ኦሪት ዘፀአት 17
17
ውኃ ከዓለት እንደ ፈለቀላቸው
(ዘዳ. 20፥1-13)
1የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ እግዚአብሔር እንዳዘዘ ከሲን ምድረ በዳ ሊጓዙ ተነሡ፤ በራፊድም ሰፈሩ፤ በዚያም ሕዝቡ የሚጠጡት ውኃ አልነበረም። 2ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት፥ “የምንጠጣውን ውኃ ስጠን” አሉ። ሙሴም፥ “ለምን ትጣሉኛላችሁ? እግዚአብሔርንስ ለምን ትፈታተናላችሁ?” አላቸው። 3ሕዝቡም በዚያ ስፍራ ውኃ ተጠሙ፥ “እኛንና ልጆቻችንን፥ ከብቶቻችንንም በጥማት ልትገድል ለምን ከግብፅ አወጣኸን?” ሲሉ በሙሴ ላይ አንጐራጐሩ። 4ሙሴም፦ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፤ እንዲህም አለ፥ “ለዚህ ሕዝብ ምን ላድርግ? በድንጋይ ሊወግሩኝ ጥቂት ቀርቶአቸዋልና።” 5እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “በሕዝቡ ፊት እለፍ፤ ከእስራኤልም ሽማግሌዎችን ከአንተ ጋር ውሰድ፤ ወንዙንም የመታህባትን በትር በእጅህ ይዘሃት ሂድ። 6እነሆ፥ እኔ በዚያ በኮሬብ በዓለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ፤ ዓለቱንም ትመታለህ፤ ሕዝቡም ይጠጣ ዘንድ ከእርሱ ውኃ ይወጣል” አለው። ሙሴም በእስራኤል ልጆች ፊት እንዲሁ አደረገ። 7ስለ እስራኤልም ልጆች ክርክር፥ “እግዚአብሔር በመካከላችን ነውን? ወይስ አይደለም?” ሲሉ እግዚአብሔርን ስለ ተፈታተኑት የዚያን ስፍራ ስም “መንሱት” ደግሞም “ጋእዝ” ብሎ ጠራው።
እስራኤል ዐማሌቃውያንን ድል እንደ አደረጉ
8ዐማሌቅም መጥቶ ከእስራኤል ጋራ በራፊድ ተዋጋ። 9ሙሴም ኢያሱን፥ “ጐልማሶችን ለአንተ ምረጥ፤ ሲነጋም ወጥተህ ከዐማሌቅ ጋር ተዋጋ፤ እኔም በተራራው ራስ ላይ እቆማለሁ፤ የእግዚአብሔርም በትር በእጄ ናት” አለው። 10ኢያሱም ሙሴ እንደ አለው አደረገ፤ ወጥቶም ከዐማሌቅ ጋር ተዋጋ፤ ሙሴና አሮን፥ ሖርም ወደ ኮረብታው ራስ ወጡ። 11እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ እጁን በአነሣ ጊዜ እስራኤል ድል ያደርግ ነበር ፤ እጁንም በአወረደ ጊዜ ዐማሌቅ ድል ያደርግ ነበር። 12የሙሴ እጆች ግን ከብደው ነበር፤ ድንጋይም ወሰዱ፤ በበታቹም አኖሩ፤ እርሱም ተቀመጠበት፤ አሮንና ሖርም አንዱ በዚህ አንዱ በዚያ ሆነው እጆቹን ይደግፉ ነበር፤ ፀሐይም እስክትገባ ድረስ እጆቹ ተዘርግተው ነበር። 13ኢያሱም ዐማሌቅንና ሕዝቡን በሰይፍ ስለት አሸነፈ።
14እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “የዐማሌቅን ዝክር ከሰማይ በታች ጨርሼ እደመስሳለሁና ይህን ለመታሰቢያ በመጽሐፍ ጻፈው፤ በኢያሱም ጆሮ ተናገር” አለው። 15ሙሴም መሠዊያ ሠራ፤ ስሙንም “ምምሕፃን”#ዕብ. “ይህዊህ ንሲ” ይላል። ብሎ ጠራው፤ 16እግዚአብሔር በተሰወረች እጅ ዐማሌቅን እስከ ልጅ ልጅ ይዋጋልና።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፀአት 17: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ