ኦሪት ዘፀአት 22
22
ስለ ዕዳ አከፋፈል
1“ሰው በሬ ወይም በግ ቢሰርቅ፥ ቢያርደው ወይም ቢሸጠው፥ በአንድ በሬ ፋንታ አምስት በሬዎች፥ በአንድ በግም ፋንታ አራት በጎች ይክፈል። 2ሌባ ቤት ሲምስ ቢገኝ፥ እርሱም ቢመታ፥ ቢሞትም በመታው ሰው ላይ የደም ዕዳ አይሆንበትም። 3ፀሐይ ግን ከወጣችበት የደም ዕዳ አለበት፤ የገደለው ይገደል፤#ዕብ. “ሌባው የሰረቀውን ይመልስ” ይላል። ሌባው ቢያዝ የሚከፍለውም ቢያጣ ስለ ሰረቀው ይሸጥ። 4የሰረቀው ደኅና ሆኖ በእጁ ቢገኝ፥ በሬ ወይም በግ ቢሆን፥ የሰረቀውን ያህል ሁለት እጥፍ ይክፈል።
5“የሰውን አዝመራ ከብቱን ያስበላ፥ የሌላ ሰው ወይንንም ያስበላ ሰው ቢኖር ግምቱን ይክፈል። የሰውን አዝመራ ፈጽሞ ቢያስበላ ግን በአጠገቡ ባለ አዝመራ ልክ ይክፈል፤ ወይንም ቢሆን በአጠገቡ ባለ ወይን ልክ ይክፈል።
6“እሳት ቢነሣ ጫካውንም ቢይዝ፥ ዐውድማውንም፥ ክምሩንም ወይም ያልታጨደውን እህል ወይም እርሻውን ቢያቃጥል እሳቱን ያነደደው ይክፈል።
7“ሰው በባልንጀራው ዘንድ ብር ወይም ሌላ ዕቃ እንዲጠብቅለት አደራ ቢያኖር ከቤቱም ቢሰረቅ፥ ሌባው ቢገኝ እጥፍ ይክፈል። 8ሌባው ባይገኝ ባለቤቱ ወደ ፈጣሪ ፊት ይቅረብ፤ ባልንጀራው አደራ በአስቀመጠበት ገንዘብም ላይ እንዳልተተነኰለና ክፉ እንዳላሰበ ይማል።#ዕብ. “በባልንጀራው ከብት ላይ እጁን እንዳልዘረጋ ይማል” ይላል። 9ሰዎች ስለ በሬ ወይም ስለ አህያ ወይም ስለ በግ ወይም ስለ ልብስ ወይም ስለሌላ ስለ ጠፋ ነገር ቢካሰሱ፥ አንዱም፦ ‘ይህ የእኔ ነው’ ቢል፥ ክርክራቸው በፈጣሪ ፊት#ዕብ. “በዳኞች ፊት” ይላል። ይቅረብ፤ በፈጣሪ ፊት የተፈረደበት እርሱ ለባልንጀራው እጥፍ ይክፈል።
10“ሰው በባልንጀራው ዘንድ አህያ ወይም በሬ ወይም በግ ወይም ሌላ እንስሳ እንዲጠብቅለት አደራ ቢያኖር፥ ማንም ሳያይ ቢሞት ወይም ቢጐዳ ወይም ቢማረክ፥ 11በባልንጀራው ከብት ላይ እጁን እንዳልዘረጋ የእግዚአብሔር መሐላ በሁለታቸው መካከል ይሁን፤ የከብቱም ባለቤት ይህን ከተቀበለ፥ እርሱ ምንም አይክፈል። 12ከእርሱም ዘንድ ቢሰረቅ ለባለቤቱ ይክፈል። 13በምድረ በዳም አውሬ ቢበላው ውዳቂውን ያሳይ፤ አይክፈልም። 14ሰው ከባልንጀራው አንዳች ቢዋስ ባለቤቱ ከእርሱ ጋር ሳይኖር ቢጎዳ፥ ወይም ቢሞት፥ ወይም ቢነጠቅ ፈጽሞ ይክፈለው። 15ባለቤቱ ግን ከእርሱ ጋር ቢኖር አይክፈል፤ ቢከራየውም ኪራዩን ይክፈል።
ማኅበራዊና ሃይማኖታዊ ሕጎች
16“ሰው ያልታጨችውን ድንግል ቢያስታት፥ ከእርስዋም ጋር ቢተኛ ሚስት አድርጎ ይውሰዳት።#ዕብ. “ማጫዋን ሰጥቶ ሚስት ያድርጋት” ይላል። 17አባቷም እርስዋን እንዳይሰጠው ፈጽሞ እንቢ ቢል እንደ ደናግል ማጫ ያህል ማጫዋን ይስጠው።
18“ከመተተኛ ጋር አንድ አትሁኑ።
19“ከእንስሳ የሚደርስ ሁሉ ሞትን ይሙት።
20“ከእግዚአብሔር ብቻ በቀር ለአማልክት የሚሠዋ ፈጽሞ ይጥፋ። 21እናንተ በግብፅ ምድር ስደተኞች ነበራችሁና ስደተኛውን አትበድሉት፤ ግፍም አታድርጉበት። 22መበለቲቱንና ድሀ-አደጎቹን አታስጨንቁአቸው። 23ብታስጨንቁአቸውና ወደ እኔ ቢጮኹ እኔ ጩኸታቸውን ፈጽሞ እሰማለሁ፤ 24ቍጣዬም ይጸናባችኋል፤ በሰይፍም አስገድላችኋለሁ፤ ሚስቶቻችሁም መበለቶች፥ ልጆቻችሁም ድሀ-አደጎች ይሆናሉ።
25“ከአንተ ጋር ለተቀመጠው ለድሃው ወገንህ ብር ብታበድረው፥ አታስጨንቀው፤ አራጣም አታስከፍለው። 26የባልንጀራህን ልብስ ለመያዣ ብትወስድ ፀሐይ ሳትገባ መልስለት፤ 27ልብሱ ነውና፥ ዕርቃኑንም የሚሸፍንበት ይህ ብቻ ነውና፤ የሚተኛበትም ሌላ የለውምና፤ ወደ እኔም ቢጮኽ ፈጥኜ እሰማዋለሁ፤ መሓሪ ነኝና።
28“ፈራጆችን አትስደብ፥ የሕዝብህንም አለቃ ክፉ አትናገረው። 29የአውድማህንና የወይንህንም መጀመሪያ ለማቅረብ አትዘግይ፤ የልጆችህንም በኵር ትሰጠኛለህ። 30እንዲሁም በበሬዎችህና በበጎችህ፥ በአህያህም ታደርገዋለህ፤ ሰባት ቀን ከእናቱ ጋር ይቀመጥ፤ በስምንተኛውም ቀን ለእኔ ትሰጠዋለህ። 31ቅዱስ ወገን ትሆኑልኛላችሁ፤ ስለዚህ አውሬ የገደለውን ሥጋ ለውሻ ጣሉት እንጂ አትብሉት።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፀአት 22: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ