የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 22

22
የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሕዝብ ኀጢ​አት
1የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 2“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ደም በም​ታ​ፈ​ስስ ከተማ ላይ ትፈ​ር​ዳ​ለ​ህን? ርኵ​ሰ​ቷን ሁሉ አስ​ታ​ው​ቃት። 3እን​ዲ​ህም በላት፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጊዜሽ እን​ዲ​ደ​ርስ በመ​ካ​ከ​ልሽ ደምን የም​ታ​ፈ​ስሺ፥ እን​ድ​ት​ረ​ክ​ሺም በራ​ስሽ ላይ ጣዖ​ታ​ትን የም​ታ​ደ​ርጊ ከተማ ሆይ! 4ባፈ​ሰ​ስ​ሽው ደም በድ​ለ​ሻል፤ ባደ​ረ​ግ​ሻ​ቸ​ውም ጣዖ​ታት ረክ​ሰ​ሻል፤ ቀን​ሽ​ንም አቀ​ረ​ብሽ፤ ዘመ​ን​ሽ​ንም አሳ​ጠ​ርሽ፤ ስለ​ዚህ ለአ​ሕ​ዛብ መሰ​ደ​ቢያ፥ ለሀ​ገ​ሮ​ችም ሁሉ መሳ​ለ​ቂያ አደ​ረ​ግ​ሁሽ። 5አንቺ ስምሽ የረ​ከሰ፥ ኀጢ​አ​ትም የሞ​ላ​ብሽ ሆይ! ወደ አንቺ የቀ​ረ​ቡና ከአ​ንቺ የራቁ ይሳ​ለ​ቁ​ብ​ሻል።
6“እነሆ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት አለ​ቆች እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ከዘ​መ​ዶ​ቻ​ቸው ጋር#ዕብ. “እያ​ን​ዳ​ንዱ እንደ ችሎቱ” ይላል። ደም ያፈ​ስሱ ዘንድ በአ​ንቺ ውስጥ ተባ​በሩ። 7በአ​ንቺ ውስጥ አባ​ት​ንና እና​ትን አቃ​ለሉ፤ በመ​ካ​ከ​ልሽ በመ​ጻ​ተ​ኛው ላይ በደ​ልን አደ​ረጉ፤ በአ​ንቺ ውስጥ ድሀ አደ​ጉ​ንና መበ​ለ​ቲ​ቱን አስ​ጨ​ነቁ። 8ቅድ​ሳ​ቴ​ንም ናቁ፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም አረ​ከሱ። 9በው​ስ​ጥሽ ደምን ያፈ​ስሱ ዘንድ ሌቦች ሰዎች በአ​ንቺ ውስጥ ነበሩ፤ በአ​ንቺ ውስጥ በተ​ራ​ሮች ላይ በሉ፤ በመ​ካ​ከ​ል​ሽም የማ​ይ​ገባ ነገ​ርን አደ​ረጉ። 10በአ​ንቺ ውስጥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ኀፍ​ረተ ሥጋ ገለጡ፤ በአ​ን​ቺም ውስጥ አደፍ ያለ​ባ​ትን አዋ​ረዱ። 11ሰውም ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ሚስት ጋር ሰሰነ፤ አባ​ትም የል​ጁን ሚስት በኀ​ጢ​አት አረ​ከሰ፤ በአ​ን​ቺም ዘንድ ወን​ድም የአ​ባ​ቱን ልጅ እኅ​ቱን አስ​ነ​ወረ። 12በአ​ንቺ ውስጥ ደምን ያፈ​ስሱ ዘንድ መማ​ለ​ጃን ተቀ​በሉ፤ በአ​ን​ቺም አራ​ጣና ትርፍ ወስ​ደ​ዋል፤ ቀማ​ኛ​ነ​ት​ሽ​ንና ኀጢ​አ​ት​ሽን ፈጸ​ምሽ፤ እኔ​ንም ረሳ​ሽኝ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
13“ስለ​ዚህ እነሆ አንቺ ባደ​ረ​ግ​ሽው ሥራ፥ በመ​ካ​ከ​ል​ሽም በነ​በ​ረው ደም ላይ በእጄ አጨ​በ​ጨ​ብሁ። 14እኔ በማ​ደ​ር​ግ​ብሽ ወራት ልብሽ ይታ​ገ​ሣ​ልን? ወይስ እጆ​ችሽ ይጸ​ና​ሉን? እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ አደ​ር​ገ​ው​ማ​ለሁ። 15ወደ አሕ​ዛ​ብም እበ​ት​ን​ሻ​ለሁ፤ በሀ​ገ​ሮ​ችም እዘ​ራ​ሻ​ለሁ፤ ከአ​ን​ቺም ርኵ​ሰ​ትሽ ይጠ​ፋል። 16በአ​ሕ​ዛ​ብም ፊት ከአ​ንቺ እወ​ር​ሳ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”
17የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 18“የሰው ልጅ ሆይ! የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ የተ​ቀ​ላ​ቀሉ ናስና ቆር​ቆሮ፥ ብረ​ትና እር​ሳስ ሆኑ​ብኝ፤ በማ​ጣ​ሪ​ያም መካ​ከል የተ​ቀ​ላ​ቀለ ብር ሆኑ። 19ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሁላ​ችሁ አተላ ሆና​ች​ኋ​ልና ስለ​ዚህ እነሆ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውስጥ እሰ​በ​ስ​ባ​ች​ኋ​ለሁ። 20እን​ዲ​ያ​ቀ​ል​ጡት እሳት ያና​ፉ​በት ዘንድ ብር​ንና መዳ​ብን፥ ብረ​ት​ንና እር​ሳ​ስን፥ ቆር​ቆ​ሮ​ንም በከ​ውር እን​ደ​ሚ​ሰ​በ​ስቡ፥ እን​ዲሁ በቍ​ጣ​ዬና በመ​ዓቴ እሰ​በ​ስ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዚ​ያም ውስጥ እጨ​ም​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ አቀ​ል​ጣ​ች​ሁ​ማ​ለሁ። 21በላ​ያ​ችሁ የመ​ዓ​ቴን እሳት አነ​ድ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በመ​ካ​ከ​ሉም ትቀ​ል​ጣ​ላ​ችሁ። 22ብርም በከ​ውር ውስጥ እን​ደ​ሚ​ቀ​ልጥ፥ እን​ዲሁ በው​ስ​ጥዋ ትቀ​ል​ጣ​ላ​ችሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓ​ቴን እን​ዳ​ፈ​ሰ​ስ​ሁ​ባ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።”
የእ​ስ​ራ​ኤል መሪ​ዎች በደል
23የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 24“የሰው ልጅ ሆይ! አንቺ ዝናም የማ​ይ​ዘ​ን​ብ​ብሽ፥ በቍጣ ቀን ጠል የማ​ይ​ወ​ር​ድ​ብሽ ምድር ነሽ በላት። 25በመ​ካ​ከሏ ያሉ ነቢ​ያት እንደ አን​በሳ ያገ​ሳሉ፤ ይነ​ጥ​ቃሉ፤ ፈጽ​መ​ውም ይቀ​ማሉ፤ ሰው​ነ​ት​ንም ያጠ​ፋሉ፤ መማ​ለ​ጃ​ንም ይቀ​በ​ላሉ፤ በመ​ካ​ከ​ል​ዋም መበ​ለ​ቶ​ችዋ ይበ​ዛሉ። 26ካህ​ና​ቷም ሕጌን ጣሱ፤ በመ​ቅ​ደ​ሴም መካ​ከል ቅድ​ሳ​ቴን አረ​ከሱ፤ ከር​ኵ​ሰ​ትም አል​ራ​ቁም፤ በን​ጹ​ሕና በር​ኩስ መካ​ከል ያለ​ው​ንም ልዩ​ነት አላ​ወ​ቁም፤ ዐይ​ና​ቸ​ው​ንም ከሰ​ን​በ​ታቴ ሸፈኑ፤ እኔም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ረከ​ስሁ። 27በው​ስ​ጥዋ ያሉ አለ​ቆ​ችዋ የስ​ስ​ትን ትርፍ ለማ​ግ​ኘት ሲሉ ደምን ያፈ​ስሱ ዘንድ፥ ነፍ​ሶ​ች​ንም ያጠፉ ዘንድ እን​ደ​ሚ​ና​ጠቁ ተኵ​ላ​ዎች ናቸው። 28ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ይቀ​ቡ​አ​ቸ​ዋል፤ ከንቱ ነገ​ር​ንም ያዩ​ላ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አለ እያ​ሉም በሐ​ሰት ያም​ዋ​ር​ቱ​ላ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን አል​ነ​ገ​ራ​ቸ​ውም። 29የም​ድር ሕዝብ ግፍን አደ​ረጉ፤ ቅሚ​ያ​ንም ሠሩ፤ ድሆ​ች​ንና ችግ​ረ​ኞ​ችን አስ​ጨ​ነቁ፤ ለመ​ጻ​ተ​ኛ​ውም አል​ፈ​ረ​ዱ​ለ​ትም። 30ቅጥ​ርን የሚ​ጠ​ግ​ንን፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም እን​ዳ​ላ​ጠ​ፋት በፈ​ረ​ሰ​በት በኩል በፊቴ የሚ​ቆ​ም​ላ​ትን ሰው ከእ​ነ​ርሱ መካ​ከል ፈለ​ግሁ፤ ነገር ግን አላ​ገ​ኘ​ሁም። 31ስለ​ዚህ ቍጣ​ዬን አፈ​ሰ​ስ​ሁ​ባ​ቸው፤ በመ​ዓ​ቴም እሳት አጠ​ፋ​ኋ​ቸው፤ መን​ገ​ዳ​ቸ​ው​ንም በራ​ሳ​ቸው ላይ መለ​ስሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ