ኦሪት ዘፀአት 35
35
የሰንበት አከባበር ሥርዐት
1ሙሴም የእስራኤልን ልጆች ማኅበር ሁሉ ሰብስቦ እንዲህ አላቸው፥ “ታደርጉ ዘንድ እግዚአብሔር ያለው ነገር ይህ ነው፤ 2ስድስት ቀን ሥራህን ትሠራለህ፤ በሰባተኛው ቀን ታርፋለህ፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የዕረፍት ሰንበት ነው፤ የሚሠራበትም ሁሉ ይሙት። 3በማደሪያዎቻችሁ ውስጥ በሰንበት ቀን እሳትን አታንድዱ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”#“እኔ እግዚአብሔር ነኝ” የሚለው በዕብ. የለም።
ለድንኳኑ ሥራ የቀረበ መባ
(ዘፀ. 25፥1-9)
4ሙሴም ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ አላቸው፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ያዘዘው ነገር ይህ ነው፤ 5ከእናንተ ዘንድ ለእግዚአብሔር ቍርባንን አቅርቡ፤ የልብ ፈቃድ ያለው ከገንዘቡ የመጀመሪያውን ለእግዚአብሔር ያምጣ፤ ወርቅና ብር፥ ናስም፤ 6ሰማያዊም፥ ሐምራዊም፥ ድርብ ቀይ ግምጃም፥ የተፈተለ በፍታም፥ የፍየል ጠጕርም፤ 7ቀይ ቀለምም የገባበት የአውራ በግ ቍርበት፥ የአቆስጣም ቍርበት፥ የማይነቅዝም ዕንጨት፤ 8ለመብራትም ዘይት፥ ለቅብዐት ሽቱን፥ ለማዕጠንት ዕጣንን፤#ምዕ. 35 ቍ. 8 በሙሉ በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 9የመረግድ ድንጋይና የተቀረጸ ድንጋይ፥ ለልብሰ መትከፍና ለልብሰ እንግድዓ የሚደረግ ፈርጥ ያምጣ።
የድንኳኑ መገልገያ ዕቃዎች
(ዘፀ. 39፥34-43)
10“በእናንተ ዘንድ ያለ፥ በልቡ ጥበበኛ የሆነ ሁሉ መጥቶ እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ያድርግ። 11ድንኳኑንም፥ አደባባዩንም፥ መደረቢያውንም፥ መያዣዎቹንም፥ ሳንቆቹንም፥ መወርወሪያዎቹንም፥ ምሰሶዎችንና እግሮቻቸውን፤ 12የቃል ኪዳኑን ታቦትም፥ መሎጊያዎቹንም፥ የስርየት መክደኛውንም፥ መጋረጃውንም፤ 13ገበታውንና መሎጊያዎቹንም፥ ዕቃውንም ሁሉ፥ ኅብስተ ገጹንም፤ 14መብራት የሚያበሩበትን መቅረዙን፥ ዕቃውንም ሁሉ፥ ቀንዲሉንም፥ የመብራቱንም ዘይት፤ 15የዕጣኑንም መሠዊያ፥ መሎጊያዎቹንም፥ የቅብዐቱንም ዘይት፥ ጣፋጩንም ዕጣን፥ ለማደሪያውም ደጃፍ የሚሆን የደጃፉን መጋረጃ፤ 16ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን መሠዊያውን፥ የናሱንም መከታ፥ መሎጊያዎቹንም፥ ዕቃውንም ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሰንም፥ መቀመጫውንም፤ 17የአደባባዩን መጋረጆች፥ ምሰሶዎችንም፥ እግሮቻቸውንም፥ የአደባባዩንም ደጃፍ መጋረጃ፤ 18የማደሪያውን ካስማዎች፥ የአደባባዩንም ካስማዎች፥ አውታሮቻቸውንም፤ 19በመቅደስ ውስጥ ለማገልገል በብልሃት የተሠሩትን ልብሶች፥ በክህነት ያገለግሉበት ዘንድ የተቀደሱትን የካህኑን የአሮንን ልብሶች፥ የልጆቹንም ልብሶች።”
20የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ከሙሴ ዘንድ ወጡ። 21ከእነርሱም ሰው ሁሉ እያንዳንዱ ልቡ እንዳነሣሣው፥ መንፈሱም እሺ እንዳሰኘው ለምስክሩ ድንኳን ሥራ ለማገልገያውም ሁሉ ለመቅደስ ልብስ ለእግዚአብሔር ስጦታ አመጡ። 22ወንዶችና ሴቶችም ልባቸው እንደ ፈቀደ ማርዳዎችን፥ ሎቲዎችንም፥ ቀለበቶችንም፥ ድሪዎችንም፥ የወርቅ ጌጦችንም ሁሉ አመጡ፤ ሰዎችም ሁሉ የወርቅ ስጦታ ለእግዚአብሔር አቀረቡ። 23ሰማያዊም፥ ሐምራዊም፥ ቀይ ግምጃም፥ የተፈተለ በፍታም፥ የፍየል ጠጕርም፥ ቀይ የአውራ በግ ቍርበትም፥ የአቆስጣ ቍርበትም ያላቸው ሰዎች ሁሉ አመጡ።#ምዕ. 35 ቍ. 22 እና 23 ግእዙ እና ግሪክ ሰባ. ሊ. አይስማሙም። 24ስዕለት የተሳለ ሁሉ፥ የብርንም፥ የናስንም ስጦታ ለእግዚአብሔር ቍርባን አቀረበ፤ የማይነቅዝ ዕንጨት ያለው ሁሉ ለድንኳኑ ማገልገያ ለሚያስፈልገው ሥራ አመጣ። 25በልባቸው ጥበበኞች የሆኑ ሴቶችም በእጃቸው ፈተሉ፤ የፈተሉትንም ሰማያዊውን፥ ሐምራዊውንም፥ ቀዩንም ግምጃ፥ ጥሩውንም በፍታ አመጡ። 26ልባቸውም በጥበብ ያስነሣቸው ሴቶች ሁሉ የፍየልን ጠጕር ፈተሉ። 27አለቆችም የመረግድ ድንጋይና የተቀረጸ ድንጋይን ለልብሰ መትከፍና ለልብሰ እንግድዓ የሚገቡትንም ፈርጦችን፥ 28ለመብራትም፥ ለቅብዐት ዘይትም፥ ለጣፋጭ ዕጣንም ሽቱንና ዘይትን አመጡ። 29ከእስራኤል ልጆችም ያመጡ ዘንድ ልባቸው ያስነሣቸው ወንዶችና ሴቶች ሁሉ ሙሴ ይሠራ ዘንድ እግዚአብሔር ላዘዘው ሥራ ሁሉ ለእግዚአብሔር ስጦታ በፈቃዳቸው አመጡ።
ባስልኤልና ኤልያብ
(ዘፀ. 31፥1-11)
30ሙሴም የእስራኤልን ልጆች አላቸው፥ “እዩ፥ እግዚአብሔር ከይሁዳ ነገድ የሆነውን የሆር የልጅ ልጅ፥ የኡሪ ልጅ ባስልኤልን በስሙ ጠራው። 31በሥራ ሁሉ ብልሃት፥ በጥበብም፥ በማስተዋልም፥ በዕውቀትም የእግዚአብሔርን መንፈስ ሞላበት፤ 32በአናጺዎች ላይ አለቃ ይሆን ዘንድ፥ የጥበብንም ሥራ ያስተውል ዘንድ፥ በወርቅና በብር፥ በናስም ይሠራ ዘንድ፥ 33በፈርጥ የሚሆነውን የዕንቍ ድንጋይ ይቀርጽ ዘንድ፥ ዕንጨቱንም ይጠርብ ዘንድ፥ የብልሃት ሥራውንም ሁሉ ይሠራ ዘንድ። 34እርሱና የዳን ነገድ የሆነው የአሒሳሚክ ልጅ ኤልያብ ያስተምሩ ዘንድ በልባቸው አሳደረባቸው። 35በአንጥረኛ፥ በብልህ ሠራተኛም፥ በሰማያዊና በሐምራዊ፥ በቀይም ግምጃ፥ በጥሩ በፍታም በሚሠራ ጠላፊ፥ በሸማኔም ሥራ የሚሠራውን፥ ማናቸውንም ሥራና በብልሃት የሚሠራውን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ በእነርሱ ልብ ጥበብን ሞላ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፀአት 35: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ