የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፀ​አት 18

18
ዮቶር ሙሴን እንደ መከ​ረው
1የም​ድ​ያም ካህን የሙሴ አማት ዮቶር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙ​ሴና ለሕ​ዝቡ ለእ​ስ​ራ​ኤል ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብፅ እንደ አወጣ ሰማ። 2በዚያ ጊዜ የሙሴ አማት ዮቶር ትቶ​አት የነ​በ​ረ​ውን የሙ​ሴን ሚስት ሲፓ​ራን፥ ሁለ​ቱ​ንም ልጆ​ች​ዋን ወሰደ። 3የአ​ን​ደ​ኛው ስም ጌር​ሳም ነበረ፤ አባቱ “በሌላ ሀገር ስደ​ተኛ ነበ​ርሁ” ብሎ​አ​ልና፤ 4የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ስም አል​ዓ​ዛር ነበረ፤ “የአ​ባቴ አም​ላክ ረዳኝ፤ ከፈ​ር​ዖ​ንም እጅ አዳ​ነኝ” ብሎ​አ​ልና። 5የሙሴ አማት ዮቶ​ርም ከል​ጆ​ቹና ከሚ​ስቱ ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ አጠ​ገብ በም​ድረ በዳ ወደ ሰፈረ ወደ ሙሴ መጣ። 6ሙሴ​ንም፥ “እነሆ፥ አማ​ትህ ዮቶር፥ ሚስ​ት​ህም ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ሁለቱ ልጆ​ችህ መጥ​ተ​ው​ል​ሃል” አሉት። 7ሙሴም አማ​ቱን ሊገ​ናኝ ወጣ፤ እጅ ነሣው፤ ሳመ​ውም፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ሰላ​ምታ ተሰ​ጣጡ፤ ወደ ድን​ኳ​ኑም ገቡ። 8ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ር​ዖ​ንና በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ላይ ስለ እስ​ራ​ኤል ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ፥ በመ​ን​ገ​ድም ያገ​ኛ​ቸ​ውን ድካም ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ አዳ​ና​ቸው ለአ​ማቱ ነገ​ረው። 9ዮቶ​ርም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ረ​ገ​ላ​ቸ​ውን ቸር​ነት ሁሉ፥ ከግ​ብ​ፃ​ው​ያን እጅና ከፈ​ር​ዖን እጅ እንደ አዳ​ና​ቸው ሰምቶ በሁሉ አደ​ነቀ። 10ዮቶ​ርም፥ “ከግ​ብ​ፃ​ው​ያን እጅና ከፈ​ር​ዖን እጅ ሕዝ​ቡን የአ​ዳነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩክ ነው። 11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግብ​ፃ​ው​ያን ከሚ​መ​ኩ​ባ​ቸ​ውና ከሚ​ገ​ዙ​ላ​ቸው አማ​ል​ክት ሁሉ እን​ዲ​በ​ልጥ አሁን ዐወ​ቅሁ” አለ። 12የሙሴ አማት ዮቶ​ርም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና ሌላ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወሰደ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ከሙሴ አማት ጋር እን​ጀራ ሊበሉ አሮ​ንና የእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ መጡ።
የዳ​ኞች መሾም
(ዘዳ. 1፥9-18)
13እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በነ​ጋው ሙሴ በሕ​ዝቡ ሊፈ​ርድ ተቀ​መጠ፤ ሕዝ​ቡም በሙሴ ፊት ከጥ​ዋት እስከ ማታ ድረስ ቆመው ነበር። 14ዮቶ​ርም ሙሴ በሕ​ዝቡ ላይ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ሁሉ አይቶ እን​ዲህ አለው፥ “ብቻ​ህን ተቀ​ም​ጠህ በሕ​ዝቡ የም​ታ​ደ​ር​ገው ይህ ምን​ድን ነው? ሕዝቡ ሁሉ ከጥ​ዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ በዙ​ሪ​ያህ ቆመ​ዋል።” 15ሙሴም አማ​ቱን፥ “ሕዝቡ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ ለመ​ጠ​የቅ ወደ እኔ ይመ​ጣሉ፤ 16ነገ​ርም ቢኖ​ራ​ቸው ወደ እኔ ይመ​ጣሉ፤ በዚ​ህና በዚያ ሰውም መካ​ከል እፈ​ር​ዳ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሥር​ዐ​ትና ሕግ አስ​ታ​ው​ቃ​ቸ​ዋ​ለሁ” አለው። 17የሙ​ሴም አማት አለው፥ “አንተ የም​ታ​ደ​ር​ገው ይህ ነገር ትክ​ክል አይ​ደ​ለም። 18አንተ፥ ከአ​ን​ተም ጋር ያለው ሕዝብ ትደ​ክ​ማ​ላ​ችሁ፤ ይህ ነገር ይከ​ብ​ድ​ብ​ሃል፤ አንተ ብቻ​ህን ልታ​ደ​ር​ገው አት​ች​ልም። 19አሁ​ንም እመ​ክ​ር​ሃ​ለ​ሁና ስማኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ንተ ጋር ይሆ​ናል፤ አንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለሕ​ዝቡ ሁን፤ ነገ​ራ​ቸ​ው​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አድ​ርስ፤ 20የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሥር​ዐ​ቱ​ንና ሕጉን መስ​ክ​ር​ላ​ቸው፤ የሚ​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም መን​ገድ፥ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ት​ንም ሥራ ሁሉ አሳ​ያ​ቸው። 21አን​ተም ከሕ​ዝቡ ሁሉ ኀያ​ላን ሰዎ​ችን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ሩ​ትን እው​ነ​ተ​ኞች ሰዎ​ችን፥ ትዕ​ቢ​ት​ንም የሚ​ጠሉ ሰዎ​ችን ፈልግ። ከእ​ነ​ር​ሱም የሺህ አለ​ቆ​ችን፥ የመቶ አለ​ቆ​ችን፥ የአ​ምሳ አለ​ቆ​ችን፥ የዐ​ሥ​ርም አለ​ቆ​ችን ሹም​ላ​ቸው። 22በሕ​ዝቡ ላይ ሁል ጊዜ ይፍ​ረዱ፤ የከ​በ​ዳ​ቸ​ውን ነገር ወደ አንተ ያም​ጡት፤ ቀላ​ሉን ነገር ሁሉ እነ​ርሱ ይፍ​ረዱ፤ ያቃ​ል​ሉ​ል​ሃል፤ ይረ​ዱ​ሃ​ልም። 23ይህ​ንም ቃሌን ብታ​ደ​ርግ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያበ​ረ​ታ​ሃል፤ መፍ​ረ​ድም ትች​ላ​ለህ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ በሰ​ላም ወደ ስፍ​ራው ይመ​ለ​ሳል።” 24ሙሴም የአ​ማ​ቱን ቃል ሰማ፤ እንደ አለ​ውም አደ​ረገ። 25ሙሴም ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ችሎታ ያላ​ቸ​ውን ሰዎች መረጠ፤ በሕ​ዝ​ቡም ላይ የሺህ አለ​ቆች፥ የመቶ አለ​ቆች፥ የአ​ም​ሳም አለ​ቆች፥ የዐ​ሥ​ርም አለ​ቆች አድ​ርጎ ሾማ​ቸው። 26በሕ​ዝ​ቡም ላይ ሁል​ጊዜ ፈረዱ፤ የከ​በ​ዳ​ቸ​ው​ንም ነገር ወደ ሙሴ አመጡ፤ ቀላ​ሉን ነገር ሁሉ ግን እነ​ርሱ ፈረዱ። 27ሙሴም አማ​ቱን አሰ​ና​በ​ተው፤ እር​ሱም ወደ ሀገሩ ተመ​ለሰ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ