የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፀ​አት 34

34
እንደ ገና የተ​ሠ​ሩት ጽላ​ቶች
(ዘዳ. 10፥1-5)
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ሁለት የድ​ን​ጋይ ጽላት እንደ ፊተ​ኞቹ አድ​ር​ገህ ቅረጽ፤ ወደ እኔም ወደ ተራራ ውጣ፤ በሰ​በ​ር​ሃ​ቸው በፊ​ተ​ኞቹ ጽላት የነ​በ​ሩ​ትን ቃላት እጽ​ፍ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ። 2ለጥ​ዋ​ትም የተ​ዘ​ጋ​ጀህ ሁን፤ ወደ ሲና ተራራ ወጥ​ተህ በዚያ በተ​ራ​ራው ራስ ላይ በፊቴ ቁም። 3ከአ​ን​ተም ጋር ማንም ሰው አይ​ውጣ፤ በተ​ራ​ራ​ውም ሁሉ ማንም አይ​ታይ፤ መን​ጎ​ችና ከብ​ቶ​ችም በዚያ ተራራ አጠ​ገብ አይ​ሰ​ማሩ። 4ሙሴም እንደ ፊተ​ኞቹ አድ​ርጎ ሁለት የድ​ን​ጋይ ጽላት ቀረጸ፤ ሁለ​ቱ​ንም የድ​ን​ጋይ ጽላት በእጁ ወሰደ፤ በነ​ጋ​ውም ማልዶ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው ወደ ሲና ተራራ ወጣ፤ 5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በደ​መ​ናው ውስጥ ወረደ፤ በዚ​ያም ከእ​ርሱ ጋር ቆመ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም ጠራ። 6ጌታም በፊቱ አለፈ፥ “ስሜም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ መሓሪ፥ ይቅር ባይ፥ ከመ​ዓት የራቀ ምሕ​ረቱ የበዛ ጻድቅ፥ 7ለብዙ ሺህ ጽድ​ቅን የሚ​ጠ​ብቅ፥ ቸር​ነ​ትን የሚ​ያ​ደ​ርግ፥ አበ​ሳ​ንና መተ​ላ​ለ​ፍን፥ ኀጢ​አ​ት​ንም ይቅር የሚል፥ በደ​ለ​ኛ​ው​ንም ከቶ የማ​ያ​ነጻ፥ የአ​ባ​ቶ​ች​ንም ኀጢ​አት በል​ጆች፥ እስከ ሦስ​ትና እስከ አራት ትው​ል​ድም በልጅ ልጆች የሚ​ያ​መጣ አም​ላክ ነው” ሲል አወጀ። 8ሙሴም ፈጥኖ ወደ መሬት ተጎ​ነ​በ​ሰና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገደ፦ 9“አቤቱ በፊ​ት​ህስ ሞገ​ስን አግ​ኝቼ እንደ ሆነ፥ ይህ ሕዝብ አን​ገተ ደን​ዳና ነውና ጌታዬ ከእኛ ጋር ይሂድ፤ ጠማ​ማ​ነ​ታ​ች​ንን፥ ኀጢ​አ​ታ​ች​ን​ንና በደ​ላ​ች​ንን ይቅር በለን፤ ለአ​ን​ተም እን​ሆ​ና​ለን” አለ።
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳ​ኑን እንደ ገና ማደሱ
(ዘፀ. 23፥14-19ዘዳ. 7፥1-516፥1-17)
10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እነሆ፥ እኔ በሕ​ዝ​ብህ ፊት ሁሉ ቃል ኪዳን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በም​ድር ሁሉ፥ በአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ ዘንድ እንደ እርሱ ያለ ከቶ ያል​ተ​ደ​ረ​ገ​ውን ታላቅ ተአ​ም​ራ​ትን አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለሁ፤ እኔም የማ​ደ​ር​ግ​ልህ ነገር ድንቅ ነውና አንተ በመ​ካ​ከሉ ያለ​ህ​በት ይህ ሕዝብ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ያያል። 11በዚህ ቀን የማ​ዝ​ዝ​ህን ነገር ጠብቅ፤ እነሆ፥ እኔ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ውን፥ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ከፊ​ትህ አወ​ጣ​ለሁ። 12በመ​ካ​ከ​ልህ ወጥ​መድ እን​ዳ​ይ​ሆ​ኑ​ብህ አንተ በም​ት​ገ​ባ​በት ምድር ከሚ​ኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እን​ዳ​ታ​ደ​ርግ ተጠ​ን​ቀቅ፤ 13ነገር ግን መሠ​ው​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ውን ታፈ​ር​ሳ​ላ​ችሁ፤ ሐው​ል​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ትሰ​ብ​ራ​ላ​ችሁ፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ቻ​ቸ​ውን ትቈ​ር​ጣ​ላ​ችሁ፤ ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ላ​ችሁ፤#“ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ላ​ችሁ” የሚ​ለው በዕብ. የለም። 14ስሙ ቀና​ተኛ የሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅን​ዐት ያለው አም​ላክ ነውና ለሌላ አም​ላክ አት​ስ​ገድ። 15በዚ​ያች ምድር ከሚ​ኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እን​ዳ​ታ​ደ​ርግ፥ እነ​ርሱ አም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ውን ተከ​ት​ለው በአ​መ​ነ​ዘ​ሩና በሠ​ዉ​ላ​ቸው ጊዜ እን​ዳ​ይ​ጠ​ሩህ፥ ከመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውም እን​ዳ​ት​በላ፥ 16ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ም​ንም ከወ​ንድ ልጆ​ችህ፥ ሴቶች ልጆ​ች​ህ​ንም ከወ​ንድ ልጆ​ቻ​ቸው ጋር እን​ዳ​ታ​ጋባ፥ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም አም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ውን ተከ​ት​ለው ሲያ​መ​ነ​ዝሩ ከአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸው በኋላ ሄደው አመ​ን​ዝ​ረ​ውም ልጆ​ች​ህን እን​ዳ​ያ​ስቱ ተጠ​ን​ቀቅ። 17ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ትን አማ​ል​ክት ለአ​ንተ አታ​ድ​ርግ።
18“የቂ​ጣ​ውን በዓል ትጠ​ብ​ቀ​ዋ​ለህ። በሚ​ያ​ዝያ ወር ከግ​ብፅ ወጥ​ተ​ሃ​ልና በታ​ዘ​ዘው ዘመን በሚ​ያ​ዝያ ወር እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁህ ሰባት ቀን ቂጣ ብላ። 19መጀ​መ​ሪያ የሚ​ወ​ለድ ተባት ሁሉ የእኔ ነው፤ የላ​ም​ህም በኵር፥ የበ​ግ​ህም በኵር፥ የበ​ሬ​ህም በኵር ሁሉ የእኔ ነው። 20የአ​ህ​ያ​ው​ንም በኵር በበግ ትዋ​ጀ​ዋ​ለህ፤ ባት​ዋ​ጀው#ዕብ. “አን​ገ​ቱን ትሰ​ብ​ረ​ዋ​ለህ” ይላል። ግን ዋጋ​ውን ትሰ​ጣ​ለህ። የል​ጆ​ች​ህ​ንም በኵር ሁሉ ትዋ​ጃ​ለህ። በፊ​ቴም ባዶ እጅ​ህን አት​ታይ።
21“ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ትሠ​ራ​ለህ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ታር​ፋ​ለህ። በም​ት​ዘ​ራ​በ​ትና በም​ታ​ጭ​ድ​በት ዘመን ታር​ፋ​ለህ። 22የሰ​ባ​ቱ​ንም ሱባዔ በዓል ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ እር​ሱም የስ​ንዴ መከር መጀ​መ​ሪያ ነው፤ በዓ​መ​ቱም መካ​ከል የመ​ክ​ተቻ በዓል ታደ​ር​ጋ​ለህ። 23ወንድ ልጅህ ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በዓ​መት ሦስት ጊዜ ይታይ። 24አሕ​ዛ​ብን ከፊ​ትህ በአ​ወ​ጣሁ ጊዜ ሀገ​ር​ህን አሰ​ፋ​ለሁ፤ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊትም ለመ​ታ​የት በዓ​መት ሦስት ጊዜ ስት​ወጣ ማንም ምድ​ር​ህን አይ​መ​ኝም።
25“የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቴን ደም ከቦካ እን​ጀራ ጋር አት​ሠዋ፤ የፋ​ሲ​ካ​ውም በዓል መሥ​ዋ​ዕት እስከ ነገ አይ​ደር። 26የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውን የም​ድ​ር​ህን ፍሬ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ትወ​ስ​ዳ​ለህ። ጠቦ​ቱን በእ​ናቱ ወተት አት​ቀ​ቅል።”
27እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “በእ​ነ​ዚህ ቃሎች ከአ​ን​ተና ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ቃል ኪዳን አድ​ር​ጌ​አ​ለ​ሁና እነ​ዚ​ህን ቃሎች ጻፍ” አለው። 28በዚ​ያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ነበረ፤ እን​ጀ​ራም አል​በ​ላም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣም። በጽ​ላ​ቱም ዐሥ​ሩን የቃል ኪዳን ቃሎች ጻፈ።
የሙሴ ፊት እንደ አበራ
29እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሙሴ ከሲና ተራራ በወ​ረደ ጊዜ ሁለቱ#ዕብ. “የም​ስ​ክር ጽላት” ይላል። ጽላት በሙሴ እጅ ነበሩ፤ ሙሴም ከተ​ራ​ራው በወ​ረደ ጊዜ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ሲነ​ጋ​ገር ፊቱ እን​ዳ​ን​ጸ​ባ​ረቀ አላ​ወ​ቀም ነበር። 30አሮ​ንና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ እነሆ፥ ፊቱ እን​ዳ​ን​ጸ​ባ​ረቀ ሙሴን በአዩ ጊዜ፥ ወደ እርሱ ለመ​ቅ​ረብ ፈሩ። 31ሙሴም ጠራ​ቸው፤ አሮ​ንም የማ​ኅ​በ​ሩም አለ​ቆች ሁሉ ወደ እርሱ ተመ​ለሱ፤ ሙሴም ተና​ገ​ራ​ቸው። 32ከዚ​ያም በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ወደ እርሱ ቀረቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሲና ተራራ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ነገር ሁሉ አዘ​ዛ​ቸው። 33ሙሴም ለእ​ነ​ርሱ ተና​ግሮ ከጨ​ረሰ በኋላ በፊቱ መሸ​ፈኛ አደ​ረገ። 34ሙሴም ከእ​ርሱ ጋር ይነ​ጋ​ገር ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በገባ ጊዜ እስ​ኪ​ወጣ ድረስ መሸ​ፈ​ኛ​ውን ከፊቱ ያነሣ ነበር፤ በወ​ጣም ጊዜ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የታ​ዘ​ዘ​ውን ነገር ይነ​ግ​ራ​ቸው ነበር። 35የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የሙ​ሴን ፊት እን​ዳ​ን​ጸ​ባ​ረቀ ያዩ ነበር፤ እር​ሱም ከእ​ርሱ ጋር ሊነ​ጋ​ገር እስ​ኪ​ገባ ድረስ እንደ ገና በፊቱ መሸ​ፈኛ ያደ​ርግ ነበር።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ