ኦሪት ዘፀአት 19
19
እስራኤል ወደ ሲና እንደ ደረሱ
1የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሦስተኛው ወር በዚያ ቀን ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ። 2ከራፊድም ተነሥተው ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ፤ በዚያም እስራኤል በተራራው ፊት ሰፈሩ። 3ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ወጣ፤ እግዚአብሔርም ከተራራው ጠርቶ አለው፥ “ለያዕቆብ ቤት እንዲህ በል፤ ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ንገር፤ 4በግብፃውያን ያደረግሁትን፥ እንደ ንስር ክንፍም እንደ ተሸከምኋችሁ፥ ወደ እኔም እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል። 5አሁንም ቃሌን በእውነት ብትሰሙ፥ ኪዳኔንም ብትጠብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጠ ርስት ትሆኑልኛላችሁ። 6እናንተም የክህነት መንግሥት፥ የተቀደሰም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፤ ይህንም ቃል ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው።”
7ሙሴም መጣ፤ የሕዝቡንም ሽማግሌዎች ጠርቶ እግዚአብሔር ያዘዘውን ይህን ቃል ሁሉ በፊታቸው ተናገረ። 8ሕዝቡም ሁሉ አንድ ቃል ሆነው፥ “እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እንሰማለን፤ እናደርጋለንም” ብለው መለሱ፤ ሙሴም የሕዝቡን ቃል ወደ እግዚአብሔር አደረሰ። 9እግዚአብሔር ሙሴን፥ “ከአንተ ጋር ስነጋገር ሕዝቡ እንዲሰሙ፥ ደግሞም ለዘለዓለም እንዲያምኑብህ፥ እነሆ፥ በዐምደ ደመና ወደ አንተ እመጣለሁ” አለው። ሙሴም የሕዝቡን ቃል ለእግዚአብሔር ነገረ። 10እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ውረድ፤ ዛሬና ነገ ራሳቸውን ያንጹ፤ ልብሳቸውንም ያጥቡ ዘንድ ሕዝቡን እዘዛቸው። 11በሦስተኛውም ቀን ሕዝቡ ሁሉ ሲያዩ እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ይወርዳልና ለሦስተኛው ቀን ተዘጋጅተው ይጠብቁ። 12ለሕዝቡም በዙሪያው ወሰን አድርግላቸው፤ ወደ ተራራው እንዳትወጡ፥ ከእርሱ ማንኛውንም ክፍል እንዳትነኩ ተጠንቀቁ፤ ተራራውንም የነካ ፈጽሞ ይሞታል” ብለህ ንገራቸው፤ 13የማንም እጅ አይንካ፤ የሚነካውም ሁሉ በድንጋይ ይወገራል፤ ወይም በፍላጻ ይወጋል፤ እንስሳ ወይም ሰው ቢሆን የቀረበ አይድንም። የመለከት ድምፅና ደመና በተራራው በዐለፈ ጊዜ ወደ ተራራው ይውጡ። 14ሙሴም ከተራራው ወደ ሕዝቡ ወረደ፤ ሕዝቡንም ቀደሰ፤ ልብሳቸውንም አጠቡ። 15ሕዝቡንም፥ “ለሦስተኛው ቀን ተዘጋጁ፤ ወደ ሴቶቻችሁም አትቅረቡ” አለ።
16እንዲህም ሆነ፤ በሦስተኛው ቀን በማለዳ ጊዜ ነጐድጓድና መብረቅ፥ ከባድም ደመና፥ ጉምም በሲና ተራራ ላይ ሆነ፤ እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምፅ ተሰማ፤ በሰፈሩም የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተንቀጠቀጡ። 17ሙሴም ሕዝቡን ከእግዚአብሔር ጋር ለማገናኘት ከሰፈር አወጣቸው፤ በተራራውም እግርጌ ቆሙ። 18እግዚአብሔርም በእሳት ስለ ወረደበት የሲና ተራራ ሁሉ እንደ ምድጃ ጢስ ይጤስ ነበር፤ ከእርሱም እንደ እቶን ጢስ ያለ ጢስ ይወጣ ነበር፤ ተራራውም ሁሉ እጅግ ይናወጥ ነበር፤ ሕዝቡም ፈጽመው ደነገጡ። 19የቀንደ መለከቱም ድምፅ እጅግ እየፈጠነ በርትቶ ይሰማ ነበር። ሙሴም ተናገረ፤ እግዚአብሔርም በድምፅ መለሰለት። 20እግዚአብሔርም በሲና ተራራ ላይ ወደ ተራራው ራስ ወረደ፤ እግዚአብሔርም ሙሴን ወደ ተራራው ራስ ጠራው፤ ሙሴም ወጣ። 21እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “ውረድ፤ ይህንም ለመረዳት ወደ እግዚአብሔር እንዳይቀርቡ፥ ከእነርሱም ብዙ እንዳይጠፉ ለሕዝቡ አስጠንቅቃቸው፤ 22ወደ እግዚአብሔርም የሚቀርቡት ካህናት ደግሞ እንዳያጠፋቸው ራሳቸውን ይቀድሱ” አለው። 23ሙሴም እግዚአብሔርን፥ “ሕዝቡ ወደ ሲና ተራራ ይወጡ ዘንድ አይችሉም፤ አንተ፦ በተራራው ዙሪያ ወሰን አድርግ፤ ቀድሰውም ብለህ አስጠንቅቀኸኛልና” አለው። 24እግዚአብሔርም፥ “ሂድ፤ ውረድ፤ አንተ አሮንም ከአንተ ጋር ትወጣላችሁ፤ ካህናቱና ሕዝቡ ግን እግዚአብሔር እንዳያጠፋቸው ወደ እግዚአብሔር ይወጡ ዘንድ አይደፋፈሩ” አለው። 25ሙሴም ወደ ሕዝቡ ወረደ፤ ይህንም ነገራቸው።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፀአት 19: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ