መጽ​ሐፈ መክ​ብብ 10

10
1የሞቱ ዝን​ቦች የተ​ቀ​መ​መ​ውን የዘ​ይት ሽቱ ያገ​ሙ​ታል፤ በስ​ን​ፍ​ናም ካለ ታላቅ ክብር ይልቅ ትንሽ ጥበብ ትበ​ል​ጣ​ለች።#ዕብ. “እን​ዲ​ሁም ትንሽ ስን​ፍና ጥበ​ብ​ንና ክብ​ርን ያጠ​ፋል” ይላል። 2የጠ​ቢብ ልብ በስ​ተ​ቀኙ ነው፥ የሰ​ነፍ ልብ ግን በስ​ተ​ግ​ራው ነው። 3ደግ​ሞም ሰነፍ በልቡ ፈቃ​ድና መን​ገድ በሚ​ሄድ ጊዜ አእ​ምሮ ይጐ​ድ​ለ​ዋል፥ የሚ​ያ​ስ​በ​ውም ሁሉ ሰን​ፍና ነው።
4ትዕ​ግ​ሥት ታላ​ቁን ኀጢ​አት ያስ​ተ​ሰ​ር​ያ​ልና የገዢ ቍጣ የተ​ነ​ሣ​ብህ እንደ ሆነ ስፍ​ራ​ህን አት​ል​ቀቅ። 5ከፀ​ሓይ በታች ያየ​ሁት ክፉ ነገር አለ፥ እር​ሱም ከገዢ ባለ​ማ​ወቅ የሚ​ወጣ ስሕ​ተት ነው፥ 6ሰነፍ በታ​ላቅ ማዕ​ርግ ላይ ተሾመ፥ ባለ​ጠ​ጎች ግን በተ​ዋ​ረደ ስፍራ ተቀ​መጡ። 7አገ​ል​ጋ​ዮች በፈ​ረስ ላይ ሲቀ​መጡ፥ መኳ​ን​ን​ትም እንደ አገ​ል​ጋ​ዮች በም​ድር ላይ በእ​ግ​ራ​ቸው ሲሄዱ አየሁ።
8ለባ​ል​ን​ጀ​ራው ጕድ​ጓ​ድን የሚ​ምስ ይወ​ድ​ቅ​በ​ታል፥ ቅጥ​ር​ንም የሚ​ያ​ፈ​ር​ስን እባብ ትነ​ድ​ፈ​ዋ​ለች። 9ድን​ጋ​ይን የሚ​ፈ​ነ​ቅል ይታ​መ​ም​በ​ታል፥ ዕን​ጨ​ት​ንም የሚ​ፈ​ልጥ ይጐ​ዳ​በ​ታል። 10ምሣሩ ከዛ​ቢ​ያው ቢወ​ልቅ ሰው​የው ፊቱን ወዲ​ያና ወዲህ ይላል፤ ብዙ ኀይ​ልም ያስ​ፈ​ል​ገ​ዋል። ጥበብ ግን ለብ​ርቱ ሰው ትርፉ ነው፤ 11እባብ ቢነ​ድፍ ባለ መድ​ኀ​ኒ​ትም ባያ​ድን ባለ መድ​ኀ​ኒቱ አይ​ጠ​ቀ​ምም።
12የጠ​ቢብ ሰው የአፉ ቃል ሞገስ ናት፤ የሰ​ነፍ ከን​ፈ​ሮች ግን ራሱን ይው​ጡ​ታል። 13የአፉ ቃል መጀ​መ​ሪያ ስን​ፍና ነው፥ የን​ግ​ግ​ሩም ፍጻሜ ክፉ ነው። 14ሰነፍ ነገ​ርን ያበ​ዛል፤ ሰውም የሆ​ነ​ው​ንና ወደ ፊት የሚ​ሆ​ነ​ውን አያ​ው​ቅም፤ ከእ​ርሱ በኋላ የሚ​ሆ​ነ​ው​ንስ ማን ይነ​ግ​ረ​ዋል? 15የሰ​ነፍ ድካሙ ያሠ​ቃ​የ​ዋል፥ ወደ ከተማ መሄ​ድን አያ​ው​ቅ​ምና።
16ንጉ​ሥሽ ሕፃን የሆነ፥ መኳ​ን​ን​ቶ​ች​ሽም ማል​ደው የሚ​በሉ፥ አንቺ ሀገር ሆይ፥ ወዮ​ልሽ! 17ንጉ​ሥሽ የጌታ ልጅ የሆነ፥ መኳ​ን​ን​ቶ​ች​ሽም ለብ​ር​ታት በጊዜ የሚ​በሉ፥ የማ​ያ​ፍ​ሩም፥ አንቺ ሀገር ሆይ፥ የተ​መ​ሰ​ገ​ንሽ ነሽ። 18በሰ​ዎች ስን​ፍ​ናና ቦዘ​ኔ​ነት የቤት ጣራ ይዘ​ብ​ጣል፥ በእ​ጆች ስን​ፍ​ናም ቤት ያፈ​ስ​ሳል። 19ሰነ​ፎች ሰዎች እን​ጀ​ራን ለሣቅ ያደ​ር​ጉ​ታል፥ የወ​ይን ጠጅም ሕያ​ዋ​ንን ደስ ያሰ​ኛል፥ ሁሉም ለገ​ን​ዘብ ይገ​ዛል። 20የሰ​ማይ ዎፍ ቃል​ህን ያወ​ጣ​ዋ​ልና፥ ክንፍ ያለ​ውም ነገ​ር​ህን ያወ​ራ​ዋ​ልና በል​ብህ ዐሳብ እን​ኳን ቢሆን ንጉ​ሥን አት​ሳ​ደብ፥ በመ​ኝታ ቤት​ህም ባለ​ጠ​ጋን አት​ሳ​ደብ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ

YouVersion የእርስዎን ተሞክሮ ግላዊ ለማድረግ ኩኪዎችን ይጠቀማል። የእኛን ድረ ገጽ በመጠቀም፣ በግለሰብነት መመሪያችን ላይ እንደተገለጸው የእኛን የኩኪዎች አጠቃቀም ተቀብለዋል