የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘዳ​ግም 9

9
በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ማመፅ የሚ​ያ​ስ​ከ​ት​ለው መቅ​ሠ​ፍት
1“እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ስማ፤ ከአ​ንተ የበ​ለ​ጡ​ት​ንና የበ​ረ​ቱ​ትን አሕ​ዛብ፥ የቅ​ጽ​ራ​ቸው ግንብ እስከ ሰማይ የሚ​ደ​ርስ ታላ​ላ​ቆች ከተ​ሞ​ችን ለመ​ው​ረስ ትገቡ ዘንድ ዛሬ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ትሻ​ገ​ረ​ዋ​ለህ። 2አን​ተም የም​ታ​ው​ቃ​ቸው፥ ስለ እነ​ር​ሱም፦ በዔ​ናቅ ልጆች ፊት መቆም ማን ይች​ላል? ሲባል የሰ​ማ​ኸው ታላቅ፥ ብዙና ረዥም ሕዝብ የዔ​ናቅ ልጆች ናቸው። 3አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊ​ትህ እን​ዲ​ያ​ልፍ ዛሬ ዕወቅ፤ እርሱ የሚ​በላ እሳት ነው፤ እርሱ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፤ በፊ​ት​ህም ያዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ነገ​ረህ ከፊ​ትህ ያር​ቃ​ቸ​ዋል፥ ፈጥ​ኖም ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል። 4አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ያን አሕ​ዛብ ከፊ​ትህ ባወ​ጣ​ቸው ጊዜ፦ ስለ ጽድቄ እወ​ር​ሳት ዘንድ ወደ​ዚች መል​ካም ምድር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ባኝ ብለህ በል​ብህ አት​ና​ገር፤#ዕብ. “ነገር ግን እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፊ​ትህ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል” የሚል ይጨ​ም​ራል። 5ምድ​ራ​ቸ​ውን ትወ​ር​ሳት ዘንድ የም​ት​ገ​ባው ስለ ጽድ​ቅ​ህና ስለ ልብህ ቅን​ነት አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፊ​ትህ በሚ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው በእ​ነ​ዚያ አሕ​ዛብ ኀጢ​አት ምክ​ን​ያ​ትና ለአ​ባ​ቶ​ችህ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን ቃል ያጸና ዘንድ ነው። 6እን​ግ​ዲህ አንተ አን​ገተ ደን​ዳና ሕዝብ ነህና አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ​ችን መል​ካም ምድር ርስት አድ​ርጎ የሰ​ጠህ ስለ ጽድ​ቅህ እን​ዳ​ይ​ደለ ዛሬ ዕወቅ።
7“አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በም​ድረ በዳ ምን ያህል እን​ዳ​ሳ​ዘ​ን​ኸው፥ ከግ​ብፅ ሀገር ከወ​ጣ​ህ​በት ቀን ጀምሮ ወደ​ዚህ ስፍራ እስከ መጣ​ችሁ ድረስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ እን​ዳ​መ​ፃ​ችሁ አስብ፤ አት​ር​ሳም። 8በኮ​ሬብ ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አሳ​ዘ​ና​ች​ሁት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሊያ​ጠ​ፋ​ችሁ በእ​ና​ንተ ላይ ተቈጣ። 9ሁለ​ቱን የድ​ን​ጋይ ጽላት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር የተ​ማ​ማ​ለ​ባ​ቸ​ውን የቃል ኪዳን ጽላት እቀ​በል ዘንድ ወደ ተራራ በወ​ጣሁ ጊዜ፥ በተ​ራ​ራው አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ተቀ​ምጬ ነበር፤ እን​ጀራ አል​በ​ላ​ሁም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣ​ሁም። 10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጣት የተ​ጻ​ፉ​ትን ሁለት የድ​ን​ጋይ ጽላት ሰጠኝ፤ በተ​ሰ​በ​ሰ​ባ​ችሁ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር#ዕብ. “በእ​ሳት ውስጥ ሆኖ” የሚል ይጨ​ም​ራል። በተ​ራ​ራው ላይ የነ​ገ​ረኝ ቃል ሁሉ ተጽ​ፎ​ባ​ቸው ነበር። 11ከአ​ርባ ቀንና ከአ​ርባ ሌሊ​ትም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁለ​ቱን የድ​ን​ጋይ ጽላት፥ የቃል ኪዳ​ኑን ጽላት ሰጠኝ። 12እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፦ ተነ​ሥ​ተህ ከዚህ ፈጥ​ነህ ውረድ፤ ከግ​ብፅ ያወ​ጣ​ሃ​ቸው ሕዝ​ብህ በድ​ለ​ዋ​ልና፤ ፈጥ​ነው ካዘ​ዝ​ኋ​ቸው መን​ገድ ፈቀቅ ብለ​ዋ​ልና፥ ቀልጦ የተ​ሠራ ምስ​ልም ለራ​ሳ​ቸው አድ​ር​ገ​ዋ​ልና። 13እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፦ ‘አንድ ጊዜም ሁለት ጊዜም እን​ዲህ ብዬ ነገ​ር​ሁህ፤#“አንድ ጊዜም ሁለት ጊዜም እን​ዲህ ብዬ ነገ​ር​ሁህ” የሚ​ለው በዕብ. የለም። ይህ ሕዝብ አን​ገተ ደን​ዳና ሕዝብ እንደ ሆነ አይ​ች​አ​ለሁ፤ 14አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ፥ ስማ​ቸ​ው​ንም ከሰ​ማይ በታች እደ​መ​ስስ ዘንድ ተወኝ፤ አን​ተ​ንም ከእ​ነ​ርሱ ለሚ​በ​ረ​ታና እጅግ ለሚ​በዛ ሕዝብ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ።’ 15እኔም ተመ​ልሼ ከተ​ራ​ራው ወረ​ድሁ፤ ተራ​ራ​ውም በእ​ሳት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እስከ ሰማይ” ብሎ ይጨ​ም​ራል። ይነ​ድድ ነበር፤ ሁለ​ቱም የቃል ኪዳን ጽላት በሁ​ለቱ እጆች ነበሩ። 16እነሆ፥ በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ በደ​ላ​ችሁ፥ ለእ​ና​ን​ተም ቀልጦ የተ​ሠራ ምስል ሠር​ታ​ችሁ ልት​ጠ​ብ​ቁት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካዘ​ዛ​ችሁ መን​ገድ ፈጥ​ና​ችሁ ፈቀቅ እን​ዳ​ላ​ችሁ ባየሁ ጊዜ፥ 17ሁለ​ቱ​ንም ጽላት ያዝሁ፤ ከሁ​ለ​ቱም እጆች ጣል​ኋ​ቸው፤ በእ​ና​ን​ተም ፊት ሰበ​ር​ኋ​ቸው። 18ስለ ሠራ​ች​ሁት ኀጢ​አት ሁሉ፥ እር​ሱ​ንም ለማ​ስ​ቈ​ጣት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ የሆ​ነ​ውን ነገር ስላ​ደ​ረ​ጋ​ችሁ፥ እንደ ፊተ​ኛው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ዳግ​መኛ ለመ​ንሁ፤ እን​ጀራ አል​በ​ላ​ሁም፥ ውኃም አል​ጠ​ጣ​ሁም። 19እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሊያ​ጠ​ፋ​ችሁ ከተ​ቈ​ጣ​ባ​ችሁ ከቍ​ጣ​ውና ከመ​ዓቱ የተ​ነሣ ፈራሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚ​ያን ጊዜ ደግሞ ሰማኝ። 20እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሮ​ንን ሊያ​ጠ​ፋው እጅግ ተቈ​ጣው፤ ስለ አሮ​ንም ደግሞ በዚ​ያን ጊዜ ጸለ​ይሁ። 21ስለ አደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ትም ኀጢ​አት የጥ​ጃ​ውን ምስል ወሰ​ድሁ፤ በእ​ሳ​ትም አቃ​ጠ​ል​ሁት፤ አደ​ቀ​ቅ​ሁ​ትም፤ እንደ ትቢ​ያም እስ​ኪ​ሆን ድረስ ፈጨ​ሁት፤ እንደ ትቢ​ያም ሆነ፤ ትቢ​ያ​ው​ንም ከተ​ራ​ራው በሚ​ወ​ርድ ወንዝ ጨመ​ር​ሁት።
22“በው​ዕ​የት፥ በፈ​ተ​ናም#ዕብ. “በተ​ቤ​ራም በማ​ሳ​ህም” ይላል። በም​ኞት መቃ​ብ​ርም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አስ​ቈ​ጣ​ች​ሁት። 23እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ውጡ፤ የሰ​ጠ​ኋ​ች​ሁ​ንም ምድር ውረሱ ብሎ ከቃ​ዴስ በርኔ በላ​ካ​ችሁ ጊዜ በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ዐመ​ፃ​ችሁ፤ በእ​ር​ሱም አላ​መ​ና​ች​ሁም፤ ቃሉ​ንም አል​ሰ​ማ​ች​ሁም። 24ለእ​ና​ንተ ከታ​ወ​ቀ​በት ቀን ጀምሮ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐመ​ፀ​ኞች ነበ​ራ​ችሁ።
25“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ያጠ​ፋ​ችሁ ዘንድ ስለ ተና​ገረ ቀድሞ እንደ ለመ​ንሁ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለመ​ንሁ። 26በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት እን​ዲህ ብዬ ጸለ​ይሁ፦ የአ​ማ​ል​ክት ንጉሥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ በታ​ላቅ ኀይ​ልህ የተ​ቤ​ዠ​ሃ​ቸ​ውን፥ በጠ​ነ​ከ​ረ​ች​ውም እጅ​ህና በተ​ዘ​ረ​ጋች ክን​ድህ ከግ​ብፅ ያወ​ጣ​ሃ​ቸ​ውን ሕዝ​ብ​ህ​ንና ርስ​ት​ህን አታ​ጥፋ። 27በራ​ስህ የማ​ል​ህ​ላ​ቸ​ውን አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን አብ​ር​ሃ​ም​ንና ይስ​ሐ​ቅን፥ ያዕ​ቆ​ብ​ንም አስብ፤ የዚ​ህን ሕዝብ ልበ ደን​ዳ​ና​ነት፥ ክፋ​ቱ​ንም፥ ኀጢ​አ​ቱ​ንም አት​መ​ል​ከት፤ 28ከእ​ር​ስዋ እኛን ያወ​ጣ​ህ​ባት ምድር ሰዎች፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተስፋ ወደ ሰጣ​ቸው ምድር ያገ​ባ​ቸው ዘንድ አል​ቻ​ለ​ምና፥ ጠል​ቶ​አ​ቸ​ው​ማ​ልና ስለ​ዚህ በም​ድረ በዳ ሊገ​ድ​ላ​ቸው አወ​ጣ​ቸው እን​ዳ​ይሉ። 29እነ​ር​ሱም በታ​ላቅ ኀይ​ልህ፥ በጸ​ና​ውና በተ​ዘ​ረ​ጋ​ውም ክን​ድህ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ሃ​ቸው ሕዝ​ብ​ህና ርስ​ትህ ናቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ