ኦሪት ዘፀአት 27
27
የመሠውያው አሠራር
(ዘፀ. 38፥1-7)
1“ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱም አምስት ክንድ መሠዊያን ከማይነቅዝ ዕንጨት አድርግ፤ አራት ማዕዘንም ይሁን፤ ከፍታውም ሦስት ክንድ ይሁን። 2በአራቱም ማዕዘን ቀንዶችን ታደርጋለህ፤ ቀንዶቹ ሥረ-ወጥ ይሁኑ፤ በናስም ለብጣቸው። 3ለመሠዊያው ክዳን ሥራለት፤ መሸፈኛውን፥ ጽዋዎቹን፥ የሥጋ ሜንጦዎቹን፥ የእሳት መጫሪያዎቹንም አድርግ። ዕቃውንም ሁሉ ከናስ አድርግ። 4ለመሠዊያውም እንደ መረብ ሆኖ የተሠራ የናስ መከታ አድርግለት፤ ለመከታውም አራት የናስ ቀለበት በአራት ማዕዘኑ አድርግለት። 5መከታውም እስከ መሠዊያው እኩሌታ ይደርስ ዘንድ ከመሠዊያው እርከን በታች አኑረው። 6ለመሠዊያውም ከማይነቅዝ ዕንጨት መሎጊያዎችን ሠርተህ በናስ ለብጣቸው፤ መሎጊያዎቹም በቀለበቶች ውስጥ ይግቡ፤ 7መሠዊያውንም ስትሸከሙ መሎጊያዎቹ በመሠዊያው በሁለት ወገን ይሁኑ። 8ሰሌዳውም ፍልፍል ይሁን፤ በተራራው እንዳሳየሁህ ምሳሌ እንዲሁ አድርግ።
የቤተ እግዚአብሔር አደባባይ
(ዘፀ. 38፥9-20)
9“ለድንኳኑም አደባባይ ሥራ፤ ከጥሩ በፍታ የተሠሩ የአደባባዩ መጋረጃዎችም በደቡብ በኩል ይሁኑ። የአንዱም ወገን ርዝመት መቶ ክንድ ይሁን፤ 10ከናስ የተሠሩ ሃያ ምሰሶዎችና ሃያ እግሮች ይሁኑለት፤ የምሰሶዎቹም ኩላቦችና ዘንጎች የብር ይሁኑ። 11እንዲሁም በሰሜን ወገን መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች፥ ከናስ የተሠሩ ሃያ ምሰሶዎች፥ ሃያም እግሮች ይሁኑ፤ ለምሰሶዎችም በብር የተለበጡ ኩላቦችና ዘንጎች ይሁኑ። 12በምዕራብም ወገን ለአደባባዩ ስፋት አምሳ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች፥ ዐሥርም ምሰሶዎች፥ ዐሥርም እግሮች ይሁኑለት። 13በምሥራቅም ወገን የአደባባዩ ስፋት አምሳ ክንድ ይሁን፤ ምሰሶዎችም ዐሥር፥ እግሮቹም ዐሥር ይሁኑ። 14በአንድ ወገን የመጋረጃዎቹ ርዝመት ዐሥራ አምስት ክንድ ይሁን፤ ምሰሶዎቹም ሦስት፥ እግሮቹም ሦስት ይሁኑ። 15በሌላውም ወገን የመጋረጃዎቹ ርዝመት ዐሥራ አምስት ክንድ ይሆናል፤ ምሰሶዎቹም ሦስት፥ እግሮቹም ሦስት ይሁኑ። 16ለአደባባዩ ደጅም ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ ከጥሩ በፍታም በጥልፍ አሠራር የተሠራ ሃያ ክንድ መጋረጃ ይሆናል፤ ምሰሶዎቹም አራት፥ እግሮቹም አራት ይሁኑ። 17በዙሪያውም ያሉ የአደባባዩ ምሰሶዎች ሁሉ በብር የተለበጡ ይሁኑ፤ የብርም ክባሶች፥ የናስም እግሮች ይሁኑላቸው። 18የአደባባዩ ርዝመት በየገጹ መቶ ክንድ፥ ስፋቱም በየገጹ አምሳ ክንድ ይሁን፤ የመጋረጃውም ከፍታ አምስት ክንድ ይሁን፤ መጋረጃውም ከጥሩ በፍታ፥ እግሮቹም ከናስ የተሠሩ ይሁኑ። 19ለማገልገል ሁሉ የድንኳን ዕቃ ሁሉ፥ አውታሮቹ ካስማዎቹም ሁሉ፤ የአደባባዩም ካስማዎች ሁሉ የናስ ይሁኑ።
የመብራቱ ዘይት
(ዘሌ. 24፥1-4)
20“አንተም መብራቱን ሁል ጊዜ ያበሩት ዘንድ ለመብራት ተወቅጦ የተጠለለ ጥሩ የወይራ ዘይት እንዲያመጡልህ የእስራኤልን ልጆች እዘዛቸው። 21በምስክሩ ድንኳን ውስጥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ካለው መጋረጃ ውጭ አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት ያብሩት፤ በእስራኤል ልጆች ዘንድ ለልጅ ልጃቸው የዘለዓለም ሥርዐት ይሁን።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፀአት 27: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ