መጽ​ሐፈ መክ​ብብ 9

9
1ይህን ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ለልቤ ሰጠሁ፥ ጻድ​ቃ​ንና ጠቢ​ባን ሥራ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ እንደ ሆኑ፥ ይህን ሁሉ ልቤ ተመ​ለ​ከ​ተች፤ ፍቅር ወይም ጥል ቢሆን ሰው አያ​ው​ቅም፥ ሁሉ ወደ ፊታ​ቸው ነው። 2በሁ​ሉም ከን​ቱ​ነት አለ፥ የጻ​ድ​ቁና የበ​ደ​ለ​ኛው፥ የመ​ል​ካ​ሙና የክ​ፉው፥ የን​ጹ​ሑና የር​ኩሱ፥ መሥ​ዋ​ዕ​ትን የሚ​ሠ​ዋ​ውና የማ​ይ​ሠ​ዋው፥ የመ​ል​ካ​ሙና እን​ዲሁ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኛው፥ የመ​ሐ​ላ​ኛ​ውና እን​ዲሁ መሐ​ላን የሚ​ፈ​ራው ድርሻ አንድ ነው። 3ከፀ​ሓይ በታች የተ​ደ​ረ​ገው ክፉ ሁሉ ለሁሉ ነው፤ የሁሉ ድርሻ አንድ ነውና። ደግ​ሞም የሰው ልጆች ልብ ክፋ​ትን ትሞ​ላ​ለች፥ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው ሳሉ ሁከት በል​ባ​ቸው አለ፥ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሙታን ይወ​ር​ዳሉ። 4ከሕ​ያ​ዋን ጋር አን​ድ​ነት ያለው ማንም ሰው ተስፋ አለ​ውና ከሞተ አን​በሳ ያል​ሞተ ውሻ ይሻ​ላል። 5ሕያ​ዋን እን​ዲ​ሞቱ ያው​ቃ​ሉና፤ ሙታን ግን አን​ዳች አያ​ው​ቁም፤ መታ​ሰ​ቢ​ያ​ቸ​ውም ተረ​ስ​ቶ​አ​ልና ከዚህ በኋላ ዋጋ የላ​ቸ​ውም። 6ፍቅ​ራ​ቸ​ውና ጥላ​ቸው ቅን​አ​ታ​ቸ​ውም በአ​ን​ድ​ነት እነሆ፥ ጠፍ​ቶ​አል፤ ከፀ​ሓይ በታ​ችም በሚ​ሠ​ራው ነገር ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዕድል ፈንታ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ የላ​ቸ​ውም።
7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ​ህን ተቀ​ብ​ሎ​ታ​ልና፦ ና እን​ጀ​ራ​ህን በደ​ስታ ብላ፥ በበጎ ልቡ​ናም የወ​ይን ጠጅ​ህን ጠጣ። 8ሁል​ጊዜ ልብ​ስህ ነጭ ይሁን፤ ቅባ​ትም ከራ​ስህ ላይ አይ​ታጣ። 9በሕ​ይ​ወ​ትህ፥ አን​ተም ከፀ​ሓይ በታች በም​ት​ደ​ክ​ም​በት ድካም ይህ ዕድል ፈን​ታህ ነውና ከንቱ በሆነ በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ፥ ከፀ​ሓይ በታች በሰ​ጠህ፥ በከ​ንቱ ዘመ​ንህ ሁሉ፥ ከም​ት​ወ​ድ​ዳት ሚስ​ትህ ጋር ደስ ይበ​ልህ። 10አንተ በም​ት​ሄ​ድ​በት በሲ​ኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕው​ቀ​ትና ጥበብ አይ​ገ​ኙ​ምና እጅህ ለማ​ድ​ረግ የም​ት​ች​ለ​ውን ሁሉ እንደ ኀይ​ልህ አድ​ርግ።
11እኔም ተመ​ለ​ስሁ፥ ከፀ​ሓይ በታ​ችም ሩጫ ለፈ​ጣ​ኖች፥ ጦር​ነ​ትም ለኀ​ያ​ላን፥ እን​ጀ​ራም ለጠ​ቢ​ባን፥ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ትም ለአ​ስ​ተ​ዋ​ዮች፥ ሞገ​ስም ለዐ​ዋ​ቂ​ዎች እን​ዳ​ል​ሆነ አየሁ፤ ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ያገ​ና​ኛ​ቸ​ዋል። 12ሰውም ጊዜ​ውን አያ​ው​ቅም፤ በክፉ መረብ እንደ ተጠ​መዱ ዓሣ​ዎች ፥ በወ​ጥ​መ​ድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እን​ዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድ​ን​ገት ሲወ​ድ​ቅ​ባ​ቸው ይጠ​መ​ዳሉ።
13ከፀ​ሓይ በታ​ችም ጥበ​ብን አየሁ፥ እር​ስ​ዋም በእኔ ዘንድ ታላቅ ናት። 14ታናሽ ከተማ ነበ​ረች፥ ጥቂ​ቶች ሰዎ​ችም ነበ​ሩ​ባት፤ ታላቅ ንጉ​ሥም መጣ​ባት፥ ከበ​ባ​ትም፥ ታላቅ ግን​ብ​ንም ሠራ​ባት። 15ጠቢብ ድሃ ሰውም በው​ስ​ጥዋ ተገ​ኘ​ባት፥ ያች​ንም ከተማ በጥ​በቡ አዳ​ናት፤ ያን ድሃ ሰው ግን ማንም አላ​ሰ​በ​ውም። 16እኔም፥ “ከኀ​ይል ይልቅ ጥበብ ትበ​ል​ጣ​ለች፤ የድ​ሃው ጥበብ ግን ተና​ቀች ቃሉም አል​ተ​ሰ​ማ​ችም” አልሁ።
17በስ​ን​ፍና ከሚ​ፈ​ርዱ ፈራ​ጆች ጩኸት ይልቅ የጠ​ቢ​ባን ቃል በጸ​ጥታ ትሰ​ማ​ለች። 18ከጦር መሣ​ሪ​ያ​ዎች ይልቅ ጥበብ ትሻ​ላ​ለች፤ አንድ ኀጢ​አ​ተኛ ግን ብዙ መል​ካ​ምን ያጠ​ፋል።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ

YouVersion የእርስዎን ተሞክሮ ግላዊ ለማድረግ ኩኪዎችን ይጠቀማል። የእኛን ድረ ገጽ በመጠቀም፣ በግለሰብነት መመሪያችን ላይ እንደተገለጸው የእኛን የኩኪዎች አጠቃቀም ተቀብለዋል