የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘዳ​ግም 21

21
ባል​ታ​ወቀ ሰው ስለ ተፈ​ጸመ ግድያ
1“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ በሚ​ሰ​ጥህ ምድር የተ​ገ​ደለ ሰው በሜዳ ወድቆ ቢገኝ፥ ገዳ​ዩም ባይ​ታ​ወቅ፥ 2ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ች​ህና ፈራ​ጆ​ችህ ወጥ​ተው በተ​ገ​ደ​ለው ሰው ዙሪያ እስ​ካ​ሉት ከተ​ሞች ድረስ በስ​ፍር ይለኩ፤ 3ለተ​ገ​ደ​ለ​ውም ሰው አቅ​ራ​ቢያ የሆ​ነች የከ​ተ​ማ​ዪቱ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ከላ​ሞች ለሥራ ያል​ደ​ረ​ሰ​ች​ውን፥ ቀን​በ​ርም ያል​ተ​ጫ​ነ​ባ​ትን ጊደር ይው​ሰዱ፤ 4የዚ​ያ​ችም ከተማ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጊደ​ሪ​ቱን ይዘው ፈሳሽ ውኃ ወዳ​ለ​በት ወዳ​ል​ታ​ረ​ሰና ዘርም ወዳ​ል​ተ​ዘ​ራ​በት ሽለቆ ይሄ​ዳሉ፤ በዚ​ያም በሸ​ለ​ቆው ውስጥ የጊ​ደ​ሪ​ቱን ቋን​ጃ​ዋን ይቈ​ር​ጣሉ። 5የሌዊ ልጆች ካህ​ና​ትም ይቀ​ር​ባሉ፤ በፊቱ እን​ዲ​ያ​ገ​ለ​ግሉ፥ በስ​ሙም እን​ዲ​ባ​ርኩ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መር​ጦ​አ​ቸ​ዋ​ልና፤ በእ​ነ​ር​ሱም ቃል ክር​ክር ሁሉ ጕዳ​ትም ሁሉ ይቆ​ማ​ልና፤ 6ወደ ተገ​ደ​ለው ሰው አቅ​ራ​ቢያ የሆ​ነ​ችው የከ​ተ​ማ​ዪቱ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች በሸ​ለ​ቆው ውስጥ ቋን​ጃዋ በተ​ቈ​ረ​ጠው ጊደር ራስ ላይ እጃ​ቸ​ውን ይታ​ጠቡ፦ 7‘እጆ​ቻ​ችን ይህን ደም አላ​ፈ​ሰ​ሱም፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ች​ንም አላ​ዩም፤ 8አቤቱ፥ ከግ​ብፅ ምድር የተ​ቤ​ዠ​ኸ​ውን ሕዝ​ብ​ህን እስ​ራ​ኤ​ልን ይቅር በል፤ በሕ​ዝ​ብ​ህም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ የን​ጹ​ሑን ደም በደል አት​ቍ​ጠር’ ብለው ይና​ገሩ፤ ስለ ደሙም ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸ​ዋል። 9አን​ተም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካ​ምና ጥሩ የሆ​ነ​ውን ባደ​ረ​ግህ ጊዜ የን​ጹ​ሑን ደም በደል#“በደል” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ታር​ቃ​ለህ።
በጦ​ር​ነት ስለ ተማ​ረኩ ሴቶች
10“ጠላ​ቶ​ች​ህን ልት​ወጋ በወ​ጣህ ጊዜ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ጅህ አሳ​ልፎ በሰ​ጣ​ቸ​ውና በማ​ረ​ክ​ሃ​ቸው ጊዜ፥ 11በም​ር​ኮው ውስጥ የተ​ዋ​በች ሴት ብታይ፥ ብት​መ​ኛ​ትም፥ ሚስ​ትም ልታ​ደ​ር​ጋት ብት​ወ​ድድ፥ 12ወደ ቤትህ ታመ​ጣ​ታ​ለህ፤ ራስ​ዋ​ንም ትላ​ጫ​ታ​ለህ፤ ጥፍ​ር​ዋ​ንም ትቈ​ር​ጥ​ላ​ታ​ለህ፤ 13የተ​ማ​ረ​ከ​ች​በ​ት​ንም ልብስ ታወ​ል​ቅ​ላ​ታ​ለህ፤ በቤ​ት​ህም ታስ​ቀ​ም​ጣ​ታ​ለህ፤ ስለ አባ​ቷና ስለ እናቷ አንድ ወር ሙሉ ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ ከዚ​ያም በኋላ ትደ​ር​ስ​ባ​ታ​ለህ፤ ባልም ትሆ​ና​ታ​ለህ፤ እር​ስ​ዋም ሚስት ትሆ​ን​ል​ሃ​ለች። 14ከዚ​ያም በኋላ በእ​ር​ስዋ ደስ ባይ​ልህ አር​ነት አው​ጥ​ተህ ትለ​ቅ​ቃ​ታ​ለህ፤ በዋጋ ግን አት​ሸ​ጣ​ትም፤ አግ​ብ​ተ​ሃ​ታ​ልና እን​ደ​ባ​ሪያ አት​ቍ​ጠ​ራት።
ስለ በኵር ልጅ መብት
15“ለአ​ንድ ሰው አን​ዲቱ የተ​ወ​ደ​ደች፥ አን​ዲ​ቱም የተ​ጠ​ላች ሁለት ሚስ​ቶች ቢኖ​ሩት፥ ለእ​ር​ሱም የተ​ወ​ደ​ደ​ችው፥ ደግ​ሞም የተ​ጠ​ላ​ችው ልጆ​ችን ቢወ​ልዱ፥ በኵ​ሩም ከተ​ጠ​ላ​ችው ሚስት የተ​ወ​ለ​ደው ልጅ ቢሆን፥ 16ለል​ጆቹ ከብ​ቱን በሚ​ያ​ወ​ር​ስ​በት ቀን ከተ​ጠ​ላ​ችው ሚስት በተ​ወ​ለ​ደው በበ​ኵሩ ፊት ከተ​ወ​ደ​ደ​ችው ሚስት የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ልጅ በኵር ያደ​ር​ገው ዘንድ አይ​ገ​ባ​ውም፤ 17ነገር ግን ከከ​ብቱ ሁለት እጥፍ ለእ​ርሱ በመ​ስ​ጠት ከተ​ጠ​ላ​ችው ሚስት የተ​ወ​ለ​ደው ልጅ በኵር እንደ ሆነ ያስ​ታ​ውቅ። የኀ​ይሉ መጀ​መ​ሪያ ነውና በኵ​ር​ነቱ የእ​ርሱ ነው።
ስለ​ማ​ይ​ታ​ዘዙ ልጆች
18“ማንም ሰው ለአ​ባቱ ቃልና ለእ​ናቱ ቃል የማ​ይ​ታ​ዘዝ፥ ቢገ​ሥ​ጹ​ትም የማ​ይ​ሰ​ማ​ቸው ትዕ​ቢ​ተ​ኛና ዐመ​ፀኛ ልጅ ቢኖ​ረው፥ 19አባ​ቱና እናቱ ይዘው ወደ ከተ​ማዉ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ ወደ​ሚ​ኖ​ር​በ​ትም ስፍራ በር ይው​ሰ​ዱት፤ 20የከ​ተ​ማ​ዉ​ንም ሰዎች፦ ‘ይህ ልጃ​ችን ትዕ​ቢ​ተ​ኛና ዐመ​ፀኛ ነው፥ ቃላ​ች​ን​ንም አይ​ሰ​ማም፤ ስስ​ታ​ምና ሰካ​ራም ነው’ ይበ​ሉ​አ​ቸው። 21የከ​ተ​ማ​ዉም ሰዎች ሁሉ በድ​ን​ጋይ ደብ​ድ​በው ይግ​ደ​ሉት፤ እን​ዲ​ህም ክፉ​ውን ነገር ከመ​ካ​ከ​ልህ ታር​ቃ​ለህ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ሰም​ተው ይፈ​ራሉ።
ልዩ ልዩ ሕጎች
22“ማንም ሰው ለሞት የሚ​ያ​በ​ቃ​ውን ኀጢ​አት ቢሠራ፥ እን​ዲ​ሞ​ትም ቢፈ​ረ​ድ​በት፥ በእ​ን​ጨ​ትም ላይ ብት​ሰ​ቅ​ለው፥ 23በእ​ን​ጨት ላይ የተ​ሰ​ቀለ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ረ​ገመ ነውና ሥጋው በእ​ን​ጨት ላይ አይ​ደር፤ ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ የሰ​ጠ​ህን ምድር እን​ዳ​ታ​ረ​ክስ በእ​ር​ግጥ በዚ​ያው ቀን ቅበ​ረው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ