የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 50

50
1ዮሴ​ፍም በአ​ባቱ ፊት ወደቀ፤ በእ​ር​ሱም ላይ አለ​ቀሰ፤ ሳመ​ውም። 2ዮሴ​ፍም ባለ መድ​ኀ​ኒ​ቶች አገ​ል​ጋ​ዮቹ አባ​ቱን በሽቱ ያሹት ዘንድ አዘዘ፤ ባለ መድ​ኀ​ኒ​ቶ​ችም እስ​ራ​ኤ​ልን በሽቱ አሹት። 3አርባ ቀንም ፈጸ​ሙ​ለት፤ ሽቱ የሚ​ቀ​ቡ​በ​ትን ቀን እን​ዲሁ ይቈ​ጥ​ራ​ሉና፤#ዕብ. “የሽቱ ማድ​ረ​ጊ​ያው ቀን እን​ዲሁ ይፈ​ጸ​ማ​ልና” ይላል። የግ​ብ​ፅም ሰዎች ሰባ ቀን አለ​ቀ​ሱ​ለት።
4የል​ቅ​ሶ​ውም ወራት ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ ዮሴፍ ለፈ​ር​ዖን መኳ​ን​ንት እን​ዲህ ብሎ ተና​ገረ፥ “እኔ በፊ​ታ​ችሁ ሞገ​ስን አግ​ኝቼ እንደ ሆንሁ ለፈ​ር​ዖን እን​ዲህ ብላ​ችሁ ስለ እኔ ንገ​ሩት፦ 5አባቴ ሳይ​ሞት አም​ሎ​ኛል፤ እን​ዲህ ሲል፦ ‘እነሆ እኔ እሞ​ታ​ለሁ፤ በቈ​ፈ​ር​ሁት መቃ​ብር በከ​ነ​ዓን ምድር በዚያ ቅበ​ረኝ።’ አሁ​ንም ወጥቼ አባ​ቴን ልቅ​በ​ርና ልመ​ለስ።” 6ፈር​ዖ​ንም ዮሴ​ፍን አለው፥ “ውጣ፤ አባ​ት​ህ​ንም እን​ዳ​ማ​ለህ ቅበ​ረው።” 7ዮሴ​ፍም አባ​ቱን ሊቀ​ብር ወጣ፤ የፈ​ር​ዖን ሎሌ​ዎ​ችም ሁሉ፥ የቤቱ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ሁሉ፥ የግ​ብፅ ምድር ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ወጡ፤ 8የዮ​ሴ​ፍም ቤተ ሰቦች ሁሉ፥ ወን​ድ​ሞ​ቹም፥ የአ​ባ​ቱም ቤተ ሰቦች ወጡ፤ ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንና በጎ​ቻ​ቸ​ውን፥ ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ብቻ በጌ​ሤም ተዉ። 9ሰረ​ገ​ሎ​ችም፥ ፈረ​ሰ​ኞ​ችም ከእ​ርሱ ጋር ወጡ፤ ሠራ​ዊ​ቱም ብዙ ነበር። 10በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወዳ​ለ​ችው ወደ አጣድ አው​ድማ ደረሱ፤ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅ​ሶም አለ​ቀ​ሱ​ለት፤ ለአ​ባ​ቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደ​ረ​ገ​ለት። 11በዚ​ያች ምድር የሚ​ኖሩ የከ​ነ​ዓን ሰዎ​ችም በአ​ጣድ አው​ድማ የሆ​ነ​ውን ልቅሶ በአዩ ጊዜ፥ “የግ​ብፅ ልቅሶ እን​ዲህ ታላቅ ነውን?” አሉ፤ ስለ​ዚ​ህም የዚ​ያን ቦታ ስም “ላሐ ግብፅ” ብለው ጠሩት፤ እር​ሱም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ነው። 12ልጆ​ቹም እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው እን​ደ​ዚ​ያው አደ​ረ​ጉ​ለት፤ 13ልጆ​ቹም ወደ ከነ​ዓን ምድር መለ​ሱት፤ ባለ ሁለት ክፍል በሆ​ነች ዋሻም ቀበ​ሩት፤ እር​ስ​ዋም በመ​ምሬ ፊት ያለች፥ አብ​ር​ሃም ለመ​ቃ​ብር ርስት ከኬ​ጢ​ያ​ዊው ከኤ​ፍ​ሮን ከእ​ር​ሻው ጋር የገ​ዛት ዋሻ ናት። 14ዮሴ​ፍና ወን​ድ​ሞቹ፥ አባ​ቱ​ንም ሊቀ​ብሩ ከእ​ርሱ ጋር የወ​ጡት ሰዎች ሁሉ አባ​ቱን ከቀ​በረ በኋላ ወደ ግብፅ ተመ​ለሱ።
ዮሴፍ ወን​ድ​ሞ​ቹን ማረ​ጋ​ጋቱ
15የዮ​ሴ​ፍም ወን​ድ​ሞች አባ​ታ​ቸው እንደ ሞተ በአዩ ጊዜ እን​ዲህ አሉ፥ “ምና​ል​ባት ዮሴፍ ያደ​ረ​ግ​ን​በ​ትን ክፋት ያስ​ብ​ብን ይሆ​ናል፤ ባደ​ረ​ግ​ን​በ​ትም ክፋት ሁሉ ብድ​ራት ይመ​ል​ስ​ብን ይሆ​ናል።” 16ወደ ዮሴ​ፍም መጡ፤ እን​ዲ​ህም አሉት፥ “አባ​ትህ ገና ሳይ​ሞት እን​ዲህ ብሎ አዝ​ዟል፦ 17‘ዮሴ​ፍን እን​ዲህ በሉት፦ እባ​ክህ የወ​ን​ድ​ሞ​ች​ህን በደል ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ይቅር በል፤ እነ​ርሱ በአ​ንተ ክፉ አድ​ር​ገ​ው​ብ​ሃ​ልና፤’ አሁ​ንም እባ​ክህ የአ​ባ​ትህ አም​ላክ ባሪ​ያ​ዎች የበ​ደ​ሉ​ህን ይቅር በል።” 18ዮሴ​ፍም ይህን ሲሉት አለ​ቀሰ። ወን​ድ​ሞቹ ደግሞ መጡ፤#ዕብ. “በፊ​ቱም ሰግ​ደው” የሚል ይጨ​ም​ራል። “እነሆ፥ እኛ ለአ​ንተ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ነን” አሉት። 19ዮሴ​ፍም አላ​ቸው፥ “አት​ፍሩ፤ ይህ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ሆኖ​አ​ልና።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና” ዕብ. “እኔ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፋንታ ነኝን” ይላል። 20እና​ንተ በእኔ ላይ ክፉ መከ​ራ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እን​ዲ​መ​ገብ ለማ​ድ​ረግ ለእኔ መል​ካም መከረ። 21አሁ​ንም አት​ፍሩ፤ እኔ እና​ን​ተ​ንና ቤተ ሰቦ​ቻ​ች​ሁን እመ​ግ​ባ​ች​ኋ​ለሁ።” አጽ​ና​ና​ቸ​ውም፤ በል​ባ​ቸው የሚ​ገባ ነገ​ርም ነገ​ራ​ቸው።
የዮ​ሴፍ ሞት
22ዮሴ​ፍም በግ​ብፅ ሀገር ተቀ​መጠ፤ እር​ሱና ወን​ድ​ሞቹ የአ​ባ​ቱም ቤተ ሰብ፤ ዮሴ​ፍም መቶ ዐሥር ዓመት ኖረ። 23ዮሴ​ፍም የኤ​ፍ​ሬ​ምን ልጆች እስከ ሦስት ትው​ልድ አየ። የም​ናሴ ልጅ የማ​ኪር ልጆ​ችም በዮ​ሴፍ ጭን ላይ ተወ​ለዱ። 24ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን አላ​ቸው፥ “እኔ እሞ​ታ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መጐ​ብ​ኘ​ትን ይጐ​በ​ኛ​ች​ኋል፤ ከዚ​ህ​ችም ምድር ያወ​ጣ​ች​ኋል። ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር ያገ​ባ​ች​ኋል።” 25ዮሴ​ፍም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጐ​በ​ኛ​ችሁ ጊዜ አጥ​ን​ቴን ከዚህ አን​ሥ​ታ​ችሁ ከእ​ና​ንተ ጋር አውጡ” ብሎ አማ​ላ​ቸው። 26ዮሴ​ፍም በመቶ ዐሥር ዓመት ዕድ​ሜው ሞተ፤ በሽ​ቱም አሹት፤ በግ​ብፅ ምድ​ርም በሣ​ጥን ውስጥ አኖ​ሩት።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ