የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘዳ​ግም 8

8
የተ​ስ​ፋ​ይ​ቱን ምድር ለመ​ው​ረስ የተ​ሰጠ መመ​ሪያ
1“በሕ​ይ​ወት እን​ድ​ት​ኖሩ፥ እን​ድ​ት​በ​ዙም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር ገብ​ታ​ችሁ እን​ድ​ት​ወ​ር​ሱ​አት፥ ዛሬ ለአ​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛዝ ሁሉ ታደ​ርጉ ዘንድ ጠብቁ። 2አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ት​ንህ ዘንድ፥ በል​ብ​ህም ያለ​ውን ትእ​ዛ​ዙን ትጠ​ብቅ ወይም አት​ጠ​ብቅ እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ፥ ሊያ​ስ​ጨ​ን​ቅህ#ዕብ. “በእ​ነ​ዚህ አርባ ዓመ​ታት” የሚል ይጨ​ም​ራል። በም​ድረ በዳ የመ​ራ​ህን መን​ገድ ሁሉ አስብ። 3ሰውም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ በሚ​ወጣ ነገር ሁሉ በሕ​ይ​ወት እን​ዲ​ኖር እንጂ ሰው በእ​ን​ጀራ ብቻ በሕ​ይ​ወት እን​ዳ​ይ​ኖር ያስ​ታ​ው​ቅህ ዘንድ አስ​ጨ​ነ​ቀህ፥ አስ​ራ​በ​ህም፤ አን​ተም ያላ​ወ​ቅ​ኸ​ውን፥ አባ​ቶ​ች​ህም ያላ​ወ​ቁ​ትን መና መገ​በህ። 4የለ​በ​ስ​ኸው ልብስ አላ​ረ​ጀም፤ እግ​ር​ህም አል​ነ​ቃም፤ እነሆ፥ አርባ ዓመት ሆነ። 5ሰውም ልጁን እን​ደ​ሚ​ገ​ሥጽ እን​ዲሁ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አን​ተን እን​ዲ​ገ​ሥጽ በል​ብህ ዕወቅ። 6በመ​ን​ገ​ዱም እን​ድ​ት​ሄድ፥ እር​ሱ​ንም እን​ድ​ት​ፈራ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ጠብቅ። 7አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መል​ካ​ምና ሰፊ ምድር፥ ከሜ​ዳና ከተ​ራ​ሮች የሚ​መ​ነጩ የውኃ ጅረ​ቶ​ችና ፈሳ​ሾ​ችም ወዳ​ሉ​ባት ምድር፥ 8ስንዴ፥ ገብ​ስም፥ ወይ​ንም፥ በለ​ስም፥ ሮማ​ንም#“ሮማ​ንም” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ወደ ሞሉ​ባት፥ ወይ​ራም፥ ቅቤም፥ ማርም ወደ ሞሉ​ባት ምድር፥ 9ሳይ​ጐ​ድ​ልህ እን​ጀ​ራን ወደ​ም​ት​በ​ላ​ባት፥ አን​ዳ​ችም ወደ​ማ​ታ​ጣ​ባት ምድር፥ ድን​ጋ​ይዋ ብረት ወደ ሆነ፥ ከተ​ራ​ራ​ዋም መዳብ ወደ​ሚ​ማ​ስ​ባት ምድር ያገ​ባ​ሃል። 10ትበ​ላ​ማ​ለህ፤ ትጠ​ግ​ብ​ማ​ለህ፤ ስለ ሰጠ​ህም ስለ መል​ካ​ሚቱ ምድር አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ሰ​ግ​ና​ለህ።
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዳ​ይ​ረሱ የተ​ሰጠ ማስ​ጠ​ን​ቀ​ቂያ
11“ዛሬ እኔ አን​ተን የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛ​ዙ​ንና ፍር​ዱን፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ባለ​መ​ጠ​በቅ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዳ​ት​ረሳ ተጠ​ን​ቀቅ፤ 12ከበ​ላ​ህና ከጠ​ገ​ብህ በኋላ፥ መል​ካ​ምም ቤት ሠር​ተህ ከተ​ቀ​መ​ጥ​ህ​ባት በኋላ፤ 13የላ​ምና የበግ መንጋ ከበ​ዛ​ልህ በኋላ፥ ብር​ህና ወር​ቅ​ህም፥ ያለ​ህም ሁሉ ከበ​ዛ​ልህ በኋላ፥ ልብህ እን​ዳ​ይ​ታ​በይ፤ 14ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት ያወ​ጣ​ህን፥ 15የሚ​ና​ደፍ እባ​ብና ጊንጥ፥ ጥማ​ትም ባለ​ባት፥ ውኃም በሌ​ለ​ባት፥ በታ​ላ​ቂ​ቱና በም​ታ​ስ​ፈ​ራው ምድረ በዳ የመ​ራ​ህን፥ ከጭ​ንጫ ድን​ጋ​ይም ጣፋጭ ውኃን ያወ​ጣ​ል​ህን፥ 16በመ​ጨ​ረ​ሻም ዘመን መል​ካም ያደ​ር​ግ​ልህ ዘንድ ሊፈ​ት​ንህ፥ ሊያ​ዋ​ር​ድ​ህም አባ​ቶ​ችህ ያላ​ወ​ቁ​ትን መና በም​ድረ በዳ የመ​ገ​በ​ህን አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዳ​ት​ረሳ፥ 17በል​ብ​ህም፦ በጕ​ል​በቴ፥ በእ​ጄም ብር​ታት ይህን ሁሉ ታላቅ ኀይል አደ​ረ​ግሁ#ዕብ. “ይህን ሀብት አመ​ጣ​ልኝ” ይላል። እን​ዳ​ትል። 18ነገር ግን ዛሬ እንደ ሆነ ለአ​ባ​ቶ​ችህ የማ​ለ​ውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ#ዕብ. “ሀብት ለማ​ከ​ማ​ቸት እርሱ ጕል​በት ሰጥ​ቶ​ሃል” ይላል። እርሱ ኀይ​ልን ስለ​ሚ​ሰ​ጥህ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አስ​በው። 19አም​ላ​ክ​ህ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽሞ ብት​ረሳ፥ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት ብት​ከ​ተል፥ ብታ​መ​ል​ካ​ቸ​ውም፥ ብት​ሰ​ግ​ድ​ላ​ቸ​ውም፥ ፈጽሞ እን​ደ​ም​ት​ጠፋ እኔ ዛሬ​ውኑ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን አስ​መ​ሰ​ክ​ር​ብ​ሃ​ለሁ።#“ሰማ​ይና ምድ​ርን” የሚ​ለው በዕብ. የለም። 20የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስለ አል​ሰ​ማ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፊ​ታ​ችሁ እን​ደ​ሚ​አ​ጠ​ፋ​ቸው እንደ አሕ​ዛብ ሁሉ እና​ን​ተም እን​ዲሁ ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ