የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘዳ​ግም 19

19
የመ​ማ​ጠኛ ከተ​ሞች
(ዘኍ​. 35፥9-28ኢያ. 20፥1-9)
1“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ራ​ቸ​ውን የሚ​ሰ​ጥ​ህን አሕ​ዛብ ባጠ​ፋ​ቸው ጊዜ፥ በወ​ረ​ስ​ሃ​ቸ​ውም ጊዜ፥ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውና በቤ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም በተ​ቀ​መ​ጥህ ጊዜ፥ 2አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ሰ​ጥህ በም​ድ​ርህ መካ​ከል ሦስት ከተ​ሞ​ችን ለራ​ስህ ትለ​ያ​ለህ። 3ለአ​ን​ተም መን​ገ​ድ​ህን ታዘ​ጋ​ጃ​ለህ፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ወ​ር​ስ​ህን ምድር ከሦ​ስት አድ​ር​ገህ ትከ​ፍ​ላ​ለህ፤ ለነ​ፍሰ ገዳ​ይም ሁሉ መማ​ጸኛ ይሁን።
4“የነ​ፍሰ ገዳይ ሕግ ይህ ነው፤ ቀድሞ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ትና​ን​ት​ናና ከት​ና​ን​ትና በፊት” ይላል። ጠላቱ ሳይ​ሆን ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ሳያ​ውቅ የገ​ደለ ወደ​ዚያ ሸሽቶ በሕ​ይ​ወት ይኑር። 5ሰው ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ጋር እን​ጨት ሊለ​ቅም ወደ ዱር ቢሄድ፥ ዛፉ​ንም ሲቈ​ርጥ ምሳሩ ከእጁ ቢወ​ድቅ፥ ብረ​ቱም ከእ​ጄ​ታው ቢወ​ልቅ፥ በባ​ል​ን​ጀ​ራ​ውም ላይ ቢወ​ድ​ቅና ቢገ​ድ​ለው፥ ከእ​ነ​ዚህ ከተ​ሞች በአ​ን​ዲቱ ተማ​ጥኖ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፤ 6ባለ ደሙ ነፍሰ ገዳ​ዩን በልቡ ተና​ድዶ እን​ዳ​ያ​ሳ​ድ​ደው መን​ገ​ዱም ሩቅ ስለ​ሆነ አግ​ኝቶ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ለው፥ አስ​ቀ​ድሞ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ትና​ን​ት​ናና ከት​ና​ን​ትና በፊት” ይላል። ጠላቱ አል​ነ​በ​ረ​ምና ሞት አይ​ገ​ባ​ውም። 7ስለ​ዚህ እኔ፦ ለአ​ንተ ሦስት ከተ​ሞ​ችን ለይ ብዬ አዝ​ዤ​ሃ​ለሁ። 8አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ችህ እንደ ማለ​ላ​ቸው ዳር​ቻ​ህን ቢያ​ሰፋ፥ ለአ​ባ​ቶ​ችህ#ግእዙ “ለወ​ን​ድ​ሞ​ችህ” ይላል። እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ ብሎ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ምድር ሁሉ ቢሰ​ጥህ፥ 9አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትወ​ድድ ዘንድ፥ ሁል​ጊ​ዜም በመ​ን​ገዱ ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ ዛሬ የማ​ዝ​ዝ​ህን ይህ​ችን ትእ​ዛዝ ሁሉ ታደ​ር​ጋት ዘንድ ብት​ሰማ፥ በእ​ነ​ዚህ በሦ​ስት ከተ​ሞች ላይ ሌሎች ሦስት ከተ​ሞ​ችን ትጨ​ም​ራ​ለህ። 10አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ በሚ​ሰ​ጥህ ምድር ውስጥ ንጹሕ ደም እን​ዳ​ይ​ፈ​ስስ፥ በው​ስ​ጥ​ህም የደም ወን​ጀ​ለኛ እን​ዳ​ይ​ኖር።
11“ሰው ግን ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ቢጠላ፥ ቢሸ​ም​ቅ​በ​ትም፥ በእ​ር​ሱም ላይ ቢነሣ፥ ቢገ​ድ​ለ​ውም፥ ከእ​ነ​ዚህ ከተ​ሞች በአ​ን​ዲቱ ቢማ​ጠን፥ 12የከ​ተ​ማው ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ይል​ካሉ፤ ከዚ​ያም ይይ​ዙ​ታል። በባ​ለ​ደ​ሙም እጅ አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​ታል፤ ይሞ​ታ​ልም። 13ዐይ​ን​ህም አት​ራ​ራ​ለት፤ ነገር ግን ንጹ​ሑን ደም ከእ​ስ​ራ​ኤል ታስ​ወ​ግ​ዳ​ለህ፤ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ል​ሃል።
ድን​በር ማፍ​ረስ እን​ደ​ማ​ይ​ገባ
14“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ በሚ​ሰ​ጥህ ምድር፤ በም​ት​ካ​ፈ​ላት ርስ​ትህ አባ​ቶ​ችህ የተ​ከ​ሉ​ትን የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህን የድ​ን​በር ምል​ክት አት​ን​ቀል።
ስለ ምስ​ክ​ሮች የተ​ሰጠ መመ​ሪያ
15“ስለ በደል ሁሉ፥ ክፉ በማ​ድ​ረ​ግም ስለ​ሚ​ሠ​ራት ኀጢ​አት ሁሉ በማ​ንም ላይ አንድ ምስ​ክር አይ​ሁን፤ በሁ​ለት ምስ​ክ​ሮች ወይም በሦ​ስት ምስ​ክ​ሮች ቃል ነገር ሁሉ ይጸ​ናል። 16በዐ​መፃ ይከ​ስ​ሰው ዘንድ በሰው ላይ ሐሰ​ተኛ ምስ​ክር ቢቆም፥ 17ሁለቱ ጠበ​ኞች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በካ​ህ​ና​ቱና በዚያ ዘመን በሚ​ፈ​ርዱ ፈራ​ጆች ፊት ይቆ​ማሉ፤ 18ፈራ​ጆ​ቹም አጥ​ብ​ቀው ይመ​ረ​ም​ራሉ፤ ያም ምስ​ክር ሐሰ​ተኛ ምስ​ክር ሆኖ በወ​ን​ድሙ ላይ በሐ​ሰት ተና​ግሮ ቢገኝ፥ 19በወ​ን​ድሙ ላይ ክፋ​ትን ያደ​ርግ ዘንድ እንደ ወደደ በእ​ርሱ ላይ ታደ​ር​ጉ​በ​ታ​ላ​ችሁ፤ እን​ዲ​ሁም ከእ​ና​ንተ መካ​ከል ክፉ​ውን ታስ​ወ​ግ​ዳ​ላ​ችሁ። 20ሌላ​ውም ሰምቶ ይፈ​ራል፤ እን​ደ​ዚህ ያለ​ው​ንም ክፋት በመ​ካ​ከ​ልህ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ደግሞ አያ​ደ​ር​ግም። 21ዐይ​ን​ህም አት​ራ​ራ​ለት፤ ነፍስ በነ​ፍስ፥ ዐይን በዐ​ይን፥ ጥርስ በጥ​ርስ፥ እጅ በእጅ፥ እግር በእ​ግር ይመ​ለ​ሳል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ