የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 21

21
በባ​ቢ​ሎን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰይፍ
1የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 2“የሰው ልጅ ሆይ! ስለ​ዚህ ትን​ቢት ተና​ገር፤ ፊት​ህን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አቅና፤ ወደ መቅ​ደ​ሶ​ችም ተመ​ል​ከት፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ምድር ላይ ትን​ቢት ተና​ገር። 3ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ምድር እን​ዲህ በል፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በአ​ንቺ ላይ ነኝ፤ ሰይ​ፌ​ንም ከሰ​ገ​ባው እመ​ዝ​ዘ​ዋ​ለሁ፤ ጻድ​ቁ​ንና ኃጥ​ኡን ከአ​ንቺ ዘንድ አጠ​ፋ​ለሁ። 4እኔም ጻድ​ቁ​ንና ኃጥ​ኡን ከአ​ንቺ ዘንድ ስለ​ማ​ጠፋ፥ ስለ​ዚህ ሰይፌ ከደ​ቡብ ጀምሮ እስከ ሰሜን ድረስ በአለ በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ ከሰ​ገ​ባው ይመ​ዘ​ዛል። 5ሥጋ ለባ​ሹም ሁሉ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰይ​ፌን ከሰ​ገ​ባው እንደ መዘ​ዝሁ ያው​ቃል፤ እር​ሱም ደግሞ አይ​መ​ለ​ስም። 6ስለ​ዚህ አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ወገ​ብ​ህን በማ​ጕ​በጥ አል​ቅስ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ምርር ብለህ አል​ቅስ። 7እነ​ር​ሱም፦ ስለ ምን ታለ​ቅ​ሳ​ለህ? ቢሉህ አንተ እን​ዲህ በላ​ቸው፦ ስለ​ሚ​መ​ጣው ወሬ ነው፤ ልብም ሁሉ ይቀ​ል​ጣል፤ እጆ​ችም ሁሉ ይዝ​ላሉ፤ ሥጋና መን​ፈስ ሁሉ ይደ​ክ​ማል፤ ከጕ​ል​በ​ትም እዥ ይፈ​ስ​ሳል፤ እነሆ ይመ​ጣል፤ ይፈ​ጸ​ማ​ልም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
8የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 9“የሰው ልጅ ሆይ! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል ብለህ ትን​ቢት ተና​ገር፤ ሰይፍ ሰይፍ የተ​ሳ​ለች፥ የተ​ሰ​ነ​ገ​ለ​ችም ሁኚ። 10ወግ​ተሽ ትገ​ድሊ ዘንድ፥ ታብ​ረ​ቀ​ር​ቂም ዘንድ ተሳዪ፤ ትገ​ድ​ሊም ዘንድ፥ ዕን​ጨ​ቱ​ንም ሁሉ ትጥዪ ዘንድ ጨክኚ፤#ዕብ. “ይገ​ድል ዘንድ ተስ​ሎ​አል ፤ ያብ​ረ​ቀ​ር​ቅም ዘንድ ተሰ​ን​ግ​ሎ​አል ፤ እኛስ ደስ ይለ​ናል ፤ የል​ጄን በትር እንደ ዛፍ ሁሉ ንቆ​ታል” ይላል። 11በእ​ጁም ይይ​ዛት ዘንድ ለአ​ር​በኛ ተሰ​ጠች፤ ሰይፍ በገ​ዳይ እጅ እን​ድ​ት​ሰጥ ተሳ​ለ​ችና ተዘ​ጋ​ጀች። 12የሰው ልጅ ሆይ! በሕ​ዝቤ ላይ ነውና፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አለ​ቆች ሁሉ ላይ ነውና ጩኽ፤ ዋይም በል፤ እነ​ርሱ ከሕ​ዝቤ ጋር ለሰ​ይፍ ተሰ​ጥ​ተ​ዋል፤ ስለ​ዚህ እጅ​ህን ጽፋ። 13እው​ነት ሆኖ​አ​ልና፤ የራቁ ሕዝቤ ምን ሆኑ? የሉ​ምና፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 14ስለ​ዚህ አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ትን​ቢት ተና​ገር፤ እጅ​ህን በእ​ጅህ ላይ አጨ​ብ​ጭብ፤ የተ​ገ​ደሉ ሰዎች ሰይፍ ሦስት ጊዜ ይደ​ጋ​ግም፤ ይኸ​ውም የታ​ላቅ ግድያ ሰይፍ ነው፤ ያስ​ደ​ነ​ግ​ጣ​ቸ​ዋ​ልም።#“ያስ​ደ​ነ​ግ​ጣ​ቸ​ዋል” የሚ​ለው በዕብ. የለም። 15ልባ​ቸው እን​ዲ​ቀ​ልጥ፥ መሰ​ና​ክ​ላ​ቸ​ውም እን​ዲ​በዛ የሚ​ገ​ድ​ለ​ውን ሰይፍ በበ​ሮ​ቻ​ቸው ሁሉ ላይ አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ ወዮ! ያብ​ረ​ቀ​ርቅ ዘንድ ተሰ​ን​ግ​ሏል፤ ይገ​ድ​ልም ዘንድ ተስ​ሏል። 16ፊትህ ወደ አቀ​ናው ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ሂድ። 17እኔ ደግሞ እጄን በእጄ ላይ አጨ​በ​ጭ​ባ​ለሁ፤ መዓ​ቴ​ንም እል​ካ​ለሁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ።”
18የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 19“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ሰይፍ የም​ት​ገ​ባ​ባ​ቸው ሁለት መን​ገ​ዶ​ችን አድ​ርግ፤ ሁለ​ቱም ከአ​ን​ዲት ምድር ይውጡ፤ ምል​ክ​ት​ንም አድ​ርግ፤ በከ​ተ​ማ​ዪቱ መን​ገድ ራስ ላይም አድ​ር​ገው። 20ሰይፍ ወደ አሞን ልጆች ሀገር፥ ወደ ራባት፥ ወደ ይሁ​ዳም፥ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም፥ በመ​ካ​ከ​ልዋ ይገባ ዘንድ መን​ገ​ድን አድ​ርግ። 21የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ምዋ​ር​ቱን ያም​ዋ​ርት ዘንድ፥ በት​ሩን#ዕብ. “ፍላ​ጾ​ችን” ይላል። ያነሣ ዘንድ፥ ጣዖ​ቱ​ንም ይጠ​ይቅ ዘንድ በሁ​ለት መን​ገ​ዶች ራስ ላይ ይቆ​ማል። 22የቅ​ጥ​ሩን ማፍ​ረሻ ያደ​ርግ ዘንድ፥ አፍ​ንም በጩ​ኸት ይከ​ፍት ዘንድ፥ በው​ካ​ታም ድም​ፅን ከፍ ያደ​ርግ ዘንድ፥ የቅ​ጥ​ሩን ማፍ​ረሻ በበ​ሮች ላይ ያደ​ርግ ዘንድ፥ አፈ​ርን ይደ​ለ​ድል ዘንድ፥ ምሽ​ግም ይሠራ ዘንድ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ምዋ​ርት በቀኝ እጁ ውስጥ ነበረ። 23እርሱ በፊ​ታ​ቸው ምዋ​ር​ትን ያም​ዋ​ር​ታል፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ዐስቦ ሰባት ሱባዔ ይቈ​ጥ​ር​ባ​ቸ​ዋል።#“ሰባት ሱባዔ ይቈ​ጥ​ር​ባ​ቸ​ዋል” የሚ​ለው በዕብ. እና በግ​ሪክ የለም።
24“ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁን ስለ ዐሰ​ባ​ችሁ፥ መተ​ላ​ለ​ፋ​ች​ሁም ስለ ተገ​ለጠ፥ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁም በሥ​ራ​ችሁ ሁሉ ስለ ታየ፥ እና​ን​ተም ስለ ታሰ​ባ​ችሁ፥ በእ​ርሱ ትያ​ዛ​ላ​ችሁ። 25አን​ተም ቀን​ህና የኀ​ጢ​አ​ትህ ቀጠሮ ጊዜ የደ​ረ​ሰ​ብህ፥ ርኩስ ኀጢ​አ​ተኛ የእ​ስ​ራ​ኤል አለቃ ሆይ! 26ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ መጠ​ም​ጠ​ሚ​ያ​ውን አው​ልቅ፤ ዘው​ዱ​ንም አርቅ፤ ይህ እን​ዲህ አይ​ሆ​ንም፤ የተ​ዋ​ረ​ደ​ውን ከፍ አድ​ርግ፤ ከፍ ያለ​ው​ንም አዋ​ርድ። 27ባድማ፥ ባድማ፥ ባድማ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ ፍርድ ያለው እስ​ኪ​መጣ ድረስ ይህች ደግሞ አት​ሆ​ንም፤ ለእ​ር​ሱም እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤#ግእዝ “ጌጋየ ወአ​በሳ ወኀ​ጢ​አተ እሬ​ስዮ ላቲ” ይላል።
28“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አሞን ልጆ​ችና ስለ ስድ​ባ​ቸው እን​ዲህ ይላል ብለህ ትን​ቢት ተና​ገር፤ ሰይፍ ሰይፍ ለመ​ግ​ደል ተመ​ዝ​ዞ​አል፤ ጨር​ሶም ያርድ ዘንድ ተሰ​ን​ግ​ሎ​አል በል። 29በተ​ገ​ደ​ሉት ኀጢ​አ​ተ​ኞች አን​ገት ላይ ያኖ​ሩህ ዘንድ ከንቱ ራእ​ይን ሲያ​ዩ​ልህ፥ በሐ​ሰት ምዋ​ር​ትም ሲና​ገ​ሩ​ልህ፥ በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ቀጠሮ ጊዜ ቀና​ቸው ደረሰ። 30ወደ ሰገ​ባ​ውም መል​ሰው፤ በተ​ፈ​ጠ​ር​ህ​ባት ስፍራ አት​ደር፤ በተ​ወ​ለ​ድ​ህ​ባ​ትም ምድር እፈ​ር​ድ​ብ​ሃ​ለሁ። 31ቍጣ​ዬ​ንም አፈ​ስ​ስ​ብ​ሃ​ለሁ፤ በመ​ዓ​ቴም እሳት አና​ፋ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ማጥ​ፋ​ት​ንም ለሚ​ያ​ውቁ ለጨ​ካ​ኞች ሰዎች እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ። 32ለእ​ሳት ማገዶ ትሆ​ና​ለህ፤ ደም​ህም በም​ድር መካ​ከል ይፈ​ስ​ሳል፤ ደግ​ሞም አት​ታ​ሰ​ብም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና።”#ምዕ. 21 ከቍ. 30 እስከ 32 አን​ዳ​ንድ ዘርእ በአ​ን​ስ​ታይ አን​ቀጽ ያነ​ብ​ባል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ