ኦሪት ዘዳግም 25
25
1“በሰዎች መካከል ጠብ ቢሆን፥ ወደ ፍርድም ቢመጡ፥ ቢፋረዱም ለጻድቁ ይፈረድለት፤ በበደለኛውም ይፈረድበት። 2በደለኛውም መገረፍ ቢገባው እንዲገረፍ ፈራጁ በፊቱ በምድር ላይ ያጋድመው፤ የግርፋቱም ቍጥር እንደ ኀጢአቱ መጠን ይሁን። 3ግርፋቱም አርባ ይሁን፤ ከዚህ በላይ ጨምሮ ብዙ ግርፋት ቢገርፈው ወንድምህ በፊትህ ነውረኛ ይሆናልና ከዚህ በላይ አይጨመርበት።
4“እህልህን በምታበራይ ጊዜ በሬዉን አፉን አትሰረው።
ወንድም፥ ለሞተ ወንድሙ የሚያደርገው ግዴታ
5“ወንድማማቾች በአንድነት ቢቀመጡ፥ አንዱም ልጅ ሳይኖረው ቢሞት፥ የሞተው ሰው ሚስት ሌላ ሰው ታገባ ዘንድ ወደ ውጭ አትሂድ፤ ነገር ግን የባልዋ ወንድም ወደ እርስዋ ገብቶ እርስዋን ያግባ፤ ከእርስዋም ጋር ይኑር። 6የምዋቹ ስም ከእስራኤል ዘንድ እንዳይጠፋ ከእርስዋ የሚወለደው#ዕብ. “በኵር” የሚል ይጨምራል። ልጅ በሞተው በወንድሙ ስም ይጠራ። 7ያም ሰው የወንድሙን ሚስት ማግባት ባይወድድ፥ ዋርሳዪቱ በበሩ አደባባይ ወደሚቀመጡ ሽማግሌዎች ሄዳ፦ ‘ዋርሳዬ በእስራኤል ዘንድ ለወንድሙ ስም ማቆም እንቢ አለ፤ ከእኔም ጋር ሊኖር አልወደደም’ ትበላቸው። 8የከተማውም ሽማግሌዎች ጠርተው ይጠይቁት፤ እርሱም በዚያ ቆሞ፦ ‘አገባት ዘንድ አልወድድም’ ቢል፥ 9ዋርሳዪቱ በሽማግሌዎቹ ፊት ወደ እርሱ ቀርባ፦ ‘የወንድሙን ቤት በማይሠራ ሰው ላይ እንዲህ ይደረግበታል’ ስትል የአንድ እግሩን ጫማ ታውጣ፤ በፊቱም እንትፍ ትበልበት። 10በእስራኤልም ዘንድ ስሙ ‘የጫማ ፈቱ ቤት’ ተብሎ ይጠራ።
ልዩ ልዩ ትእዛዛት
11“ሁለት ሰዎች እርስ በርሳቸው ቢጣሉ፥ የአንደኛውም ሰው ሚስት ባልዋን ከሚመታው ሰው እጅ ታድነው ዘንድ ብትቀርብ፥ እጅዋንም ዘርግታ ሁለቱን የብልቱን ፍሬዎች ብትይዝ፥ 12እጅዋን ቍረጥ፤ ዐይንህም አትራራላት።
13“በከረጢትህ ውስጥ ታላቅና ታናሽ ሚዛን አይኑርልህ። 14በቤትህ ውስጥ ታላቅና ታናሽ መስፈሪያ አይኑርልህ። 15አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ ይረዝም ዘንድ እውነተኛና ፍጹም ሚዛን ይሁንልህ፤ እውነተኛና ፍጹም መስፈሪያም ይሁንልህ። 16ይህን የሚያደርግ ሁሉ፥ ክፋትንም የሚያደርግ ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና።
ዐማሌቃውያንን ስለ ማጥፋት የተሰጠ ትእዛዝ
17“ከግብፅ በወጣህ ጊዜ ዐማሌቅ በመንገድ ላይ ያደረገብህን ዐስብ፤ 18በመንገድ ላይ እንደ ተቃወመህ፥ አንተም ተርበህና ደክመህ ሳለህ ጓዝህንና ከአንተ በኋላ ደክመው የነበሩትን ሁሉ እንደ መታ፤ እግዚአብሔርንም አልፈራውም። 19ስለዚህ አምላክህ እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ በሚሰጥህ ምድር ከሚከብቡህ ጠላቶችህ ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ባሳረፈህ ጊዜ፥ የዐማሌቅን ዝክረ ስሙን ከሰማይ በታች አጥፋው፤ ይህንም አትርሳ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 25: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ