ኦሪት ዘፀአት 33
33
እስራኤል ከሲና ተራራ እንደ ተነሡ
1እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፥ “ሂድ፤ አንተ ከግብፅ ከአወጣኸው ሕዝብህ ጋር ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ለዘራችሁ እሰጣታለሁ ብዬ ወደ ማልሁባት ምድር ውጣ። 2መልአኬንም ከአንተ ጋር በፊትህ እልካለሁ፤ ከነዓናዊውን፥ አሞሬዎናዊውንም፥ ኬጤዎናዊውንም፥ ፌርዜዎናዊውንም፥ ጌርጌሴዎናዊውን፥ ኤዌዎናውዊውንም፥ ኢያቡሴዎናዊውንም ያወጣቸዋል። 3ወተትና ማርም ወደምታፈስሰው ምድር አስገባሃለሁ፤ አንገተ ደንዳና ስለሆኑ ሕዝብህ በመንገድ ላይ እንዳላጠፋህ እኔ ከአንተ ጋር አልወጣም።” 4ሕዝቡም ይህን ክፉ ወሬ ሰምተው ታላቅ ኀዘን አዘኑ፤#ዕብ. “ከእነርሱም ማንም ጌጡን አልለበሰም” የሚል ይጨምራል። 5እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “ለእስራኤል ልጆች እናንተ አንገተ ደንዳና ሕዝብ ናችሁ፤ ሌላ መቅሠፍት እንዳላመጣባችሁና እንዳላጠፋችሁ ተጠንቀቁ፤ አሁንም የክብር ልብሳችሁንና ጌጣችሁን ከእናንተ አውጡ፤ የማደርግባችሁንም አሳያችኋለሁ በላቸው” አለው። 6የእስራኤልም ልጆች ከኮሬብ ተራራ ጀምረው ልብሶቻቸውንና ጌጦቻቸውን አወጡ።
ደብተራ ኦሪት
7ሙሴም ድንኳኑን ወስዶ ከሰፈር ውጭ ይተክለው ነበር፤ ከሰፈሩም ራቅ ያደርገው ነበር፤ “የምስክሩም ድንኳን” ብሎ ጠራው። እግዚአብሔርንም የፈለገ ሁሉ ከሰፈር ውጭ ወደአለው ወደ ድንኳኑ ይወጣ ነበር። 8ሙሴም ከሰፈር ውጭ ወደአለው ድንኳን በሄደ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ፥ እያንዳንዱም በድንኳኑ ደጃፍ እየጠበቀ ይቆም ነበር፤ ሙሴም ወደ ድንኳኑ እስኪገባ ድረስ ይመለከቱት ነበር። 9ሙሴም ወደ ድንኳኑ በገባ ጊዜ ዐምደ ደመና ይወርድ ነበር፤ በድንኳኑም ደጃፍ ይቆም ነበር፤ እግዚአብሔርም ሙሴን ይናገረው ነበር። 10ሕዝቡም ሁሉ ዐምደ ደመናው በድንኳኑ ደጃፍ ሲቆም ያየው ነበር፤ ሕዝቡም ሁሉ ተነሥቶ እያንዳንዱ በድንኳኑ ደጃፍ ይሰግድ ነበር። 11እግዚአብሔርም፥ ሰው ከባልንጀራው ጋር እንደሚነጋገር ፊት ለፊት ከሙሴ ጋር ይነጋገር ነበር። ሙሴም ወደ ሰፈሩ ይመለስ ነበር፤ ነገር ግን አገልጋዩ ብላቴና የነዌ ልጅ ኢያሱ ከድንኳኑ አይወጣም ነበር።
ሙሴና የእግዚአብሔር ክብር
12ሙሴም እግዚአብሔርን፥ “እነሆ፥ አንተ፦ ይህን ሕዝብ አውጣ ትለኛለህ፤ ነገር ግን ከእኔ ጋር የምትልከውን አላስታወቅኸኝም። አንተም ከሁሉ ይልቅ#ዕብ. “በስምህ” ይላል። ዐወቅሁህ፥ ደግሞም በእኔ ፊት ሞገስን አገኘህ አልኸኝ። 13አሁንም በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆነ፥ ዐውቅህ ዘንድ በፊትህም ሞገስን አገኝ ዘንድ ይህም ትልቅ ሕዝብ ሕዝብህ እንደ ሆነ ዐውቅ ዘንድ ተገለጥልኝ” አለው። 14እግዚአብሔርም፥ “እኔ በፊትህ እሄዳለሁ፥ አሳርፍህማለሁ” አለው። 15እርሱም፥ “አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህስ፥ ከዚህ አታውጣን። 16በምድርም ከአለው ሕዝብ ሁሉ እኔና ሕዝብህ ተለይተን እንከብር ዘንድ አንተ ከእኛ ጋር ካልሄድህ፥ እኔና ሕዝብህ በአንተ ዘንድ በእውነት ሞገስ ማግኘታችን በምን ይታወቃል?” አለው።
17እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ይህን ያልኸኝን ነገር አደርግልሃለሁ፤ በፊቴ ሞገስን አግኝተሀልና ከሁሉ ይልቅ ዐውቄሃለሁና”#ዕብ. “በስምህ ዐውቄሃለሁ” ይላል።አለው። 18እርሱም፥ “ክብርህን አሳየኝ” አለው። 19እግዚአብሔርም፥ “እኔ በክብሬ በፊትህ አልፋለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ስም በፊትህ እጠራለሁ፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በስሜ እግዚአብሔርን እጠራለሁ” ይላል። ይቅርም የምለውን ይቅር እላለሁ፤ የምምረውንም እምራለሁ” አለ። 20እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም” አለ። 21እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “እነሆ፥ ስፍራ በእኔ ዘንድ አለ፥ በዐለቱም ላይ ትቆማለህ፤ 22ክብሬም በአለፈ ጊዜ በአለቱ ስንጥቅ ውስጥ አኖርሃለሁ፤ 23እስከ አልፍም ድረስ እጄን በላይህ እጋርዳለሁ፤ እጄንም ፈቀቅ አደርጋለሁ፤ በዚያ ጊዜ ጀርባዬን ታያለህ፤ ፊቴ ግን ለአንተ አይታይም።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘፀአት 33: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ