የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፀ​አት 21

21
ስለ ባሪ​ያ​ዎች የተ​ሰጠ ሕግ
(ዘዳ. 15፥12-18)
1“በፊ​ታ​ቸው የም​ታ​ደ​ር​ገው ሥር​ዐት ይህ ነው። 2ዕብ​ራዊ ባሪያ የገ​ዛህ እንደ ሆነ ስድ​ስት ዓመት ያገ​ል​ግ​ልህ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ዓመት በነጻ አር​ነት ይውጣ። 3ብቻ​ውን መጥቶ እንደ ሆነ ብቻ​ውን ይውጣ፤ ከሚ​ስ​ቱም ጋር መጥቶ እንደ ሆነ ሚስቱ ከእ​ርሱ ጋር ትውጣ። 4ጌታው ሚስት አጋ​ብ​ቶት እንደ ሆነ ወን​ዶች ወይም ሴቶች ልጆች ብት​ወ​ል​ድ​ለት፥ ሚስ​ቱና ልጆቹ ለጌ​ታው ይገዙ፤ እር​ሱም ብቻ​ውን ነጻ ይውጣ። 5ባሪ​ያ​ውም፦ ጌታ​ዬን፥ ሚስ​ቴን፥ ልጆ​ች​ንም እወ​ድ​ዳ​ለሁ፤ አር​ነ​ትም አል​ወ​ጣም ብሎ ቢና​ገር፥ 6ጌታው ወደ ቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈራ​ጆች ይው​ሰ​ደው፤ ወደ ደጁም፥ ወደ መቃ​ኑም አቅ​ርቦ አፍ​ን​ጫ​ውን#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “ጆሮ​ውን” ይላል። በወ​ስፌ ይብ​ሳው፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ባሪ​ያው ይሁ​ነው።
7“ሴት ልጁን ለባ​ር​ነት አሳ​ልፎ የሰጠ ቢኖር ሴቶች ባሪ​ያ​ዎች አር​ነት እን​ደ​ሚ​ወጡ እር​ስዋ ትውጣ። 8ለእ​ርሱ ከታ​ጨች በኋላ ጌታ​ዋን ደስ ባታ​ሰ​ኘው በዎጆ ይስ​ደ​ዳት፤ ነገር ግን ለሌላ ወገን ይሸ​ጣት ዘንድ አይ​ገ​ባ​ውም። እርሱ አር​ክ​ሶ​አ​ታ​ልና። 9ለል​ጁም ሊድ​ራት ቢወ​ድድ፥ ለሴት ልጆች የሚ​ገ​ባ​ውን ያድ​ር​ግ​ላት፤ 10ከእ​ር​ስ​ዋም ሌላ ቢያ​ገባ፥ ቀለ​ብ​ዋን፥ ልብ​ስ​ዋ​ንም፥ ለጋ​ብ​ቻ​ዋም ተገ​ቢ​ውን ይስ​ጣት፤ እን​ዳ​ል​በ​ደ​ላ​ትም ምስ​ክር ያሰ​ማ​ባት።#“እን​ዳ​ል​በ​ደ​ላ​ትም ምስ​ክር ያሰ​ማ​ባት” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. የለም። 11ይህ​ንም ሦስት ነገር ባያ​ደ​ር​ግ​ላት ያለ ገን​ዘብ ነጻ ትውጣ።
ዐመ​ፀ​ኞች የሚ​ቀ​ጡ​በት ሕግ
12“ሰው ሰውን ቢመታ፥ ቢሞ​ትም፥ የመ​ታው ፈጽሞ ይገ​ደል። 13ሳይ​ፈ​ቅድ ቢመ​ታው፥ ባይ​ሸ​ም​ቅ​በ​ትም፥ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድን​ገት በእጁ ቢጥ​ለው፥ ገዳዩ የሚ​ሸ​ሽ​በ​ትን ስፍራ እኔ አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለሁ። 14ሰው ግን ቢሸ​ምቅ ጠላ​ቱ​ንም በተ​ን​ኰል ቢገ​ድ​ለ​ውና ቢማ​ፀን፥ እን​ዲ​ገ​ደል ከመ​ሠ​ዊ​ያዬ አው​ጥ​ተህ ውሰ​ደው።
15“አባ​ቱን ወይም እና​ቱን የሚ​ማታ ይገ​ደል።
16“አባ​ቱን ወይም እና​ቱን የሚ​ሰ​ድብ በሞት ይቀጣ።
17“ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አን​ዱን የሰ​ረቀ ወይም ግፍ የፈ​ጸ​መ​በት፥ ወይም አሳ​ልፎ ቢሰ​ጠው፥ ወይም በእ​ርሱ ዘንድ ቢገኝ፥ እርሱ ይገ​ደል።
18“ሁለት ሰዎ​ችም እርስ በር​ሳ​ቸው ቢጣሉ፥ አን​ዱም ሌላ​ውን በድ​ን​ጋይ ወይም በጡጫ ቢመታ፥ ያም ባይ​ሞት ነገር ግን በአ​ል​ጋው ላይ ቢተኛ፥ 19ተነ​ሥ​ቶም በም​ር​ኩዝ ወደ ሜዳ ቢወጣ፥ የመ​ታው ንጹሕ ነው፤ ነገር ግን ተግ​ባ​ሩን ስላ​ስ​ፈ​ታው ገን​ዘብ ይክ​ፈ​ለው፤ ለባለ መድ​ኀ​ኒ​ትም ይክ​ፈ​ል​ለት።
20“ሰውም ወንድ ባሪ​ያ​ውን ወይም ሴት ባሪ​ያ​ውን በበ​ትር ቢመታ፥ በእጁ ቢሞ​ት​በ​ትም፥ ፈጽሞ ይቀጣ፤#ግዕዙ “ይገ​ደል” ይላል። 21የተ​መ​ታው ግን አንድ ወይም ሁለት ቀን ቢቈይ ገን​ዘቡ ነውና አይ​ቀጣ።#ግእዙ “ከሞት ይድ​ናል” ይላል።
22“ሁለት ሰዎች እርስ በር​ሳ​ቸው ቢጣሉ፥ ያረ​ገ​ዘ​ች​ንም ሴት ቢያ​ቈ​ስሉ ተሥ​ዕ​ሎተ መል​ክእ ያል​ተ​ፈ​ጸ​መ​ለት ፅን​ስም ቢያ​ስ​ወ​ር​ዳት፥ የሴ​ቲቱ ባል የጣ​ለ​በ​ትን ያህል ካሳ ይክ​ፈል፤ 23ተሥ​ዕ​ሎተ መል​ክእ የተ​ፈ​ጸ​መ​ለት ፅንስ ቢያ​ስ​ወ​ር​ዳት ግን ሕይ​ወት በሕ​ይ​ወት፥ 24ዐይን በዐ​ይን፥ ጥርስ በጥ​ርስ፥ እጅ በእጅ፥ እግር በእ​ግር፥ 25መቃ​ጠል በመ​ቃ​ጠል፥ ቍስል በቍ​ስል፥ ግር​ፋት በግ​ር​ፋት ይክ​ፈል።
26“ሰውም የባ​ሪ​ያ​ውን ዐይን ወይም የባ​ሪ​ያ​ዪ​ቱን ዐይን ቢመታ፥ ቢያ​ጠ​ፋ​ውም፥ ስለ ዐይ​ና​ቸው አር​ነት ያው​ጣ​ቸው። 27የባ​ሪ​ያ​ውን ጥርስ ወይም የባ​ሪ​ያ​ዪ​ቱን ጥርስ ቢሰ​ብር፥ ስለ ጥር​ሳ​ቸው አር​ነት ያው​ጣ​ቸው።
ስለ ንብ​ረት የተ​ሰጠ ሕግ
28“በሬም ወን​ድን ወይም ሴትን ቢወጋ ቢሞ​ቱም፥ በሬው በድ​ን​ጋይ ይወ​ገር፤ ሥጋ​ውም አይ​በላ፤ የበ​ሬው ባለ​ቤት ግን ንጹሕ ነው። 29በሬው ግን ከት​ና​ን​ትና ከት​ና​ንት ወዲያ ተዋጊ ቢሆን፥ ሰዎ​ችም ለባ​ለ​ቤቱ ቢመ​ሰ​ክ​ሩ​ለት ባያ​ስ​ወ​ግ​ደ​ውም፥ ወን​ድን ወይም ሴትን ቢገ​ድል፥ በሬው ይወ​ገር፤ ባለ​ቤቱ ደግሞ ይገ​ደል። 30ከእ​ርሱ ግን ካሳ ቢፈ​ልጉ፥ የሕ​ይ​ወ​ቱን ካሳ የጫ​ኑ​በ​ትን ያህል ይስጥ። 31በሬው ወን​ድን ልጅ ቢወጋ፥ ሴት​ንም ልጅ ቢወጋ ይህ​ንኑ ፍርድ ያድ​ር​ጉ​በት። 32በሬው ወንድ ባሪያ ወይም ሴት ባሪያ ቢወጋ፥ የበ​ሬው ባለ​ቤት ሠላሳ የብር ሰቅል ለጌ​ታ​ቸው ይስጥ፤ በሬ​ውም ይወ​ገር።
33“ሰውም ጕድ​ጓድ ቢከ​ፍት ወይም ጕድ​ጓድ ቢቈ​ፍር ባይ​ከ​ድ​ነ​ውም፥ በሬም ወይም አህያ፤ ቢወ​ድ​ቅ​በት፥ 34የጕ​ድ​ጓዱ ባለ​ቤት ዋጋ​ቸ​ውን ለባ​ለ​ቤ​ታ​ቸው ይክ​ፈል፤ የሞ​ተ​ውም ለእ​ርሱ ይሁን።
35“የሰው በሬ የሌ​ላ​ውን በሬ ቢወጋ፥ ቢሞ​ትም፥ ደኅ​ና​ውን በሬ ይሽጡ፤ ዋጋ​ው​ንም በት​ክ​ክል ይካ​ፈሉ፤ የሞ​ተ​ው​ንም ደግሞ በት​ክ​ክል ይካ​ፈሉ። 36በሬ​ውም ትና​ን​ትና ከት​ና​ንት ወዲያ ተዋጊ መሆኑ ቢታ​ወቅ ለባ​ለ​ቤ​ቱም ቢመ​ሰ​ክ​ሩ​ለት፥ ባለ​ቤ​ቱም ባያ​ስ​ወ​ግ​ደው በሬ​ውን በበ​ሬው ፋንታ ይስጥ፤ የሞ​ተ​ውም ለእ​ርሱ ይሁ​ነው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ