ኦሪት ዘፀአት 23
23
ትክክለኛ ፍርድ
1“ሐሰተኛ ወሬ አትቀበል፤ የዐመፅ ምስክርም ትሆን ዘንድ ከዐመፀኛ ጋር አትቀመጥ። 2ለዐመፅ ከብዙ ሰው ጋር አንድ አትሁን፤ ፍርድንም ለማጣመም ከብዙ ሰው ጋር አትጨመር። 3በፍርድ ለድሀው አትራራ።
4“የጠላትህን በሬ ወይም አህያውን ጠፍቶ ብታገኘው ፈጽሞ መልስለት። 5የጠላትህን አህያ ከጭነቱ በታች ወድቆ ብታገኘው አትለፈው፤ ነገር ግን ከእርሱ ጋር ለማንሣት ርዳው።
6“በፍርድ የድሀውን ፍርድ አታጣምም። 7ከዐመፅ ፍርድ ሁሉ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከዐመፅ ነገር ሁሉ” ይላል። ራቅ፤ በደል የሌለበትንና ጻድቅን አትግደል፤ ኀጢአተኛውንም በመማለጃ አታድን፤ 8መማለጃን አትቀበል፤ መማለጃ የዐይናማዎችን ዐይን ያሳውራልና፥ እውነተኛ ቃልንም ያጣምማልና። 9በስደተኛው ግፍ አታድርጉ፤ እናንተ በግብፅ ምድር ስደተኞች ስለ ነበራችሁ የስደተኛ ነፍስ እንዴት እንደ ሆነች ዐውቃችኋልና።
ሰባተኛው ዓመትና ሰባተኛው ቀን
10“ስድስት ዓመት ምድርህን ዝራ፤ ፍሬዋንም አግባ፤ 11በሰባተኛው ዓመት ግን ተዋት፤ አሳርፋትም፤ የሕዝብህም ድሆች ይበሉታል፤ እነርሱ ያስቀሩትንም የሜዳ እንስሳ ይብላው። እንዲሁም በወይንህና በወይራህ አድርግ። 12ስድስት ቀን ሥራህን ሁሉ ሥራ፤ በሬህና አህያህ ያርፉ ዘንድ ለባሪያህም ልጅ ለመጻተኛውም ዕረፍት ይሆን ዘንድ በሰባተኛው ቀን ዕረፍ። 13ያልኋችሁንም ነገር ሁሉ ጠብቁ፤ የሌሎችንም አማልክት ስም አትጥሩ፤ ከአፋችሁም አይሰማ።
ሦስቱ ዐበይት በዓላት
(ዘፀ. 34፥18-26፤ ዘዳ. 16፥1-17)
14“በዓመት ሦስት ጊዜ በዓል አድርጉልኝ። 15የቂጣውን በዓል ጠብቁ፤ በአዲስ ወር ከግብፅ ምድር ወጥታችኋልና በዚህ ወር እንዳዘዝኋችሁ ሰባት ቀን ቂጣ ትበላላችሁ። 16በፊቴ ባዶ እጅህን አትታይ። በእርሻም የምትዘራትን የፍሬህን በኵራት የመከር በዓል፥ ዓመቱም ሲያልቅ ፍሬህን ከእርሻ ባከማቸህ ጊዜ የመክተቻውን በዓል ጠብቅ። 17በዓመት ሦስት ጊዜ በአንተ ዘንድ ያለው ወንድ ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ይታይ።
18“የመሥዋዕቴን ደም ከቦካ እንጀራ ጋር አትሠዋ፤ የበዓሌም ስብ እስኪነጋ አይደር። 19የምድርህን ፍሬ በኵራት ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጣ። ጠቦትን በእናቱ ወተት አትቀቅል።
የተስፋዋን ምድር እንደሚወርሱ የተሰጠ ቃል ኪዳን
20“በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ፥ ወዳዘጋጀሁልህም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ፥ እኔ መልአኬን በፊትህ እልካለሁ። 21ራስህን ጠብቅ፤ ስማው፤ እንቢም አትበለው፤ ስሜ በእርሱ ስለ ሆነ ይቅር አይልምና። 22አንተ ግን ቃሌን ብትሰማ፥ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ቃል ኪዳኔንም ብትጠብቁ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጠ ርስት ትሆኑኛላችሁ እናንተም የካህናት መንግሥት፥ የተቀደሰም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ ፤ ለእስራኤልም ልጆች የምነግራቸው ቃል ይህ ነው ቃሌንም ብትሰማ፥ ያልሁህንም ብታደርግ” የሚለውን ከምዕ. 19 ቍ. 5 እና 6ን አምጥቶ በምዕ. 23 ቍ. 22 ውስጥ አስገብቶ ይጽፋል። ጠላቶችህን እጥላቸዋለሁ፤ የሚቃወሙህንም እቃወማለሁ። 23መልአኬ በፊትህ ይሄዳልና፥ ወደ አሞሬዎናውያንም፥ ወደ ኬጤዎናውያንም፥ ወደ ፌርዜዎናውያንም፥ ወደ ከነዓናውያንም፥ ወደ ጌርጌሴዎናውያንም፥ ወደ ኤዌዎናውያንም፥ ወደ ኢያቡሴዎናውያንም ያገባሃል፤ እኔም አጠፋቸዋለሁ። 24ለአማልክቶቻቸው አትስገድ፤ አታምልካቸውም፤ እንደ ሥራቸውም አትሥራ፤ ነገር ግን ፈጽመህ አፍርሳቸው፤ ምስሎቻቸውንም ሰባብራቸው። 25አምላክህንም እግዚአብሔርን ታመልካለህ፤ እኔ እህልህንና ወይንህን፥ ውኃህንም እባርካለሁ፤ በሽታንም ከአንተ አርቃለሁ። 26በምድርህም መካን፥ ወይም የማይወልድ አይኖርም፤ የዘመንህንም ቍጥር እሞላለሁ። 27በፊትህ መፈራትን እሰድዳለሁ፤ የምትሄድበትን ሕዝብ ሁሉ አስደነግጣቸዋለሁ፤ ጠላቶችህንም ሁሉ እንዲሸሹልህ አደርጋለሁ። 28በፊትህም ተርብ እሰድዳለሁ፤ አሞራዊውንም፥ ኤዌዎያዊውንም፥ ከነዓናዊውንም፥ ኬጤዎናዊውንም ከፊትህ ያባርራቸዋል። 29ምድር ባድማ እንዳትሆን፥ የምድር አራዊትም እንዳይበዙብህ፥ በአንድ ዓመት አላባርራቸውም። 30ነገር ግን እስክትበዛ፥ ምድርንም እስክትወርስ ድረስ ጥቂት በጥቂት አባርራቸዋለሁ። 31ድንበርህንም ከኤርትራ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፥ ከምድረ በዳም እስከ ታላቁ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ አሰፋለሁ፤ በምድር የሚኖሩትን በእጅህ እጥላለሁና፤ ከአንተም አስወጣቸዋለሁ። 32ከእነርሱና ከአማልክቶቻቸው ጋር ቃል ኪዳን አታድርግ። 33እኔን እንድትበድል እንዳያደርጉህ በሀገርህ ላይ አይቀመጡ፤ አማልክቶቻቸውንም ብታመልክ ወጥመድ ይሆኑብሃልና።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘፀአት 23: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ