ትን​ቢተ ዳን​ኤል 5

5
ብል​ጣ​ሶር ለመ​ኳ​ን​ንቱ ግብር እንደ አበላ
1ንጉሡ ብል​ጣ​ሶር ለሺህ መኳ​ን​ንቱ ትልቅ ግብዣ አደ​ረገ፤ ለሺ​ሁም የወ​ይን ጠጅ ያጠጣ ነበር። 2ብል​ጣ​ሶ​ርም የወ​ይን ጠጅ በጠጣ ጊዜ ንጉ​ሡና መኳ​ን​ንቱ፥ ሚስ​ቶ​ቹና ቁባ​ቶቹ ይጠ​ጡ​ባ​ቸው ዘንድ፥ “አባቴ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከነ​በ​ረው ቤተ መቅ​ደስ ያመ​ጣ​ቸ​ውን የወ​ር​ቁ​ንና የብ​ሩን ዕቃ​ዎች አምጡ” ብሎ አዘዘ። 3ያን ጊዜም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከነ​በ​ረው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ መቅ​ደስ የመ​ጡ​ትን የወ​ር​ቁ​ንና የብ​ሩን ዕቃ​ዎች አመጡ፤ ንጉ​ሡና መኳ​ን​ን​ቱም፥ ሚስ​ቶ​ቹና ቁባ​ቶ​ቹም ጠጡ​ባ​ቸው። 4የወ​ይን ጠጅም እየ​ጠጡ ከወ​ር​ቅና ከብር፥ ከና​ስና ከብ​ረት፥ ከእ​ን​ጨ​ትና ከድ​ን​ጋይ የተ​ሠ​ሩ​ትን አማ​ል​ክት አመ​ሰ​ገኑ።
5በዚ​ያም ሰዓት የሰው እጅ ጣት ወጥታ በን​ጉሡ ቤት በተ​ለ​ሰ​ነው ግንብ ላይ በመ​ቅ​ረዙ አን​ጻር ጻፈች፤ ንጉ​ሡም የሰው ጣት ስት​ጽፍ አየ። 6ያን ጊዜም የን​ጉሡ ፊት ተለ​ወጠ፤ ልቡም ታወከ፤ የወ​ገ​ቡም ጅማ​ቶች ተፈቱ፤ ጕል​በ​ቶ​ቹም ተብ​ረ​ከ​ረኩ። 7ንጉ​ሡም አስ​ማ​ተ​ኞ​ቹ​ንና ከለ​ዳ​ው​ያ​ኑን፥ ቃላ​ተ​ኞ​ቹ​ንም ያገቡ ዘንድ በታ​ላቅ ድምፅ ጮኸ፤ ንጉ​ሡም የባ​ቢ​ሎ​ንን ጠቢ​ባን፥ “ይህን ጽሕ​ፈት ያነ​በበ፥ ፍቺ​ው​ንም የነ​ገ​ረኝ ሐም​ራዊ ግምጃ ይለ​ብ​ሳል፤ የወ​ር​ቅም ማርዳ በአ​ን​ገቱ አስ​ር​ለ​ታ​ለሁ፤ በመ​ን​ግ​ሥ​ቴም ላይ ሦስ​ተኛ ገዥ አድ​ርጌ እሾ​መ​ዋ​ለሁ” ብሎ ተና​ገረ። 8የዚ​ያን ጊዜም የን​ጉሡ ጠቢ​ባን ሁሉ ገቡ፤ ነገር ግን ጽሕ​ፈ​ቱን ያነ​ብቡ ዘንድ፥ ፍቺ​ው​ንም ለን​ጉሡ ይነ​ግሩ ዘንድ አል​ቻ​ሉም። 9ንጉ​ሡም ብል​ጣ​ሶር እጅግ ደነ​ገጠ፤ ፊቱም ተለ​ወ​ጠ​በት፤ መኳ​ን​ን​ቱም ተደ​ና​ገጡ።
10ንግ​ሥ​ቲ​ቱም የን​ጉ​ሡ​ንና የመ​ኳ​ን​ን​ቱን ቃል#“የን​ጉ​ሡ​ንና የመ​ኳ​ን​ን​ቱን ቃል” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። ሰምታ ወደ ግብዣ ቤት ገባች፤ እን​ዲ​ህም አለች፥ “ንጉሥ ሆይ! ለዘ​ለ​ዓ​ለም ኑር፤ አሳ​ብህ አያ​ስ​ቸ​ግ​ርህ፤ ፊት​ህም አይ​ለ​ወጥ። 11የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ መን​ፈስ ያለ​በት ሰው በመ​ን​ግ​ሥ​ትህ ውስጥ አለ፤ በአ​ባ​ት​ህም ዘመን እንደ አማ​ል​ክት ጥበብ ያለ ጥበ​ብና ማስ​ተ​ዋል፥ ዕው​ቀ​ትም ተገ​ኘ​በት፤ አባ​ትህ ንጉሡ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር የሕ​ልም ተር​ጓ​ሚ​ዎ​ችና የአ​ስ​ማ​ተ​ኞች፥ የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንና የቃ​ላ​ተ​ኞች አለቃ አድ​ርጎ ሾመው። 12መል​ካም መን​ፈስ፥ ዕው​ቀ​ትም፥ ማስ​ተ​ዋ​ልም፥ ሕል​ም​ንም መተ​ር​ጐም፥ እን​ቆ​ቅ​ል​ሽ​ንም መግ​ለጥ፥ የታ​ተ​መ​ው​ንም መፍ​ታት በእ​ርሱ ተገ​ኝ​ቶ​አ​ልና፤ እር​ሱም ንጉሡ ስሙን ብል​ጣ​ሶር ብሎ የሰ​የ​መው ዳን​ኤል ነው። አሁ​ንም እርሱ ይጠራ፤ እር​ሱም ፍቺ​ውን ይነ​ግ​ር​ሃል።”
13የዚ​ያን ጊዜም ዳን​ኤል ወደ ንጉሡ ፊት ገባ፤ ንጉ​ሡም ተና​ገ​ረው፤ ዳን​ኤ​ል​ንም እን​ዲህ አለው፥ “ንጉሡ አባቴ ከይ​ሁዳ ከማ​ረ​ካ​ቸው ከይ​ሁዳ ምር​ኮ​ኞች ልጆች የሆ​ንህ ዳን​ኤል አንተ ነህን? 14የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ መን​ፈስ እንደ አለ​ብህ፥ ዕው​ቀ​ትና ማስ​ተ​ዋ​ልም፥ ሕል​ም​ንም መተ​ር​ጐም እንደ ተገ​ኘ​ብህ ስለ አንተ ሰም​ቻ​ለሁ። 15አሁ​ንም ይህን ጽሕ​ፈት ያነ​ብቡ ዘንድ፥ ፍቺ​ው​ንም ይነ​ግ​ሩኝ ዘንድ ጠን​ቋ​ዮ​ችና ፈላ​ስ​ፎች፥ ጠቢ​ባ​ንና ሟር​ተ​ኞ​ችም ወደ እኔ ገብ​ተው ነበር፤ ነገር ግን የነ​ገ​ሩን ፍቺ ይነ​ግ​ሩኝ ዘንድ አል​ቻ​ሉም። 16አንተ ግን ፍቺን ትሰጥ ዘንድ፥ የታ​ተ​መ​ው​ንም ትፈታ ዘንድ እን​ድ​ት​ችል ሰም​ቻ​ለሁ፤ አሁ​ንም ጽሕ​ፈ​ቱን ታነ​ብብ ዘንድ፥ ፍቺ​ው​ንም ትነ​ግ​ረኝ ዘንድ ብት​ችል፥ ሐም​ራዊ ግምጃ ትለ​ብ​ሳ​ለህ፤ የወ​ር​ቅም ማርዳ በአ​ን​ገ​ትህ ዙሪያ አስ​ር​ል​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም በመ​ን​ግ​ሥቴ ላይ ሦስ​ተኛ ገዥ ትሆ​ና​ለህ።” 17የዚ​ያን ጊዜም ዳን​ኤል መለሰ፤ በን​ጉ​ሡም ፊት እን​ዲህ አለ፥ “ስጦ​ታህ ለአ​ንተ ይሁን፤ የመ​ን​ግ​ሥ​ት​ህ​ንም ሢሶ ለሌላ ስጥ፤ ነገር ግን ጽሕ​ፈ​ቱን ለን​ጉሡ አነ​ብ​ባ​ለሁ፤ ፍቺ​ው​ንም እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ። 18ንጉሥ ሆይ! ልዑል አም​ላክ ለአ​ባ​ትህ ለና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር መን​ግ​ሥ​ት​ንና ታላ​ቅ​ነ​ትን፥ ክብ​ር​ንና ግር​ማን ሰጠው። 19ስለ ሰጠው ታላ​ቅ​ነት ወገ​ኖ​ችና አሕ​ዛብ፥ በልዩ ልዩም ቋንቋ የሚ​ና​ገሩ ሁሉ በፊቱ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጡና ይፈሩ ነበር፤ የፈ​ቀ​ደ​ውን ይገ​ድል፥ የፈ​ቀ​ደ​ው​ንም በሕ​ይ​ወት ያኖር ነበር፤ የፈ​ቀ​ደ​ው​ንም ያነሣ፥ የፈ​ቀ​ደ​ው​ንም ያዋ​ርድ ነበር። 20ልቡ ግን በታ​በየ ጊዜ፥ በኵ​ራ​ትም ያደ​ርግ ዘንድ መን​ፈሱ በጠ​ነ​ከረ ጊዜ፥ ከመ​ን​ግ​ሥቱ ዙፋን ተዋ​ረደ፤ ክብ​ሩም ተለ​የው። 21ልዑል አም​ላ​ክም የሰ​ዎ​ችን መን​ግ​ሥት እን​ዲ​ገዛ፥ ለሚ​ወ​ድ​ደ​ውም እን​ዲ​ሰ​ጠው እስ​ኪ​ያ​ውቅ ደረስ ከሰው ልጆች ተለ​ይቶ ተሰ​ደደ፥ ልቡም እንደ አውሬ ልብ ሆነ፤ መኖ​ሪ​ያ​ውም ከም​ድረ በዳ አህ​ዮች ጋር ነበረ፤ እንደ በሬም ሣር በላ፤ አካ​ሉም በሰ​ማይ ጠል ረሰ​ረሰ። 22ብል​ጣ​ሶር ሆይ! አንተ ልጁ ስት​ሆን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ልብ​ህን አላ​ዋ​ረ​ድ​ህም፤ ይህ​ንም ሁሉ አላ​ወ​ቅ​ህም። 23በሰ​ማይ አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ኰራህ፤ የመ​ቅ​ደ​ሱ​ንም ዕቃ​ዎች በፊ​ትህ አመጡ፤ አን​ተም መኳ​ን​ን​ት​ህም፥ ሚስ​ቶ​ች​ህም፥ ቁባ​ቶ​ች​ህም የወ​ይን ጠጅ ጠጣ​ች​ሁ​ባ​ቸው፤ ከብ​ርና ከወ​ር​ቅም፥ ከና​ስና ከብ​ረ​ትም፥ ከእ​ን​ጨ​ትና ከድ​ን​ጋ​ይም የተ​ሠ​ሩ​ትን፥ የማ​ያ​ዩ​ት​ንና የማ​ይ​ሰ​ሙ​ት​ንም፥ የማ​ያ​ው​ቁ​ት​ንም አማ​ል​ክት አመ​ሰ​ገ​ንህ፤ ትን​ፋ​ሽ​ህ​ንና መን​ገ​ድ​ህን ሁሉ በእጁ የያ​ዘ​ውን አም​ላክ ግን አላ​መ​ሰ​ገ​ን​ኸ​ውም። 24ስለ​ዚ​ህም ይህ የሰው እጅ ጣት ከእ​ርሱ ዘንድ ተል​ኳል፤ ይህም ጽሕ​ፈት ተጽ​ፎ​አል።
25“የተ​ጻ​ፈ​ውም ጽሕ​ፈት፦ ማኔ፥ ቴቄል፥ ፋሬስ ይላል። 26የነ​ገ​ሩም ፍቺ ይህ ነው፤ ማኔ ማለት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥ​ት​ህን ቈጠ​ራት፤ ፈጸ​ማ​ትም ማለት ነው። 27ቴቄል ማለት፥ በሚ​ዛን ተመ​ዘ​ነች፤ ቀል​ላም ተገ​ኘች#ዕብ. “በሚ​ዛን ተመ​ዝ​ነህ ቀል​ለ​ህም ተገ​ኘህ” ይላል። ማለት ነው። 28ፋሬስ ማለት፥ መን​ግ​ሥ​ትህ ተከ​ፈ​ለች፤ ለሜ​ዶ​ንና ለፋ​ርስ ሰዎ​ችም ተሰ​ጠች” ማለት ነው።
29የዚ​ያን ጊዜም ብል​ጣ​ሶር ለዳ​ን​ኤል ሐም​ራዊ ግምጃ እን​ዲ​ያ​ለ​ብ​ሱት፥ የወ​ርቅ ማር​ዳም በአ​ን​ገቱ ዙሪያ እን​ዲ​ያ​ደ​ር​ጉ​ለት አዘዘ፤ በመ​ን​ግ​ሥ​ትም ላይ ሦስ​ተኛ ገዥ እን​ዲ​ሆን ዐዋጅ አስ​ነ​ገረ።
30በዚ​ያም ሌሊት የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ንጉሥ ብል​ጣ​ሶር ተገ​ደለ። 31ሜዶ​ና​ዊ​ውም ዳር​ዮስ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ። ዕድ​ሜ​ውም ስድሳ ሁለት ዓመት ነበረ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ