ድምፅም ጮኸ፥ “ቤል ሆይ! አንተ ታላቅ ነህ፤ መታለልም የለብህም” አለ።
19ዳንኤልም ሳቀ፤ ንጉሡንም ያዘው፤ ወደ ውስጥም እንዳይገባ ከለከለው፤ “ወደ ምድር ተመልከት፤ ፍለጋውንም እይ፤ ይህ የምን ፍለጋ ነው?” አለው። 20ንጉሡም፥ “የወንዶችንና የሴቶችን፥ የልጆችንም ፍለጋ አያለሁ” አለ። ንጉሡም ተቈጣ። 21ያንጊዜም የቤልን ካህናት ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን ያዛቸው፤ በማዕዱም የተዘጋጀውን ይበሉና ይጠጡ ዘንድ የሚገቡበትን ስውር በር አሳዩት። 22ስለዚህም ንጉሡ ገደላቸው፥ ቤልንም ለዳንኤል ሰጠው፤ ዳንኤልም ሰባበረው፤ ቤቱንም አፈረሰው።
ዳንኤል ዘንዶውን እንደ ገደለ
23በዚያም ስፍራ የባቢሎን ሰዎች የሚያመልኩት ታላቅ ዘንዶ ነበር። 24ንጉሡም ዳንኤልን፥ “ይህንም ናስ ነው ትለዋለህን? እነሆ ሕያው ነው፤ ይበላል፤ ይጠጣልም፤ ሕያው አምላክ አይደለም ትለው ዘንድ አትችልም፤ ስለዚህ ስገድለት” አለው።
25ዳንኤልም “ለፈጣሪዬ ለእግዚአብሔር እሰግዳለሁ፤ እርሱ ሕያው አምላክ ነውና። 26ንጉሥ ሆይ! ይህን ዘንዶ ያለ ሰይፍና ያለ በትር እገድለው ዘንድ ፍቀድልኝ” አለው፤ ንጉሡም ዳንኤልን፥ “ፈቅጀልሃለሁ” አለው። 27ዳንኤልም አደሮማርና ጠጕር ስብም አምጥቶ በአንድነት ቀቀለው፤ ልህሉህም አደረገው፤ ለዘንዶውም በአፉ አጐረሰው፤ ዘንዶውም በጐረሰው ጊዜ ተሰንጥቆ ሞተ፤ ዳንኤልም፥ “አምላካችሁን እዩ” አላቸው።
28ከዚህ በኋላ የባቢሎን ሰዎች በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቈጡ፤ በንጉሡም ላይ ተነሡ፤ እንዲህም አሉ፥ “ንጉሥ ይሁዳዊ ሆነ፤ ቤልን ሰበረ፤ ካህናቱንም አረደ፤ ዘንዶውንም ገደለ።” 29ወደ ንጉሡም ሄዱ፤ እንዲህም አሉት፥ “ዳንኤልን ስጠን። ይህ ካልሆነ ግን ገንዘብህን እንዘርፋለን፤#“ገንዘብህን እንዘርፋለን” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። እንገድልሃለን፤ ቤትህንም በእሳት እናቃጥላለን” አሉት።
30ንጉሡም እጅግ እንዳስጨነቁት በአየ ጊዜ፥ ለንጉሡም ግዴታ በሆነበት ጊዜ ዳንኤልን አሳልፎ ሰጣቸው። 31እነርሱም ወደ አንበሶች ጕድጓድ ጣሉት፤ በዚያም ስድስት ቀን ተቀመጠ። 32በዚያም ሰባት አንበሶች ነበሩ። በየቀኑም ሁለት ሰውና ሁለት በግ ይመግቧቸው ነበር፤ ያንጊዜ ግን ዳንኤልን እንዲበሉት ምንም አልሰጧቸውም ነበር።
33ነቢዩ ዕንባቆምም በይሁዳ ነበር፤ የምስር ንፍሮም አስቀቀለ፤ እንጀራም አስጋገረ፤ በቅርጫትም አድርጎ እህል ለሚያጭዱ ሰዎች ይዞ ወደ እርሻ ሄደ። 34የእግዚአብሔርም መልአክ ዕንባቆምን፥ “ይህን ምሳ በባቢሎን በአንበሶች ጕድጓድ ላለው ለዳንኤል ውሰድ” አለው።
35ዕንባቆምም፥ “አቤቱ! ባቢሎንን አላየሁም፤ የአንበሶችም ጕድጓድ ወዴት እንደ ሆነ አላውቅም” አለው። 36የእግዚአብሔርም መልአክ በራሱ ጠጕር ተሸክሞ በመንፈስ ቅዱስ ኀይል በባቢሎን ወደ አለው ወደ አንበሶች ጕድጓድ አደረሰው። 37ዕንባቆምም እንዲህ ብሎ ጮኸ፥ “ዳንኤል! ዳንኤል! እግዚአብሔር የላከልህን ይህን ምሳ ተቀበል” አለ። 38ዳንኤልም፥ “ወዳጆቹን የማይዘነጋቸው እግዚአብሔር አሰበኝን?” አለ። 39ዳንኤልም ተነሥቶ በላ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ ዕንባቆምን ወዲያውኑ ወደ ሀገሩ መለሰው።
40ንጉሡም በሰባተኛዪቱ ቀን መጥቶ ለዳንኤል አለቀሰለት፤ ወደ አንበሶቹም ጕድጓድ በቀረበ ጊዜ ዳንኤልን በአንበሶቹ መካከል ተቀምጦ አየው። 41ንጉሡም በታላቅ ቃል ጮኸ፤ እንዲህም አለ፥ “የዳንኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ታላቅ ነህ፤ ያለ አንተም ሌላ አምላክ የለም” አለ። 42ዳንኤልንም ያንጊዜ ከአንበሶቹ ጕድጓድ አወጣው። ዳንኤልን ይገድሉት ዘንድ የወደዱ እነዚያንም ሰዎች ይዘው በአንበሶች ጕድጓድ ጣሏቸው፤ አንበሶቹም ወዲያውኑ በፊቱ በሉአቸው።
# ቀጣዩ ከምዕ. 6 ቍ. 27 የመጣ ነው። ያንጊዜም ንጉሡ፥ “የሚያድን እርሱ ነውና በሰማይና በምድርም ምልክትንና ድንቅ ሥራን ያደርጋልና፥ ዳንኤልንም ከአንበሶች አፍ አድኖታልና ሁሉም የዳንኤልን አምላክ ያምልኩት” አለ።
Currently Selected:
ትንቢተ ዳንኤል 14: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ