የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፀ​አት 5

5
ሙሴና አሮን በፈ​ር​ዖን ፊት
1ከዚ​ህም በኋላ ሙሴና አሮን ወደ ፈር​ዖን ገብ​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ‘በም​ድረ በዳ በዓል ያደ​ር​ግ​ልኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።’ ” 2ፈር​ዖ​ንም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እለ​ቅቅ ዘንድ ቃሉን የም​ሰ​ማው እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማን ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​ው​ቅም፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ደግሞ አል​ለ​ቅ​ቅም” አለ። 3እነ​ር​ሱም፥ “ቸነ​ፈር ወይም ሰይፍ እን​ዳ​ይ​ጥ​ል​ብን የሦ​ስት ቀን መን​ገድ በም​ድረ በዳ እን​ድ​ን​ሄድ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ድ​ን​ሠዋ የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ ጠራን” አሉት። 4የግ​ብፅ ንጉ​ሥም፥ “እና​ንተ ሙሴና አሮን፥ ሕዝ​ቡን ለምን ሥራ​ቸ​ዉን ታስ​ተ​ዋ​ላ​ችሁ? ወደ ተግ​ባ​ራ​ችሁ ሂዱ” አላ​ቸው። 5ፈር​ዖ​ንም ለሕ​ዝቡ አለ፥ “እነሆ፥ ሕዝቡ በም​ድር በጣም በዝ​ተ​ዋል፤ እና​ን​ተም ከሥ​ራ​ቸው አሳ​ር​ፋ​ች​ኋ​ቸ​ዋል። 6ፈር​ዖ​ንም በዚያ ቀን የሕ​ዝ​ቡን አሠ​ሪ​ዎ​ችና ጸሓ​ፊ​ዎች እን​ዲህ ሲል አዘዘ፦ 7“እንደ ወት​ሮው ለጡብ ሥራ ደግሞ ገለባ ለሕ​ዝቡ አት​ስጡ፤ ነገር ግን እነ​ርሱ ሄደው ለራ​ሳ​ቸው ገለባ ይሰ​ብ​ስቡ። 8ቀድሞ ያደ​ር​ጉት የነ​በ​ረ​ውን የጡብ ቍጥር እን​ዲሁ በየ​ቀኑ በእ​ነ​ርሱ ላይ አድ​ር​ጉት፤ ምንም ከእ​ርሱ አታ​ጕ​ድሉ፤ ሥራ ሰል​ች​ተ​ዋ​ልና ስለ​ዚህ፦ ‘ለአ​ም​ላ​ካ​ችን እን​ድ​ን​ሠዋ እን​ሂድ’ እያሉ ይጮ​ሃሉ። 9በእ​ነ​ዚህ ሰዎች ላይ ሥራው ይክ​በ​ድ​ባ​ቸው፤ ይህን ብቻ ያስ​ባሉ፤ ከንቱ ቃልም አያ​ስ​ቡም።” 10የሕ​ዝ​ቡም አሠ​ሪ​ዎ​ችና ጸሓ​ፊ​ዎች ወጡ፤ ሕዝ​ቡ​ንም፥ “ፈር​ዖን እን​ዲህ ይላል፦ እን​ግ​ዲህ ገለባ አይ​ሰ​ጣ​ች​ሁም፤ 11እና​ንተ ሂዱ፤ ከም​ታ​ገ​ኙ​በ​ትም ስፍራ ገለባ ሰብ​ስቡ፤ ከም​ት​ሠ​ሩት ጡብ ግን ምንም አይ​ጐ​ድ​ልም” አሉ​አ​ቸው። 12ሕዝ​ቡም ሁሉ ስለ ገለባ እብቅ ሊሰ​በ​ስቡ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ተበ​ተኑ። 13አሠ​ሪ​ዎ​ቹም፥ “ገለባ ትቀ​በ​ሉ​በት እን​ደ​ነ​በረ ጊዜ የቀን ሥራ​ች​ሁን ጨርሱ” እያሉ ያስ​ቸ​ኩ​ሉ​አ​ቸው ነበር። 14የፈ​ር​ዖ​ንም ሹሞች፥ “ቀድሞ ታደ​ር​ጉት እንደ ነበ​ራ​ችሁ እንደ ትና​ን​ት​ና​ውና እንደ ትና​ን​ትና በስ​ቲ​ያው የተ​ቈ​ጠ​ረ​ውን ጡብ ዛሬስ ስለ​ምን አት​ጨ​ር​ሱም?” እያሉ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ የተ​ሾ​ሙ​ትን አለ​ቆች ይገ​ርፉ ነበር።
15የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አለ​ቆ​ችም ወደ ፈር​ዖን ገቡ፥ “ለምን በአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ እን​ዲህ ታደ​ር​ጋ​ለህ? ገለባ አይ​ሰ​ጡ​አ​ቸ​ውም፤ ጡቡ​ንም ሥሩ ይሉ​አ​ቸ​ዋል፤ 16እነ​ሆም፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ይገ​ረ​ፋሉ፤ ይገ​ፋ​ሉም፤ ግፉም በአ​ንተ ሕዝብ ላይ ነው” ብለው ጮኹ። 17እርሱ ግን፥ “እና​ንተ አር​ፋ​ች​ኋል፤ ቦዝ​ና​ች​ኋል፤ ስለ​ዚ​ህም፦ ‘እን​ሂድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ሠዋ’ ትላ​ላ​ችሁ። 18አሁ​ንም ሂዱ፤ ሥሩ፤ ገለ​ባም አይ​ሰ​ጡ​አ​ች​ሁም፤ የጡ​ቡን ቍጥር ግን ታመ​ጣ​ላ​ችሁ” አላ​ቸው። 19የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አለ​ቆች ዕለት ዕለት ከም​ት​ሠ​ሩት ከጡቡ ቍጥር ምንም አታ​ጕ​ድሉ ባሉ​አ​ቸው ጊዜ ነገሩ እንደ ከፋ​ባ​ቸው አዩ። 20ከፈ​ር​ዖ​ንም ዘንድ ሲወጡ ሙሴ​ንና አሮ​ንን በፊ​ታ​ቸው ቆመው ተገ​ና​ኙ​አ​ቸው። 21እነ​ር​ሱም፥ “በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ፊት ሽታ​ች​ንን አግ​ም​ታ​ች​ሁ​ታ​ልና፥ ይገ​ድ​ለ​ንም ዘንድ ሰይ​ፍን በእጁ ሰጥ​ታ​ች​ሁ​ታ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ል​ከ​ታ​ችሁ፤ ይፍ​ረ​ድ​ባ​ች​ሁም” አሉ​አ​ቸው።
ሙሴ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ረ​በው አቤ​ቱታ
22ሙሴም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተመ​ለ​ሰና፥ “ጌታ ሆይ፥ ስለ​ምን ይህን ሕዝብ አስ​ከ​ፋህ? ስለ ምንስ ላክ​ኸኝ? 23በስ​ምህ እና​ገር ዘንድ ወደ ፈር​ዖን ከገ​ባሁ ወዲህ፥ ይህን ሕዝብ አስ​ከ​ፍ​ቶ​ታ​ልና፤ አን​ተም ሕዝ​ብ​ህን ከቶ አላ​ዳ​ን​ኸ​ውም” አለ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ