ትንቢተ ዳንኤል 6
6
በዳንኤል ላይ የተደረገ ሤራ
1ዳርዮስም በመንግሥቱ ሁሉ ዘንድ እንዲሆኑ መቶ ሃያ መሳፍንትን በመንግሥቱ ላይ ይሾም ዘንድ ወደደ። 2መሳፍንቱም ግብሩን ያመጡላቸው ዘንድ፥ ንጉሡም በማንኛውም እንዳይቸገር ሦስት አለቆች በላያቸው አደረገ፤ ከእነርሱም አንደኛው ዳንኤል ነበረ። 3ዳንኤልም መልካም መንፈስ ስለ አለው ከአለቆችና ከመሳፍንት በለጠ፤ ንጉሡም በመንግሥቱ ሁሉ ላይ ሾመው።
4ያን ጊዜም አለቆችና መሳፍንቱ ስለ መንግሥቱ#“ስለ መንግሥቱ” የሚለው በዕብ. ብቻ። በዳንኤል ላይ ምክንያት ይፈልጉ ነበር፤ ነገር ግን የታመነ ነበረና፥ ምንም በደል አልተገኘበትምና በእርሱ ላይ ሰበብና በደል ያገኙበት ዘንድ አልቻሉም።#“በእርሱ ላይ ሰበብና በደል ሊያገኙበት አልቻሉም” የሚለው በዕብ. ብቻ። 5እነዚያም ሰዎች፥ “ከአምላኩ ሕግ በቀር በዚህ በዳንኤል ላይ ሌላ ምክንያት አናገኝበትም” አሉ።
6ያን ጊዜም ሹሞቹና መኳንንቱ ወደ ንጉሡ ተሰብስበው እንዲህ አሉት፥ “ንጉሥ ዳርዮስ ሆይ! ለዘለዓለም ኑር። 7የመንግሥቱ አለቆች ሁሉ ሹሞችና መሳፍንት፥ አማካሪዎችና አዛዦች፦ ንጉሥ ሆይ! ከአንተ በቀር ማንም እስከ ሠላሳ ቀን ድረስ ልመና ከአምላክ ወይም ከሰው ቢለምን፥ በአንበሶች ጕድጓድ ውስጥ ይጣል የሚል የንጉሥ ሕግና ብርቱ ትእዛዝ ይወጣ ዘንድ ተማከሩ። 8አሁንም ንጉሥ ሆይ! እንደማይለወጠው እንደ ሜዶንና እንደ ፋርስ ሕግ እንዳይለወጥ ትእዛዙን አጽና፤ ጽሕፈቱንም ጻፍ።” 9ያን ጊዜም ንጉሡ ዳርዮስ ይህን ሥርዐት ይጽፉ ዘንድ አዘዘ።
ዳንኤል በአንበሳ ጕድጓድ እንደ ተጣለ
10ዳንኤልም ይህ ሥርዐት እንደ ታዘዘ በዐወቀ ጊዜ ወደ ቤቱ ገባ፤ የእልፍኙም መስኮቶች ወደ ኢየሩሳሌም አንጻር ተከፍተው ነበር፤ ቀድሞም ያደርግ እንደ ነበረ ከቀኑ በሦስት ሰዓት በጕልበቱ ተንበርክኮ በአምላኩ ፊት ጸለየ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በየዕለቱ ሦስት ጊዜ ...” ይላል። አመሰገነም። 11እነዚያም ሰዎች በማንኛውም ነገር ዘወትር ይመለከቱት ነበርና ዳንኤል በአምላኩ ፊት ሲጸልይና ሲለምን አገኙት። 12ወደ ንጉሡም ቀርበው ስለ ንጉሡ ትእዛዝ፥ “ንጉሥ ሆይ! ከአንተ በቀር እስከ ሠላሳ ቀን ድረስ ከአምላክ ወይም ከሰው የሚለምን ሰው ሁሉ በአንበሶች ጕድጓድ ውስጥ እንዲጣል ትእዛዝ አልጻፍህምን?” አሉት። ንጉሡም መልሶ፥ “ነገሩ እንደማይለወጠው እንደ ሜዶንና እንደ ፋርስ ሕግ እውነት ነው” አላቸው። 13የዚያን ጊዜም በንጉሡ ፊት መልሰው፥ “ንጉሥ ሆይ! ከይሁዳ የምርኮ ልጆች የሆነው ዳንኤል ከቀኑ በሦስት ሰዓት#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “በየዕለቱ ሦስት ጊዜ” ይላል። ልመናውን ይለምናል እንጂ አንተንና የጻፍኸውን ትእዛዝ አይቀበልም” አሉት። 14ንጉሡም ይህን ቃል በሰማ ጊዜ በጣም አዘነ፤ ያድነውም ዘንድ ልቡን ወደ ዳንኤል አደረገ፤ ሊያድነውም ፀሐይ እስኪገባ ድረስ ደከመ። 15ያን ጊዜም እነዚያ ሰዎች ወደ ንጉሡ ተሰብስበው ንጉሡን፥ “ንጉሥ ሆይ! ንጉሡ ያጸናው ትእዛዝ ወይም ሥርዐት ይለወጥ ዘንድ እንዳይገባ የሜዶንና የፋርስ ሕግ እንደ ሆነ ዕወቅ” አሉት። 16ያን ጊዜም ዳንኤልን አምጥተው በአንበሶች ጕድጓድ ይጥሉት ዘንድ ንጉሡ አዘዘ፤ ንጉሡም ዳንኤልን፥ “ሁልጊዜ የምታመልከው አምላክህ እርሱ ያድንህ” አለው። 17ድንጋይም አምጥተው በጕድጓዱ አፍ ላይ ገጠሙበት፤ ንጉሡም በዳንኤል ላይ የሚተነኳኰል ሰው እንዳይኖር#ዕብ. “የተደረገው እንዳይለወጥ” ይላል። በቀለበቱና በመኳንንቱ ቀለበት አተመው። 18ንጉሡም ወደ ቤቱ ሄደ፤ ሳይበላም ተኛ፤ የሚበላውም አላመጡለትም፤ እንቅልፉም ከእርሱ ራቀ። እግዚአብሔርም የአንበሶቹን አፍ ዘጋ፤ ዳንኤልንም አልቧጨሩትም።#“እግዚአብሔርም የአንበሶችን አፍ ዘጋ፥ ዳንኤልንም አልቧጨሩትም” የሚለው በግእዝ ብቻ።
ዳንኤል ከአንበሶች አፍ እንደ ዳነ
19በነጋውም ንጉሡ ማልዶ ተነሣ፤ ፈጥኖም ወደ አንበሶች ጕድጓድ ሄደ። 20ወደ ጕድጓዱም በቀረበ ጊዜ በታላቅ ቃል ጮኸ፤ ንጉሡም ዳንኤልን፥ “የሕያው አምላክ ባሪያ ዳንኤል ሆይ! ሁልጊዜ የምታመልከው አምላክህ ከአንበሶች አፍ ያድንህ ዘንድ ችሎአልን?” አለው። 21ዳንኤልም ንጉሡን፥ “ንጉሥ ሆይ! ለዘለዓለም ኑር። 22በፊቱ ቅንነት ተገኝቶብኛልና፥ በአንተም ፊት ደግሞ፤ ንጉሥ ሆይ! አልበደልሁምና አምላኬ መልአኩን ልኮ የአንበሶችን አፍ ዘጋ፤ እነርሱም አልቧጨሩኝም” አለው። 23ያን ጊዜም ንጉሡ እጅግ ደስ አለው፤ ዳንኤልንም ከጕድጓዱ ያወጡት ዘንድ አዘዘ፤ ዳንኤልም ከጕድጓዱ ወጣ፤ በአምላኩም ታምኖ ነበርና አንዳች ጕዳት አልተገኘበትም።
24ንጉሡም ዳንኤልን የከሰሱ እነዚያን ሰዎች ያመጡአቸው ዘንድ አዘዘ፤ እነርሱንና ልጆቻቸውንም፥ ሚስቶቻቸውንም በአንበሶች ጕድጓድ ጣሉአቸው፤ ወደ ጕድጓዱም መጨረሻ ሳይደርሱ አንበሶች ያዙአቸው፤ አጥንታቸውንም ሁሉ ሰባበሩ።
25ያን ጊዜም ንጉሥ ዳርዮስ በምድር ሁሉ ላይ ወደሚኖሩ ወገኖችና አሕዛብ፥ በልዩ ልዩም ቋንቋ ወደሚናገሩ ሁሉ ጻፈ፤ እንዲህም አለ፥ “ሰላም ይብዛላችሁ። 26በመንግሥቴ ግዛት ሁሉ ያሉ ሰዎች በዳንኤል አምላክ ፊት እንዲፈሩና እንዲንቀጠቀጡ አዝዣለሁ፤ እርሱ ሕያው አምላክ ለዘለዓለም የሚኖር ነውና፤ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው፥ ግዛቱም ለዘለዓለም ይኖራል። 27ያድናል፤ ይታደግማል፤ በሰማይና በምድርም ተአምራትንና ድንቅን ይሠራል፤ ዳንኤልንም ከአንበሶች አፍ አድኖታል።”
28ይህም ዳንኤል በዳርዮስ መንግሥትና በፋርሳዊው በቂሮስ መንግሥት ከፍ ከፍ አለ።
Currently Selected:
ትንቢተ ዳንኤል 6: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ