የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘዳ​ግም 24

24
ስለ ጋብ​ቻና ፍች የተ​ሰጠ ሕግ
1“አንድ ሰው ሴትን ወስዶ ቢያ​ገባ፥ የእ​ፍ​ረት ነገር ስላ​ገ​ኘ​ባት በእ​ርሱ ዘንድ ሞገስ ባታ​ገኝ፥ የፍ​ች​ዋን ጽሕ​ፈት ጽፎ በእ​ጅዋ ይስ​ጣት፤ ከቤ​ቱም ይስ​ደ​ዳት። 2ከቤ​ቱም ከወ​ጣች በኋላ ሌላ ወንድ ብታ​ገባ፥ 3ሁለ​ተ​ኛ​ውም ባል ቢጠ​ላት፥ የፍ​ች​ዋ​ንም ጽሕ​ፈት ጽፎ በእ​ጅዋ ቢሰ​ጣት ፥ ከቤ​ቱም ቢሰ​ድ​ዳት፥ ወይም ሚስት አድ​ርጎ ያገ​ባት ሁለ​ተ​ኛው ባልዋ ቢሞት፥ 4የሰ​ደ​ዳት የቀ​ድሞ ባልዋ ከረ​ከ​ሰች በኋላ ደግሞ ያገ​ባት ዘንድ አይ​ገ​ባ​ውም፤ ያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ጠላ ነውና፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ የሰ​ጠ​ህን ምድር አታ​ር​ክስ።
ልዩ ልዩ ሕግ​ጋት
5“አዲስ ሚስ​ትም ያገባ ሰው ወደ ጦር​ነት አይ​ሂድ፤ ምንም ነገር አይ​ጫ​ኑ​በት፤ ነገር ግን አንድ ዓመት በቤቱ በፈ​ቃዱ ይቀ​መጥ፤ የወ​ሰ​ዳ​ት​ንም ሚስ​ቱን ደስ ያሰ​ኛት።
6“የሰ​ውን ነፍስ እንደ መው​ሰድ ነውና ወፍጮ ወይም መጅ ስለ መያዣ ማንም አይ​ው​ሰድ።
7“ማንም ሰው ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከወ​ን​ድ​ሞቹ ሰውን አፍኖ ሲሰ​ር​ቅና ሲሸጥ ቢገኝ ያን የሰ​ረ​ቀ​ውን ሰው ይግ​ደ​ሉት፤ እን​ዲ​ሁም ክፉ​ውን ነገር ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ አርቁ።
8“ስለ ለምጽ ደዌ ሌዋ​ው​ያን ካህ​ናት ያስ​ተ​ማ​ሩ​ህን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ያስ​ተ​ማ​ሩ​አ​ች​ሁን” ይላል። ሁሉ ፈጽ​መህ እን​ድ​ት​ጠ​ብቅ እን​ድ​ታ​ደ​ር​ግም ተጠ​ን​ቀቅ፤ እኔ ያዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ውን እን​ዲሁ ታደ​ርግ ዘንድ ጠብቅ። 9አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ብፅ ባወ​ጣ​ችሁ ጊዜ በመ​ን​ገድ ሳላ​ችሁ በማ​ር​ያም ላይ ያደ​ረ​ገ​ውን ዐስብ።
10“ለባ​ል​ን​ጀ​ራህ ባበ​ደ​ር​ኸው ጊዜ መያ​ዣ​ውን ልት​ወ​ስድ ወደ ቤቱ አት​ግባ። 11አንተ ግን በውጭ ቁም፤ ያበ​ደ​ር​ኸ​ውም ሰው መያ​ዣ​ውን ወደ ውጭ ያው​ጣ​ልህ። 12ያም ሰው ድሃ ቢሆን መያ​ዣ​ውን በአ​ንተ ዘንድ አታ​ሳ​ድር። 13ለብ​ሶት እን​ዲ​ተኛ እን​ዲ​ባ​ር​ክ​ህም ፀሐይ ሳይ​ገባ መያ​ዣ​ውን ፈጽ​መህ መል​ስ​ለት፤ በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ምጽ​ዋት#ዕብ. “ጽድቅ” ይላል። ይሆ​ን​ል​ሃል።
14“ከወ​ን​ድ​ሞ​ችህ ወይም በሀ​ገ​ርህ ውስጥ ከአ​ሉት መጻ​ተ​ኞች ድሃና ችግ​ረኛ የሆ​ነ​ውን ምን​ደኛ ደመ​ወ​ዙን አት​ከ​ል​ክ​ለው፤ 15ድሃ ነውና፥ ተስ​ፋ​ውም እርሱ ነውና ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ይ​ጮ​ኽ​ብህ፥ ኀጢ​አ​ትም እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ብህ ደመ​ወ​ዙን ፀሐይ ሳይ​ገባ በቀኑ ስጠው።
16“አባ​ቶች ስለ ልጆ​ቻ​ቸው አይ​ገ​ደሉ፤ ልጆ​ችም ስለ አባ​ቶ​ቻ​ቸው አይ​ገ​ደሉ፤ ነገር ግን ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ በኀ​ጢ​አቱ ይገ​ደል።
17“የመ​ጻ​ተ​ኛ​ው​ንና የድሃ-አደ​ጉን፥ የመ​በ​ለ​ቲ​ቱ​ንም ፍርድ አታ​ጣ​ም​ም​ባ​ቸው፤ የመ​በ​ለ​ቲ​ቱ​ንም ልብስ ለመ​ያዣ አት​ው​ሰ​ድ​ባት። 18አን​ተም በግ​ብፅ ባሪያ እንደ ነበ​ርህ፥ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚያ እን​ዳ​ዳ​ነህ ዐስብ፤ ስለ​ዚህ ይህን ነገር ታደ​ርግ ዘንድ አዝ​ዤ​ሃ​ለሁ።
19“የእ​ር​ሻ​ህን መከር ባጨ​ድህ ጊዜ ነዶም ረስ​ተህ በእ​ር​ሻህ ብታ​ስ​ቀር፥ ትወ​ስ​ደው ዘንድ አት​መ​ለስ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ጅህ ሥራ ሁሉ እን​ዲ​ባ​ር​ክህ፥ ለመ​ጻ​ተ​ኛና ለድሃ-አደግ፥ ለመ​በ​ለ​ትም ተወው። 20የወ​ይ​ራ​ህን ፍሬ በለ​ቀ​ምህ ጊዜ ከቅ​ር​ን​ጫ​ፎቹ ላይ አጥ​ር​ተህ ለመ​ል​ቀም ዳግ​መኛ አት​መ​ለስ፤ ለመ​ጻ​ተ​ኛና ለድሃ-አደግ፥ ለመ​በ​ለ​ትም ይሁን። 21የወ​ይ​ን​ህን ፍሬ በቈ​ረ​ጥህ ጊዜ ቃር​ሚ​ያ​ውን አት​ል​ቀ​መው፤ ለመ​ጻ​ተ​ኛና ለድሃ-አደግ፥ ለመ​በ​ለ​ትም ይሁን። 22አን​ተም በግ​ብፅ ሀገር መጻ​ተኛ እንደ ነበ​ርህ ዐስብ፤ ስለ​ዚህ ይህን ነገር ታደ​ርግ ዘንድ አዝ​ዤ​ሃ​ለሁ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ