የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘዳ​ግም 25

25
1“በሰ​ዎች መካ​ከል ጠብ ቢሆን፥ ወደ ፍር​ድም ቢመጡ፥ ቢፋ​ረ​ዱም ለጻ​ድቁ ይፈ​ረ​ድ​ለት፤ በበ​ደ​ለ​ኛ​ውም ይፈ​ረ​ድ​በት። 2በደ​ለ​ኛ​ውም መገ​ረፍ ቢገ​ባው እን​ዲ​ገ​ረፍ ፈራጁ በፊቱ በም​ድር ላይ ያጋ​ድ​መው፤ የግ​ር​ፋ​ቱም ቍጥር እንደ ኀጢ​አቱ መጠን ይሁን። 3ግር​ፋ​ቱም አርባ ይሁን፤ ከዚህ በላይ ጨምሮ ብዙ ግር​ፋት ቢገ​ር​ፈው ወን​ድ​ምህ በፊ​ትህ ነው​ረኛ ይሆ​ና​ልና ከዚህ በላይ አይ​ጨ​መ​ር​በት።
4“እህ​ል​ህን በም​ታ​በ​ራይ ጊዜ በሬ​ዉን አፉን አት​ሰ​ረው።
ወን​ድም፥ ለሞተ ወን​ድሙ የሚ​ያ​ደ​ር​ገው ግዴታ
5“ወን​ድ​ማ​ማ​ቾች በአ​ን​ድ​ነት ቢቀ​መጡ፥ አን​ዱም ልጅ ሳይ​ኖ​ረው ቢሞት፥ የሞ​ተው ሰው ሚስት ሌላ ሰው ታገባ ዘንድ ወደ ውጭ አት​ሂድ፤ ነገር ግን የባ​ልዋ ወን​ድም ወደ እር​ስዋ ገብቶ እር​ስ​ዋን ያግባ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ይኑር። 6የም​ዋቹ ስም ከእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ እን​ዳ​ይ​ጠፋ ከእ​ር​ስዋ የሚ​ወ​ለ​ደው#ዕብ. “በኵር” የሚል ይጨ​ም​ራል። ልጅ በሞ​ተው በወ​ን​ድሙ ስም ይጠራ። 7ያም ሰው የወ​ን​ድ​ሙን ሚስት ማግ​ባት ባይ​ወ​ድድ፥ ዋር​ሳ​ዪቱ በበሩ አደ​ባ​ባይ ወደ​ሚ​ቀ​መጡ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሄዳ፦ ‘ዋር​ሳዬ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ለወ​ን​ድሙ ስም ማቆም እንቢ አለ፤ ከእ​ኔም ጋር ሊኖር አል​ወ​ደ​ደም’ ትበ​ላ​ቸው። 8የከ​ተ​ማ​ውም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጠር​ተው ይጠ​ይ​ቁት፤ እር​ሱም በዚያ ቆሞ፦ ‘አገ​ባት ዘንድ አል​ወ​ድ​ድም’ ቢል፥ 9ዋር​ሳ​ዪቱ በሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎቹ ፊት ወደ እርሱ ቀርባ፦ ‘የወ​ን​ድ​ሙን ቤት በማ​ይ​ሠራ ሰው ላይ እን​ዲህ ይደ​ረ​ግ​በ​ታል’ ስትል የአ​ንድ እግ​ሩን ጫማ ታውጣ፤ በፊ​ቱም እን​ትፍ ትበ​ል​በት። 10በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ስሙ ‘የጫማ ፈቱ ቤት’ ተብሎ ይጠራ።
ልዩ ልዩ ትእ​ዛ​ዛት
11“ሁለት ሰዎች እርስ በር​ሳ​ቸው ቢጣሉ፥ የአ​ን​ደ​ኛ​ውም ሰው ሚስት ባል​ዋን ከሚ​መ​ታው ሰው እጅ ታድ​ነው ዘንድ ብት​ቀ​ርብ፥ እጅ​ዋ​ንም ዘር​ግታ ሁለ​ቱን የብ​ል​ቱን ፍሬ​ዎች ብት​ይዝ፥ 12እጅ​ዋን ቍረጥ፤ ዐይ​ን​ህም አት​ራ​ራ​ላት።
13“በከ​ረ​ጢ​ትህ ውስጥ ታላ​ቅና ታናሽ ሚዛን አይ​ኑ​ር​ልህ። 14በቤ​ትህ ውስጥ ታላ​ቅና ታናሽ መስ​ፈ​ሪያ አይ​ኑ​ር​ልህ። 15አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ በሚ​ሰ​ጥህ ምድር ላይ ዕድ​ሜህ ይረ​ዝም ዘንድ እው​ነ​ተ​ኛና ፍጹም ሚዛን ይሁ​ን​ልህ፤ እው​ነ​ተ​ኛና ፍጹም መስ​ፈ​ሪ​ያም ይሁ​ን​ልህ። 16ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ፥ ክፋ​ት​ንም የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ጠላ ነውና።
ዐማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ንን ስለ ማጥ​ፋት የተ​ሰጠ ትእ​ዛዝ
17“ከግ​ብፅ በወ​ጣህ ጊዜ ዐማ​ሌቅ በመ​ን​ገድ ላይ ያደ​ረ​ገ​ብ​ህን ዐስብ፤ 18በመ​ን​ገድ ላይ እንደ ተቃ​ወ​መህ፥ አን​ተም ተር​በ​ህና ደክ​መህ ሳለህ ጓዝ​ህ​ንና ከአ​ንተ በኋላ ደክ​መው የነ​በ​ሩ​ትን ሁሉ እንደ መታ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ፈ​ራ​ውም። 19ስለ​ዚህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ በሚ​ሰ​ጥህ ምድር ከሚ​ከ​ብ​ቡህ ጠላ​ቶ​ችህ ሁሉ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሳ​ረ​ፈህ ጊዜ፥ የዐ​ማ​ሌ​ቅን ዝክረ ስሙን ከሰ​ማይ በታች አጥ​ፋው፤ ይህ​ንም አት​ርሳ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ