ኦሪት ዘፀአት 1
1
በግብፅ በእስራኤላውያን ላይ የደረሰው ግፍዕ
1ከአባታቸው ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገቡት የእስራኤል ልጆች ስሞች እነዚህ ናቸው፤ ሰው ሁሉ ከቤተ ሰቡ ጋር ገባ፤ 2ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ 3ይሳኮር፥ ዛብሎን፥ ብንያም። 4ዳን፥ ንፍታሌም፥ ጋድ፥ አሴር። 5ዮሴፍም አስቀድሞ በግብፅ ነበረ። ከያዕቆብ ጕልበት የወጡት ሰዎች ሁሉ ሰባ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሰባ አምስት” ይላል። ነፍሶች ነበሩ፤ 6ዮሴፍም ሞተ፤ ወንድሞቹም፥ ያም ትውልድ ሁሉ። 7የእስራኤልም ልጆች በዙ፤ ተባዙም፤ የተጠሉም ሆኑ።#“የተጠሉም ሆኑ” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. የለም። እጅግም ጸኑ፤ ምድሪቱም በእነርሱ ሞላች።
8በግብፅ ዮሴፍን ያላወቀ ሌላ ንጉሥ ተነሣ። 9እርሱም ሕዝቡን፥ “እነሆ፥ የእስራኤል ልጆች ሕዝብ ታላቅና ብዙ ሆነዋል፤ ከእኛም ይልቅ በርትተዋል፤ 10ኑ፤ እንጠበብባቸው፤ የበዙ እንደሆነ ጦርነት በመጣብን ጊዜ በጠላቶቻችን ላይ ተደርበው በኋላችን ይወጉናልና፥ ከምድራችንም ያስወጡናልና።” 11በብርቱ ሥራም ያስጨንቋቸው ዘንድ የሠራተኞች አለቆችን ሾመባቸው፤ ለፈርዖንም ፌቶምን፥ ራምሴንና የፀሐይ ከተማ የምትባል ዖንን ጽኑ ከተሞች አድርገው ሠሩ። 12ነገር ግን እንዳስጨነቁአቸው መጠን እንዲሁ በዙ፤ እጅግም ጸኑ ፤ ግብፃውያንም የእስራኤልን ልጆች ይጸየፉአቸው ነበር።#ዕብ. “ከእስራኤልም ልጆች የተነሣ ግብፃውያን ይፈሩ ነበር” ይላል። 13ግብፃውያንም የእስራኤልን ልጆች በግፍዕ ገዙአቸው። 14በጽኑ ሥራ፥ በጭቃ፥ በጡብም፥ በእርሻም ሥራ ሁሉ፥ በመከራም በሚያሠሩአቸው ሥራ ሁሉ፤ ሕይወታቸውን ያስመርሩአቸው ነበር።
15የግብፅም ንጉሥ አንዲቱ ሲፓራ፥ ሁለተኛዪቱም ፎሓ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ፎያ” ይላል። የሚባሉትን የዕብራውያትን አዋላጆች እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ 16“እናንተ ዕብራውያትን ሴቶች ስታዋልዱ ለመውለድ እንደ ደረሱ በአያችሁ ጊዜ፥ ወንድ ቢሆን ግደሉት፤ ሴት ብትሆን ግን አትግደሏት።” 17አዋላጆች ግን እግዚአብሔርን ፈሩ፤ የግብፅ ንጉሥም እንደ አዘዛቸው አላደረጉም፤ ወንዶቹን ሕፃናትንም አዳኑአቸው። 18የግብፅም ንጉሥ አዋላጆችን ጠርቶ፥ “ለምን እንዲህ አደረጋችሁ? ወንዶቹን ሕፃናትንስ ለምን አዳናችሁ?” አላቸው። 19አዋላጆችም ፈርዖንን፥ “የዕብራውያን ሴቶች እንደ ግብፅ ሴቶች ስላልሆኑ አዋላጆች ሳይገቡ ይወልዳሉ” አሉት። 20እግዚአብሔርም ለአዋላጆች መልካም አደረገላቸው፤ ሕዝቡም በዙ፤ እጅግም ጸኑ። 21እንዲህም ሆነ፤ አዋላጆች እግዚአብሔርን ስለፈሩ ቤቶችን አደረገላቸው። 22ፈርዖንም፥ “የሚወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ ወደ ወንዝ ጣሉት፤ ሴትን ልጅ ሁሉ ግን በሕይወት አድኑአት” ብሎ ሕዝቡን ሁሉ አዘዘ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፀአት 1: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ