የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፀ​አት 32

32
የወ​ርቅ ጥጃው ምስል
(ዘዳ. 9፥6-29)
1ሕዝ​ቡም ሙሴ ከተ​ራ​ራው ሳይ​ወ​ርድ እንደ ዘገየ ባዩ ጊዜ፥ ወደ አሮን ተሰ​ብ​ስ​በው፥ “ይህ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣን ሰው ሙሴ ምን እንደ ሆነ አና​ው​ቅ​ምና ተነ​ሥ​ተህ በፊ​ታ​ችን የሚ​ሄዱ አማ​ል​ክት ሥራ​ልን” አሉት። 2አሮ​ንም፥ “በሚ​ስ​ቶ​ቻ​ች​ሁና በሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ችሁ ጆሮ ያሉ​ትን የወ​ርቅ ጌጦች አም​ጡ​ልኝ” አላ​ቸው። 3ሕዝ​ቡም ሁሉ በጆ​ሮ​ዎ​ቻ​ቸው ያሉ​ትን የወ​ርቅ ጌጦች ወደ አሮን አመ​ጡ​ለት። 4ከእ​ጃ​ቸ​ውም ተቀ​ብሎ በመ​ቅ​ረጫ ቀረ​ጸው፤ ቀልጦ የተ​ሠራ ጥጃም አደ​ረ​ገው፤ እር​ሱም፥ “እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እነ​ዚህ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጡህ አማ​ል​ክ​ትህ ናቸው” አላ​ቸው። 5አሮ​ንም በአ​የው ጊዜ መሠ​ዊ​ያ​ውን በፊቱ ሠራ፤ አሮ​ንም፥ “ነገ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓል ነው” ሲል አወጀ። 6አሮ​ንም በነ​ጋው ማልዶ ተነሣ፤ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም ሠዋ፤ የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም አቀ​ረበ#ዕብ. “በበ​ነ​ጋው ማል​ደው ተነ​ሥ​ተው የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ሰዉ ፤ የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ትም አቀ​ረቡ” ይላል። ሕዝ​ቡም ሊበ​ሉና ሊጠጡ ተቀ​መጡ፤ ሊዘ​ፍ​ኑም ተነሡ።
7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን ተና​ገ​ረው እን​ዲ​ህም አለው፥ “ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ኻ​ቸው ሕዝ​ብህ በድ​ለ​ዋ​ልና ሂድ፤ ፈጥ​ነህ ውረድ። 8ካዘ​ዝ​ኋ​ቸው መን​ገድ ፈጥ​ነው ፈቀቅ አሉ፤ ቀልጦ የተ​ሠራ የጥጃ ምስል ለራ​ሳ​ቸው አደ​ረጉ፤ ሰገ​ዱ​ለ​ትም፤ ሠዉ​ለ​ትም፤ 9‘እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እነ​ዚህ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጡህ አማ​ል​ክ​ትህ ናቸው’ አሉ።#ዕብ. “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ እኔ ይህን ሕዝብ አየ​ሁት ፤ እነ​ሆም አን​ገተ ደን​ዳና ሕዝብ ነው” የሚል ይጨ​ም​ራል። 10አሁ​ንም ተቈ​ጥቼ አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ተወኝ፤ አን​ተ​ንም ለታ​ላቅ ሕዝብ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ።” 11ሙሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ም​ላኩ ፊት ጸለየ፤ አለም፥ “አቤቱ፥ በታ​ላቅ ኀይ​ልና በጽኑ እጅ ከግ​ብፅ ምድር በአ​ወ​ጣ​ኸው በሕ​ዝ​ብህ ላይ ለምን ተቈ​ጣህ? 12ግብ​ፃ​ው​ያ​ንስ፦ ‘በተ​ራራ መካ​ከል ሊገ​ድ​ላ​ቸው፥ ከም​ድ​ርም ፊት ሊያ​ጠ​ፋ​ቸው ለክ​ፋት አወ​ጣ​ቸው’ ብለው ስለ ምን ይና​ገ​ራሉ? ከመ​ዓ​ትህ ተመ​ለስ፤ ለሕ​ዝ​ብ​ህም በክ​ፋ​ታ​ቸው ላይ ራራ። 13ዘራ​ች​ሁን እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት አበ​ዛ​ለሁ፤ ይህ​ች​ንም የተ​ና​ገ​ር​ኋ​ትን ምድር ሁሉ ለዘ​ራ​ችሁ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ይወ​ር​ሱ​አ​ታል ብለህ በራ​ስህ የማ​ል​ህ​ላ​ቸው ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህን አብ​ር​ሃ​ም​ንና ይስ​ሐ​ቅን ያዕ​ቆ​ብ​ንም ዐስብ።” 14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ዝቡ ላይ ሊያ​ደ​ርግ ስላ​ሰ​በው ክፋት ይቅር አለ።
15ሙሴም ተመ​ለሰ፤ ሁለ​ቱ​ንም የም​ስ​ክር ጽላት በእጁ ይዞ ከተ​ራ​ራው ወረደ፤ የድ​ን​ጋይ ጽላ​ቱም በዚ​ህና በዚያ በሁ​ለት ወገን ተጽ​ፎ​ባ​ቸው ነበር። 16ጽላቱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ ነበሩ፤ ጽሕ​ፈ​ቱም በጽ​ላቱ ላይ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ባ​ቸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽሕ​ፈት ነበረ። 17ኢያ​ሱም ሲጮሁ የሕ​ዝ​ቡን ድምፅ ሰምቶ ሙሴን፥ “የሰ​ልፍ ድምፅ በሰ​ፈሩ ውስጥ አለ” አለው። 18ሙሴም፥ “ይህ የድል ነሺ​ዎች ወይም የድል ተነ​ሺ​ዎች ድምፅ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን የወ​ይን ስካር ድምፅ እሰ​ማ​ለሁ” አለው። 19እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ወደ ሰፈሩ ሲቀ​ርብ ጥጃ​ው​ንም ዘፈ​ኑ​ንም አየ፤ የሙ​ሴም ቍጣ ተቃ​ጠለ፤ እነ​ዚ​ያ​ንም ሁለ​ቱን ጽላት ከእጁ ጥሎ ከተ​ራ​ራው በታች ሰበ​ራ​ቸው። 20የሠ​ሩ​ት​ንም ጥጃ ወስዶ በእ​ሳት አቀ​ለ​ጠው፤ ፈጨው፤ አደ​ቀ​ቀ​ውም፤ በው​ኃም ላይ በተ​ነው፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አጠ​ጣ​ቸው።
21ሙሴም አሮ​ንን፥ “ይህን ታላቅ ኀጢ​አት ታመ​ጣ​በት ዘንድ ይህ ሕዝብ ምን አደ​ረ​ገህ?” አለው። 22አሮ​ንም እን​ዲህ አለ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በእኔ ላይ አት​ቈጣ፤ የዚ​ህን ሕዝብ ጠባይ አንተ ታው​ቃ​ለህ። 23እነ​ር​ሱም ይህ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣን ሰው ሙሴ ምን እንደ ሆነ አና​ው​ቅ​ምና በፊ​ታ​ችን የሚ​ሄዱ አማ​ል​ክት ሥራ​ልን አሉኝ። 24እኔም ከእ​ና​ንተ ወርቅ ያለው ሰው ያም​ጣ​ልኝ አል​ኋ​ቸው፤ ሰጡ​ኝም፤ በእ​ሳ​ትም ላይ ጣል​ሁት፤ ይህም ጥጃ ወጣ።”
25ሙሴም በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ፊት እን​ዲ​ነ​ወሩ አሮን ስድ ለቅ​ቆ​አ​ቸ​ዋ​ልና ሕዝቡ ስድ እንደ ተለ​ቀቀ በአየ ጊዜ፥ 26ሙሴ በሰ​ፈሩ ደጅ ቆሞ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወገን የሆነ ወደ እኔ ይምጣ” አለ፤ የሌዊ ልጆች ሁሉ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ። 27እር​ሱም፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰይ​ፉን በወ​ገቡ ላይ ይታ​ጠቅ፤ ሂዱና በሰ​ፈሩ ውስጥ ከበር እስከ በር ተመ​ላ​ለሱ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወን​ድ​ሙን፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ጎረ​ቤ​ቱን፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም የቅ​ር​ቡን ይግ​ደል” አላ​ቸው። 28የሌ​ዊም ልጆች ሙሴ እን​ዳለ አደ​ረጉ፤ በዚ​ያም ቀን ከሕ​ዝቡ ሦስት ሺህ ሰዎች ሞቱ። 29ሙሴም፥ “ዛሬ በረ​ከ​ትን እን​ዲ​ያ​ወ​ር​ድ​ላ​ችሁ ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ ከል​ጁና፥ ከወ​ን​ድሙ የተ​ነሣ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በእ​ጃ​ችሁ ደስ አሰ​ኛ​ች​ሁት” አላ​ቸው።
30በነ​ጋ​ውም ሙሴ ለሕ​ዝቡ፥ “እና​ንተ ታላቅ በደል ሠር​ታ​ች​ኋል፤ አሁ​ንም አስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ችሁ ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እወ​ጣ​ለሁ፤” አላ​ቸው። 31ሙሴም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተመ​ልሶ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ እኒህ ሕዝብ ታላቅ ኀጢ​አት ሠር​ተ​ዋል፤ ለራ​ሳ​ቸ​ውም የወ​ርቅ አማ​ል​ክት አድ​ር​ገ​ዋል፤ 32አሁ​ንም ይህን ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይቅር ትላ​ቸው እን​ደ​ሆነ ይቅር በላ​ቸው፤ ያለ​ዚያ ግን ከጻ​ፍ​ኸው መጽ​ሐፍ ደም​ስ​ሰኝ” አለ። 33እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “በፊቴ የበ​ደ​ለ​ውን እር​ሱን ከመ​ጽ​ሐፌ እደ​መ​ስ​ሰ​ዋ​ለሁ። 34አሁ​ንም ሂድ፤ ይህ​ንም ሕዝብ ወደ ነገ​ር​ሁህ ቦታ ምራ፤ እነሆ፥ መል​አኬ በፊ​ትህ ይሄ​ዳል፤ ነገር ግን በም​ጐ​በ​ኝ​በት ቀን ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን አመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ” አለው። 35አሮን የሠ​ራ​ውን ጥጃ ስለ ሠሩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ቀሠፈ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ