የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፀ​አት 19

19
እስ​ራ​ኤል ወደ ሲና እንደ ደረሱ
1የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሦ​ስ​ተ​ኛው ወር በዚያ ቀን ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ። 2ከራ​ፊ​ድም ተነ​ሥ​ተው ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ፤ በዚ​ያም እስ​ራ​ኤል በተ​ራ​ራው ፊት ሰፈሩ። 3ሙሴም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከተ​ራ​ራው ጠርቶ አለው፥ “ለያ​ዕ​ቆብ ቤት እን​ዲህ በል፤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ንገር፤ 4በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን፥ እንደ ንስር ክን​ፍም እንደ ተሸ​ከ​ም​ኋ​ችሁ፥ ወደ እኔም እን​ዳ​መ​ጣ​ኋ​ችሁ አይ​ታ​ች​ኋል። 5አሁ​ንም ቃሌን በእ​ው​ነት ብት​ሰሙ፥ ኪዳ​ኔ​ንም ብት​ጠ​ብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ የተ​መ​ረጠ ርስት ትሆ​ኑ​ል​ኛ​ላ​ችሁ። 6እና​ን​ተም የክ​ህ​ነት መን​ግ​ሥት፥ የተ​ቀ​ደ​ሰም ሕዝብ ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ይህ​ንም ቃል ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ንገ​ራ​ቸው።”
7ሙሴም መጣ፤ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጠርቶ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ይህን ቃል ሁሉ በፊ​ታ​ቸው ተና​ገረ። 8ሕዝ​ቡም ሁሉ አንድ ቃል ሆነው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያለ​ውን ሁሉ እን​ሰ​ማ​ለን፤ እና​ደ​ር​ጋ​ለ​ንም” ብለው መለሱ፤ ሙሴም የሕ​ዝ​ቡን ቃል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አደ​ረሰ። 9እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን፥ “ከአ​ንተ ጋር ስነ​ጋ​ገር ሕዝቡ እን​ዲ​ሰሙ፥ ደግ​ሞም ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዲ​ያ​ም​ኑ​ብህ፥ እነሆ፥ በዐ​ምደ ደመና ወደ አንተ እመ​ጣ​ለሁ” አለው። ሙሴም የሕ​ዝ​ቡን ቃል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነገረ። 10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ውረድ፤ ዛሬና ነገ ራሳ​ቸ​ውን ያንጹ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ያጥቡ ዘንድ ሕዝ​ቡን እዘ​ዛ​ቸው። 11በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ሕዝቡ ሁሉ ሲያዩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሲና ተራራ ላይ ይወ​ር​ዳ​ልና ለሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ተዘ​ጋ​ጅ​ተው ይጠ​ብቁ። 12ለሕ​ዝ​ቡም በዙ​ሪ​ያው ወሰን አድ​ር​ግ​ላ​ቸው፤ ወደ ተራ​ራው እን​ዳ​ት​ወጡ፥ ከእ​ርሱ ማን​ኛ​ው​ንም ክፍል እን​ዳ​ት​ነኩ ተጠ​ን​ቀቁ፤ ተራ​ራ​ው​ንም የነካ ፈጽሞ ይሞ​ታል” ብለህ ንገ​ራ​ቸው፤ 13የማ​ንም እጅ አይ​ንካ፤ የሚ​ነ​ካ​ውም ሁሉ በድ​ን​ጋይ ይወ​ገ​ራል፤ ወይም በፍ​ላጻ ይወ​ጋል፤ እን​ስሳ ወይም ሰው ቢሆን የቀ​ረበ አይ​ድ​ንም። የመ​ለ​ከት ድም​ፅና ደመና በተ​ራ​ራው በዐ​ለፈ ጊዜ ወደ ተራ​ራው ይውጡ። 14ሙሴም ከተ​ራ​ራው ወደ ሕዝቡ ወረደ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ቀደሰ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም አጠቡ። 15ሕዝ​ቡ​ንም፥ “ለሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ተዘ​ጋጁ፤ ወደ ሴቶ​ቻ​ች​ሁም አት​ቅ​ረቡ” አለ።
16እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን በማ​ለዳ ጊዜ ነጐ​ድ​ጓ​ድና መብ​ረቅ፥ ከባ​ድም ደመና፥ ጉምም በሲና ተራራ ላይ ሆነ፤ እጅ​ግም የበ​ረታ የቀ​ንደ መለ​ከት ድምፅ ተሰማ፤ በሰ​ፈ​ሩም የነ​በ​ሩት ሕዝብ ሁሉ ተን​ቀ​ጠ​ቀጡ። 17ሙሴም ሕዝ​ቡን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ለማ​ገ​ና​ኘት ከሰ​ፈር አወ​ጣ​ቸው፤ በተ​ራ​ራ​ውም እግ​ርጌ ቆሙ። 18እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ሳት ስለ ወረ​ደ​በት የሲና ተራራ ሁሉ እንደ ምድጃ ጢስ ይጤስ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም እንደ እቶን ጢስ ያለ ጢስ ይወጣ ነበር፤ ተራ​ራ​ውም ሁሉ እጅግ ይና​ወጥ ነበር፤ ሕዝ​ቡም ፈጽ​መው ደነ​ገጡ። 19የቀ​ንደ መለ​ከ​ቱም ድምፅ እጅግ እየ​ፈ​ጠነ በር​ትቶ ይሰማ ነበር። ሙሴም ተና​ገረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በድ​ምፅ መለ​ሰ​ለት። 20እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሲና ተራራ ላይ ወደ ተራ​ራው ራስ ወረደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን ወደ ተራ​ራው ራስ ጠራው፤ ሙሴም ወጣ። 21እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ውረድ፤ ይህ​ንም ለመ​ረ​ዳት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ይ​ቀ​ርቡ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ብዙ እን​ዳ​ይ​ጠፉ ለሕ​ዝቡ አስ​ጠ​ን​ቅ​ቃ​ቸው፤ 22ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ቀ​ር​ቡት ካህ​ናት ደግሞ እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው ራሳ​ቸ​ውን ይቀ​ድሱ” አለው። 23ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “ሕዝቡ ወደ ሲና ተራራ ይወጡ ዘንድ አይ​ች​ሉም፤ አንተ፦ በተ​ራ​ራው ዙሪያ ወሰን አድ​ርግ፤ ቀድ​ሰ​ውም ብለህ አስ​ጠ​ን​ቅ​ቀ​ኸ​ኛ​ልና” አለው። 24እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ሂድ፤ ውረድ፤ አንተ አሮ​ንም ከአ​ንተ ጋር ትወ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ካህ​ና​ቱና ሕዝቡ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይወጡ ዘንድ አይ​ደ​ፋ​ፈሩ” አለው። 25ሙሴም ወደ ሕዝቡ ወረደ፤ ይህ​ንም ነገ​ራ​ቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ