የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ዳን​ኤል 14

14
ምዕ​ራፍ 14
ዳን​ኤ​ልና የቤል ካህ​ናት
1ንጉሡ አስ​ጢ​ያ​ጊ​ስም ሞቶ በአ​ባ​ቶቹ መቃ​ብር ከተ​ቀ​በረ በኋላ የፋ​ርሱ ንጉሥ ቂሮስ መን​ግ​ሥ​ቱን ያዘ። 2ዳን​ኤ​ልም የን​ጉሡ እል​ፍኝ አሽ​ከር ነበረ፤ ከጓ​ደ​ኞ​ቹም ሁሉ እርሱ ይከ​ብር ነበር።
3የባ​ቢ​ሎን ሰዎች የሚ​ያ​መ​ል​ኩት ስሙ ቤል የሚ​ባል ጣዖት ነበር፤ ምግ​ቡ​ንም ሁል​ጊዜ ዐሥራ ሁለት ጫን በሚ​ፈጅ ቻል ዐሥራ ሁለት መስ​ፈ​ሪያ ስንዴ፥ አርባ በግ፥ ስድ​ስት ፊቀ​ንም ወይን እያ​ው​ጣጡ ይሰ​ጡት ነበር። 4ንጉ​ሡም ያመ​ል​ከው ነበር፤ ሁል​ጊ​ዜም ወደ እርሱ እየ​ሄደ ይሰ​ግ​ድ​ለት ነበር፤ ዳን​ኤል ግን ለፈ​ጣ​ሪው ይሰ​ግድ ነበር። ንጉ​ሡም ዳን​ኤ​ልን፥ “ለቤል የማ​ት​ሰ​ግድ ለም​ን​ድን ነው?” አለው። 5ዳን​ኤ​ልም ንጉ​ሡን፥ “እኔስ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን የፈ​ጠረ፥ ፍጥ​ረ​ትን ሁሉ የሚ​ገዛ ሕያው አም​ላ​ክን አመ​ል​ካ​ለሁ እንጂ የሰው እጅ የሠ​ራው ጣዖ​ትን አላ​መ​ል​ክም” አለው።
6ንጉ​ሡም፥ “ቤል ሕያው ያል​ሆነ አም​ላክ ይመ​ስ​ል​ሃ​ልን? በየ​ቀኑ እን​ደ​ሚ​በ​ላና እን​ደ​ሚ​ጠጣ አታ​ይ​ምን?” አለው። 7ዳን​ኤ​ልም ሳቀና፥ “ንጉሥ ሆይ! አያ​ስ​ቱህ፤ ይህስ ውስጡ ጭቃ፥ ላዩም ናስ ነው፤ ፈጽ​ሞም አይ​በ​ላም፥ አይ​ጠ​ጣ​ምም” አለው። 8ንጉ​ሡም ተቈጣ፤ የቤ​ልን ካህ​ናት ጠርቶ፥ “ይህን የቤ​ልን ምግብ ማን እን​ደ​ሚ​በ​ላው ካል​ነ​ገ​ራ​ች​ሁኝ ትሞ​ታ​ላ​ችሁ። 9ቤል እን​ደ​ሚ​በላ ብታ​ረ​ጋ​ግ​ጡ​ልኝ ግን ቤልን የፀ​ረፈ ዳን​ኤል ይሞ​ታል” አላ​ቸው። ዳን​ኤ​ልም ንጉ​ሡን፥ “እን​ዳ​ል​ኸው ይሁን” አለው።
10ከሴ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ከል​ጆ​ቻ​ቸው በቀር የቤል ካህ​ናት ሰባ ይሆኑ ነበር፤ ዳን​ኤ​ልና ንጉ​ሡም ወደ ቤል ቤት ሄዱ። 11የቤል ካህ​ና​ትም እን​ዲህ አሉ፥ “እነሆ እኛ ወደ ውጭ እን​ሄ​ዳ​ለን፤ ንጉሥ ሆይ! አን​ተም ማዕ​ዱን ሥራ፤ ወይ​ኑ​ንም ቀድ​ተህ አዘ​ጋ​ጅ​ተህ አኑር፤ ደጃ​ፉ​ንም ዝጋ፤ በማ​ኅ​ተ​ም​ህም አት​መው። 12ሲነ​ጋም ሂድ፤ ቤል ሁሉን ሳይ​በላ ቢገኝ እኛ እን​ሞ​ታ​ለን፤ ካል​ሆነ ግን በእኛ ላይ ሐሰ​ትን የተ​ና​ገረ ዳን​ኤል ይሞ​ታል” አሉት። 13እነ​ርሱ ግን የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ያውቁ ነበር፤ በማ​ዕዱ በታች ስውር መግ​ቢያ ነበ​ራ​ቸው፤ ሁል​ጊ​ዜም በዚያ እየ​ገቡ ይበሉ ነበር።
14እነ​ር​ሱም ከወጡ በኋላ ንጉሡ ለቤል የሚ​በ​ላ​ውን አዘ​ጋጀ፤ ዳን​ኤ​ልም ብላ​ቴ​ና​ውን አመድ ያመጣ ዘንድ አዘ​ዘው፤ በን​ጉሡ ፊት ብቻ በቤቱ ሁሉ ነሰ​ነ​ሰው፤ ከወ​ጡም በኋላ ደጃ​ፉን ዘግ​ተው በን​ጉሡ ማኅ​ተም አተ​ሙት። 15እነ​ር​ሱም ከሄዱ በኋላ የቤል ካህ​ናት እንደ ልማ​ዳ​ቸው ከል​ጆ​ቻ​ቸ​ውና ከሚ​ስ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር በሌ​ሊት ገብ​ተው ሁሉ​ንም በሉ፤ ጠጡም።
16ንጉ​ሡና ዳን​ኤ​ልም በማ​ለዳ ሄዱ። 17ንጉ​ሡም ዳን​ኤ​ልን፥ “ማኅ​ተሙ ደኅና ነውን?” አለው። ዳን​ኤ​ልም፥ “ንጉሥ ሆይ፥ አወን ደኅና ነው” አለው። 18ከዚ​ህም በኋላ ደጃ​ፉን በከ​ፈተ ጊዜ ንጉሡ ማዕ​ዱን እንደ ጨረ​ሱት አገኘ፤ በታ​ላቅ ድም​ፅም ጮኸ፥ “ቤል ሆይ! አንተ ታላቅ ነህ፤ መታ​ለ​ልም የለ​ብ​ህም” አለ።
19ዳን​ኤ​ልም ሳቀ፤ ንጉ​ሡ​ንም ያዘው፤ ወደ ውስ​ጥም እን​ዳ​ይ​ገባ ከለ​ከ​ለው፤ “ወደ ምድር ተመ​ል​ከት፤ ፍለ​ጋ​ው​ንም እይ፤ ይህ የምን ፍለጋ ነው?” አለው። 20ንጉ​ሡም፥ “የወ​ን​ዶ​ች​ንና የሴ​ቶ​ችን፥ የል​ጆ​ች​ንም ፍለጋ አያ​ለሁ” አለ። ንጉ​ሡም ተቈጣ። 21ያን​ጊ​ዜም የቤ​ልን ካህ​ናት ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ያዛ​ቸው፤ በማ​ዕ​ዱም የተ​ዘ​ጋ​ጀ​ውን ይበ​ሉና ይጠጡ ዘንድ የሚ​ገ​ቡ​በ​ትን ስውር በር አሳ​ዩት። 22ስለ​ዚ​ህም ንጉሡ ገደ​ላ​ቸው፥ ቤል​ንም ለዳ​ን​ኤል ሰጠው፤ ዳን​ኤ​ልም ሰባ​በ​ረው፤ ቤቱ​ንም አፈ​ረ​ሰው።
ዳን​ኤል ዘን​ዶ​ውን እንደ ገደለ
23በዚ​ያም ስፍራ የባ​ቢ​ሎን ሰዎች የሚ​ያ​መ​ል​ኩት ታላቅ ዘንዶ ነበር። 24ንጉ​ሡም ዳን​ኤ​ልን፥ “ይህ​ንም ናስ ነው ትለ​ዋ​ለ​ህን? እነሆ ሕያው ነው፤ ይበ​ላል፤ ይጠ​ጣ​ልም፤ ሕያው አም​ላክ አይ​ደ​ለም ትለው ዘንድ አት​ች​ልም፤ ስለ​ዚህ ስገ​ድ​ለት” አለው።
25ዳን​ኤ​ልም “ለፈ​ጣ​ሪዬ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሰ​ግ​ዳ​ለሁ፤ እርሱ ሕያው አም​ላክ ነውና። 26ንጉሥ ሆይ! ይህን ዘንዶ ያለ ሰይ​ፍና ያለ በትር እገ​ድ​ለው ዘንድ ፍቀ​ድ​ልኝ” አለው፤ ንጉ​ሡም ዳን​ኤ​ልን፥ “ፈቅ​ጀ​ል​ሃ​ለሁ” አለው። 27ዳን​ኤ​ልም አደ​ሮ​ማ​ርና ጠጕር ስብም አም​ጥቶ በአ​ን​ድ​ነት ቀቀ​ለው፤ ልህ​ሉ​ህም አደ​ረ​ገው፤ ለዘ​ን​ዶ​ውም በአፉ አጐ​ረ​ሰው፤ ዘን​ዶ​ውም በጐ​ረ​ሰው ጊዜ ተሰ​ን​ጥቆ ሞተ፤ ዳን​ኤ​ልም፥ “አም​ላ​ካ​ች​ሁን እዩ” አላ​ቸው።
28ከዚህ በኋላ የባ​ቢ​ሎን ሰዎች በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቈጡ፤ በን​ጉ​ሡም ላይ ተነሡ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ንጉሥ ይሁ​ዳዊ ሆነ፤ ቤልን ሰበረ፤ ካህ​ና​ቱ​ንም አረደ፤ ዘን​ዶ​ው​ንም ገደለ።” 29ወደ ንጉ​ሡም ሄዱ፤ እን​ዲ​ህም አሉት፥ “ዳን​ኤ​ልን ስጠን። ይህ ካል​ሆነ ግን ገን​ዘ​ብ​ህን እን​ዘ​ር​ፋ​ለን፤#“ገን​ዘ​ብ​ህን እን​ዘ​ር​ፋ​ለን” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። እን​ገ​ድ​ል​ሃ​ለን፤ ቤት​ህ​ንም በእ​ሳት እና​ቃ​ጥ​ላ​ለን” አሉት።
30ንጉ​ሡም እጅግ እን​ዳ​ስ​ጨ​ነ​ቁት በአየ ጊዜ፥ ለን​ጉ​ሡም ግዴታ በሆ​ነ​በት ጊዜ ዳን​ኤ​ልን አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው። 31እነ​ር​ሱም ወደ አን​በ​ሶች ጕድ​ጓድ ጣሉት፤ በዚ​ያም ስድ​ስት ቀን ተቀ​መጠ። 32በዚ​ያም ሰባት አን​በ​ሶች ነበሩ። በየ​ቀ​ኑም ሁለት ሰውና ሁለት በግ ይመ​ግ​ቧ​ቸው ነበር፤ ያን​ጊዜ ግን ዳን​ኤ​ልን እን​ዲ​በ​ሉት ምንም አል​ሰ​ጧ​ቸ​ውም ነበር።
33ነቢዩ ዕን​ባ​ቆ​ምም በይ​ሁዳ ነበር፤ የም​ስር ንፍ​ሮም አስ​ቀ​ቀለ፤ እን​ጀ​ራም አስ​ጋ​ገረ፤ በቅ​ር​ጫ​ትም አድ​ርጎ እህል ለሚ​ያ​ጭዱ ሰዎች ይዞ ወደ እርሻ ሄደ። 34የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ዕን​ባ​ቆ​ምን፥ “ይህን ምሳ በባ​ቢ​ሎን በአ​ን​በ​ሶች ጕድ​ጓድ ላለው ለዳ​ን​ኤል ውሰድ” አለው።
35ዕን​ባ​ቆ​ምም፥ “አቤቱ! ባቢ​ሎ​ንን አላ​የ​ሁም፤ የአ​ን​በ​ሶ​ችም ጕድ​ጓድ ወዴት እንደ ሆነ አላ​ው​ቅም” አለው። 36የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ በራሱ ጠጕር ተሸ​ክሞ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ኀይል በባ​ቢ​ሎን ወደ አለው ወደ አን​በ​ሶች ጕድ​ጓድ አደ​ረ​ሰው። 37ዕን​ባ​ቆ​ምም እን​ዲህ ብሎ ጮኸ፥ “ዳን​ኤል! ዳን​ኤል! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የላ​ከ​ል​ህን ይህን ምሳ ተቀ​በል” አለ። 38ዳን​ኤ​ልም፥ “ወዳ​ጆ​ቹን የማ​ይ​ዘ​ነ​ጋ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሰ​በ​ኝን?” አለ። 39ዳን​ኤ​ልም ተነ​ሥቶ በላ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ዕን​ባ​ቆ​ምን ወዲ​ያ​ውኑ ወደ ሀገሩ መለ​ሰው።
40ንጉ​ሡም በሰ​ባ​ተ​ኛ​ዪቱ ቀን መጥቶ ለዳ​ን​ኤል አለ​ቀ​ሰ​ለት፤ ወደ አን​በ​ሶ​ቹም ጕድ​ጓድ በቀ​ረበ ጊዜ ዳን​ኤ​ልን በአ​ን​በ​ሶቹ መካ​ከል ተቀ​ምጦ አየው። 41ንጉ​ሡም በታ​ላቅ ቃል ጮኸ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “የዳ​ን​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! አንተ ታላቅ ነህ፤ ያለ አን​ተም ሌላ አም​ላክ የለም” አለ። 42ዳን​ኤ​ል​ንም ያን​ጊዜ ከአ​ን​በ​ሶቹ ጕድ​ጓድ አወ​ጣው። ዳን​ኤ​ልን ይገ​ድ​ሉት ዘንድ የወ​ደዱ እነ​ዚ​ያ​ንም ሰዎች ይዘው በአ​ን​በ​ሶች ጕድ​ጓድ ጣሏ​ቸው፤ አን​በ​ሶ​ቹም ወዲ​ያ​ውኑ በፊቱ በሉ​አ​ቸው።
# ቀጣዩ ከምዕ. 6 ቍ. 27 የመጣ ነው። ያን​ጊ​ዜም ንጉሡ፥ “የሚ​ያ​ድን እርሱ ነውና በሰ​ማ​ይና በም​ድ​ርም ምል​ክ​ት​ንና ድንቅ ሥራን ያደ​ር​ጋ​ልና፥ ዳን​ኤ​ል​ንም ከአ​ን​በ​ሶች አፍ አድ​ኖ​ታ​ልና ሁሉም የዳ​ን​ኤ​ልን አም​ላክ ያም​ል​ኩት” አለ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ