የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፀ​አት 26

26
ስለ ተቀ​ደ​ሰው ድን​ኳን
(ዘፀ. 36፥8-38)
1“ለድ​ን​ኳ​ኑም ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀ​ይም ግምጃ ዐሥር መጋ​ረ​ጆ​ችን ሥራ፤ ኪሩ​ቤ​ልም በእ​ነ​ርሱ ላይ ይሁኑ፤ እንደ ሽመና ሥራም በብ​ል​ሃት ትሠ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ። 2የእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ መጋ​ረጃ ርዝ​መት ሃያ ስም​ንት ክንድ፥ ወር​ዱም አራት ክንድ ይሁን፤ የመ​ጋ​ረ​ጆ​ችም ሁሉ መጠን ትክ​ክል ይሁን። 3አም​ስቱ መጋ​ረ​ጃ​ዎች እርስ በር​ሳ​ቸው የተ​ጋ​ጠሙ ይሁኑ፤ ሌሎ​ችም አም​ስት መጋ​ረ​ጃ​ዎች እን​ዲሁ እርስ በር​ሳ​ቸው የተ​ጋ​ጠሙ ይሁኑ።። 4ከሚ​ጋ​ጠ​ሙት መጋ​ረ​ጆች በአ​ን​ደ​ኛው መጋ​ረጃ ዘርፍ ላይ የሰ​ማ​ያ​ዊ​ውን ግምጃ ቀለ​በ​ቶች አድ​ርግ፤ ደግሞ ከተ​ጋ​ጠ​ሙት ከሌ​ሎች በአ​ን​ደ​ኛው መጋ​ረጃ ዘርፍ ላይ በውጭ በኩል እን​ዲሁ አድ​ርግ። 5አምሳ ቀለ​በ​ቶ​ችን በአ​ንድ መጋ​ረጃ አድ​ርግ፤ አም​ሳ​ው​ንም ቀለ​በ​ቶች በሁ​ለ​ተ​ኛው መጋ​ረጃ ዘርፍ አድ​ርግ፤ ቀለ​በ​ቶቹ ሁሉ እርስ በር​ሳ​ቸው ፊት ለፊት ይሆ​ናሉ። 6አምሳ የወ​ርቅ መያ​ዣ​ዎች ሥራ፤ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ችን እርስ በር​ሳ​ቸው በመ​ያ​ዣ​ዎች አጋ​ጥ​ማ​ቸው፤ ድን​ኳ​ኑም አንድ ይሆ​ናል።
7“ከማ​ደ​ሪ​ያ​ውም በላይ ለድ​ን​ኳን የሚ​ሆኑ መጋ​ረ​ጃ​ዎች ከፍ​የል ጠጕር አድ​ርግ፤ ዐሥራ አንድ መጋ​ረ​ጃ​ዎች ታደ​ር​ጋ​ለህ። 8እያ​ን​ዳ​ን​ዱም መጋ​ረጃ ርዝ​መቱ ሠላሳ ክንድ፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም መጋ​ረጃ ወርዱ አራት ክንድ ይሁን፤ የዐ​ሥራ አን​ዱም መጋ​ረ​ጃ​ዎች መጠ​ና​ቸው ትክ​ክል ይሁን። 9አም​ስቱ መጋ​ረ​ጃ​ዎች እርስ በር​ሳ​ቸው አንድ ሆነው ይጋ​ጠሙ፤ ስድ​ስ​ቱም መጋ​ረ​ጃ​ዎች እርስ በር​ሳ​ቸው አንድ ሆነው ይጋ​ጠሙ፤ ስድ​ስ​ተ​ኛ​ውም መጋ​ረጃ በድ​ን​ኳኑ ፊት ይደ​ረብ። 10በውጭ ከተ​ጋ​ጠ​ሙት መጋ​ረ​ጃ​ዎች በአ​ን​ደ​ኛው መጋ​ረጃ ዘርፍ ላይ አምሳ ቀለ​በ​ቶች አድ​ርግ፤ ደግሞ ከተ​ጋ​ጠ​ሙት ከሌ​ሎቹ በአ​ን​ደ​ኛው መጋ​ረጃ ዘርፍ ላይ እን​ዲሁ አምሳ ቀለ​በ​ቶች አድ​ርግ። 11አም​ሳም የናስ መያ​ዣ​ዎ​ችን ሥራ፤ መያ​ዣ​ዎ​ች​ንም ወደ ቀለ​በ​ቶች አግ​ባ​ቸው፤ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ች​ንም አጋ​ጥ​ማ​ቸው፤ አን​ድም ይሆ​ናሉ። 12ከድ​ን​ኳኑ መጋ​ረ​ጃ​ዎች የቀረ ትርፍ ግማሽ መጋ​ረጃ በድ​ን​ኳኑ ጀርባ ይጋ​ረድ። 13ድን​ኳ​ኑን እን​ዲ​ሸ​ፍን ከር​ዝ​መቱ በአ​ንድ ወገን አንድ ክንድ፤ በአ​ንድ ወገ​ንም አንድ ክንድ ከድ​ን​ኳኑ መጋ​ረ​ጆች የቀ​ረው ትርፍ በድ​ን​ኳኑ ውጭ በወ​ዲ​ህና በወ​ዲያ ይጋ​ረድ። 14ለድ​ን​ኳ​ኑም መደ​ረ​ቢያ ከቀይ አውራ በግ ቍር​በት፥ ከዚ​ያም በላይ ሌላ መደ​ረ​ቢያ ከአ​ቆ​ስጣ ቍር​በት አድ​ርግ።
15“ለድ​ን​ኳ​ኑም ሳን​ቆ​ችን ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት አድ​ርግ። 16የእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሳንቃ ርዝ​መቱ ዐሥር ክንድ፥ ወር​ዱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን። 17ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሳንቃ አን​ዱን በአ​ንዱ ላይ የሚ​ያ​ያ​ይዙ ሁለት ማጋ​ጠ​ሚ​ያ​ዎች ይሁ​ኑ​ለት፤ ለድ​ን​ኳኑ ሳን​ቆች ሁሉ እን​ዲሁ አድ​ርግ። 18ለድ​ን​ኳ​ኑም በደ​ቡብ በኩል ሃያ ሳን​ቆ​ችን አድ​ርግ። 19ከሃ​ያ​ውም ሳን​ቆች በታች አርባ የብር እግ​ሮ​ችን አድ​ርግ፤ ከእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ሳንቃ በታች ለሁ​ለት ማጋ​ጠ​ሚ​ያ​ዎች ሁለት እግ​ሮች ይሁኑ። ከሌ​ላ​ውም ሳንቃ በታች ለሁ​ለት ማጋ​ጠ​ሚ​ያ​ዎች ሁለት እግ​ሮች ይሁኑ። 20ለድ​ን​ኳኑ ለሁ​ለ​ተ​ኛው ወገን በሰ​ሜን በኩል ሃያ ሳን​ቆች፥ 21ለእ​ነ​ር​ሱም አርባ የብር እግ​ሮች ይሁኑ፤ ከእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሳንቃ በታች ሁለት እግ​ሮች ይሁኑ። 22ለድ​ን​ኳ​ኑም በም​ዕ​ራቡ በኩል በስ​ተ​ኋላ ስድ​ስት ሳን​ቆች አድ​ርግ። 23ለድ​ን​ኳ​ኑም ለሁ​ለቱ ማዕ​ዘን በስ​ተ​ኋላ ሁለት ሳን​ቆች አድ​ርግ። 24ከታ​ችም እኩል ይሁኑ፤ ከላይ እስከ አን​ደ​ኛው መጋ​ጠ​ሚያ ድረስ እንደ አን​ደኛ ክፍል እኩል ይሁኑ፤ እን​ዲ​ሁም ለሁ​ለቱ ማዕ​ዘን አድ​ርግ፤ እኩ​ልም ይሁኑ። 25ስም​ንት ሳን​ቆ​ችና ዐሥራ ስድ​ስት የብር እግ​ሮ​ቻ​ቸው ይሁኑ፤ ከእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሳንቃ በታች በሁ​ለ​ቱም መጋ​ጠ​ሚ​ያ​ዎች ሁለት ሁለት እግ​ሮች ይሆ​ናሉ።
26“ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ችን ሥራ፤ በድ​ን​ኳኑ በአ​ን​ደ​ኛው ገጽ ላሉ ሳን​ቆች አም​ስት መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ችን፥ 27በድ​ን​ኳኑ በሁ​ለ​ተኛ ወገን ላሉት ሳን​ቆች አም​ስት መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ችን፥ በድ​ን​ኳ​ኑም በስ​ተ​ኋላ በም​ዕ​ራብ በኩል ላሉት ሳን​ቆች አም​ስት መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ችን አድ​ርግ። 28መካ​ከ​ለ​ኛ​ውም መወ​ር​ወ​ሪያ በሳ​ን​ቆቹ መካ​ከል ከዳር እስከ ዳር ይለፍ። 29ሳን​ቆ​ቹን በወ​ርቅ ለብ​ጣ​ቸው፤ ቀለ​በ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም የመ​ወ​ር​ወ​ሪያ ቤት እን​ዲ​ሆ​ኑ​ላ​ቸው ከወ​ርቅ ሥራ​ቸው፤ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ንም በወ​ርቅ ለብ​ጣ​ቸው። 30ድን​ኳ​ኑ​ንም በተ​ራ​ራው ላይ በአ​ሳ​የ​ሁህ ምሳሌ ሥራ።
31“መጋ​ረ​ጃ​ው​ንም ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀ​ይም ግምጃ ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍ​ታም አድ​ርግ፤ በሽ​መና ሥራም ኪሩ​ቤ​ልን ሥራ። 32በወ​ርቅ በተ​ለ​በ​ጡት፥ ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨ​ትም በተ​ሠ​ሩት በአ​ራቱ ምሰ​ሶ​ዎች ላይ ስቀ​ለው፤ ኩላ​ቦ​ቻ​ቸ​ውም ከወ​ርቅ፥ አራ​ቱም እግ​ሮ​ቻ​ቸው ከብር የተ​ሠሩ ይሁኑ። 33መጋ​ረ​ጃ​ው​ንም በም​ሰ​ሶ​ዎች ላይ ስቀ​ለው፤ በመ​ጋ​ረ​ጃ​ውም ውስጥ የም​ስ​ክ​ሩን ታቦት አግ​ባው፤ መጋ​ረ​ጃ​ውም በቅ​ድ​ስ​ቱና በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ መካ​ከል መለያ ይሁ​ና​ችሁ። 34መጋ​ረ​ጃ​ውም የም​ስ​ክ​ሩን ታቦት በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ውስጥ ይጋ​ርድ።#ዕብ. “በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ውስጥ የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውን በም​ስ​ክሩ ታቦት ላይ አድ​ርግ” ይላል። 35ገበ​ታ​ው​ንም በመ​ጋ​ረ​ጃው ውጭ፥ መቅ​ረ​ዙ​ንም በገ​በ​ታው ፊት ለፊት በድ​ን​ኳኑ በደ​ቡብ ወገን አድ​ርግ፤ ገበ​ታ​ው​ንም በድ​ን​ኳኑ በሰ​ሜን ወገን አድ​ር​ገው። 36ለድ​ን​ኳኑ ደጃ​ፍም ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀይ ግም​ጃም ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍ​ም​ታም በጥ​ልፍ አሠ​ራር የተ​ሠራ መጋ​ረጃ አድ​ር​ግ​ለት። 37ለመ​ጋ​ረ​ጃ​ውም አም​ስት ምሰ​ሶ​ዎች ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት አድ​ርግ፤ በወ​ር​ቅም ለብ​ጣ​ቸው፤ ኩላ​ቦ​ቻ​ቸ​ውም ከወ​ርቅ የተ​ሠሩ ይሁኑ፤ አም​ስ​ትም የናስ እግ​ሮች አድ​ር​ግ​ላ​ቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ